የፊት መሸፈኛ ጨርቅን መጠቀም (Mask)

  • Print

የፊት መሸፈኛ ጨርቅን መጠቀም የ COVID-19 ወረርሽኝ መስፋፋትን ለመቀነስ ያግዛል

የፊት መሸፈኛ ጭምብልን እንዴት መጠቀም እንደሚገባ፦
የፊት መሸፈኛው ጨርቅ (ጭምብል)፦
 የፊት ገጽን በማይጎዳ መልኩ በደንብ ጠበቅ ሊል ይገባዋል
 በጆሮ ላይ የሚደረገው ማሰሪያ ክር አስተማማኝ መሆን ይኖርበታል
 ለመከላከል አመቺ እንዲሆን በተደራራቢ ጨርቆች መሠራት ይገባዋል
 መተንፈስ እንዳይችሉ ማድረግ የለበትም
 ይዘቱንና ቅርጹን ሳይቀይር በልብስ ማጠቢያ ማሽን የሚታጠብና የሚደርቅ መሆን ይገባዋል



የበሽታ መቆጣጠርያ ማዕከል (CDC) በቤት ውስጥ በሚሠሩ የፊት መሸፈኛ ጭምብልን በተመለከተ
ርቀት ጠብቆ መጓዝ በማይቻልበት እንደ ምግብ መሸጫ መደብር እና መድኃኒት ቤት (ፋርማሲ) አካባቢ በተለይም ለበሽታው መተላለፊያ ዓይነተኛ ምክንያት ይሆናሉ በሚባሉት አካባቢዎች የፊት መሸፈኛ ጭምብል መደረግ እንዳለበት የበሽታ መቆጣጠርያ ማዕከል (CDC) ይመክራል።

ቫይረሱ እንዳለባቸው ሳያውቁ ለሌላ እንዳያስተላልፉና የቫይረሱንም መስፋፋት ለመቀነስ ስለሚያግዝ ማንኛውንም የአፍ መሸፈኛ ማድረግ ተገቢ መሆኑን ማዕከሉ (CDC) ይመክራል። በተመጣጣኝ ዋጋ በቤት ውስጥ የሚሠሩ የአፍ መሸፈኛ ጭምብሎች የሕዝብ ጤናን ለመጠበቅ ተጨማሪ ድጋፍ ይሆናሉ።

ዕድሜያቸው ከሁለት ዓመት በታች ያሉ ሕፃናት፣ የመተንፈስ ችግር ያለባቸው፣ ራሳቸውን የሳቱ፣ አቅመ ደካሞችና በቀላሉ ጭምብሉን ከላያቸው ላይ ማውረድ የማይችሉ ሰዎች የፊት መሸፈኛ ጭምብል ማድረግ የለባቸውም።

እንዲለበስ የተፈቀደው የፊት መሸፈኛ ጭምብል በሕክምና የተፈቀደ ወይም N-95 በመባል የሚታወቅ ለመተንፈስ የሚያስችል ጭምብል አይደለም። በሕክምና የተፈቀደው ጭምብል ለጤና ባለሙያዎች እና ለሌሎች ከጤና ጋር በተገናኘ የመጀመርያ ተንከባካቢዎች ሊያደርጉት የሚገባ በበሽታ መቆጣጠርያ ማዕከል (CDC) የተፈቀደ ነው።



የፊት መሸፈኛ ጭምብሎች በየጊዜው መታጠብ መጽዳት ይገባቸዋል? ተገቢስ ከሆነ በየስንት ጊዜው?
አዎ፤ እንደአጠቃቀማችን መጠን በየጊዜው መጽዳት አለባቸው።

ተጠቃሚዎች የፊት መሸፈኛ ጭምብላቸውን በጥንቃቄ ማጽዳት የሚችሉት እንዴት ነው?
ጭምብሉን በደንብ ለማጽዳት የልብስ ማጠቢያ ማሽን መጠቀም አስፈላጊ ነው።

ተጠቃሚዎች የፊት መሸፈኛ ጭምብላቸውን እንዴት ማውለቅ ይኖርባቸዋል?
ተጠቃሚዎች ጭምብላቸውን ሲያወልቁ ዓይናቸውን፣ አፍንጫቸውን እና አፋቸውን እንዳይነኩ መጠንቀቅ ይኖርባቸዋል። ጭምብሉን ካወለቁ በኋላም እጃቸውን ወዲያውኑ መታጠብ ይገባቸዋል።

Faith Community Health Program of the Holy Trinity EOTC, Minneapolis MN