በሜኔሶታ ሃገረ ገዢ የተላለፈውን ትእዛዝ Gov. Walz's Order May 13

  • Print

ከሜይ 18 2020 ወይም ከግንቦት 10 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ
በሜኔሶታ ሃገረ ገዢ የተላለፈውን ትእዛዝ እንዲያከብሩ እያሳሰብን ከዚህ በታች ያሉትን ማስታወሻዎች ይመልከቱ፣
** የችርቻሮ መደብሮች ፣ የገበያ አዳራሾች እና ሌሎች ዋና የአካባቢ ንግድ ሥራዎች የደህንነት ዕቅድ ካላቸውና እና ከ 50 በመቶ በማይበልጥ ይዘት ብቻ የሚሠሩ ከሆነ እንደገና ሊከፍቱ ይችላሉ።
** ምግብ ቤቶች ፣ መጠጥ ቤቶች ፣ ሳሎን እና ስፖርት ቤቶች እንደተዘጉ ይቆያሉ።
** ሚነሶታዎች 10 እና ከዛ በታች እስከሆኑ ድረስ ከጓደኞቻቸው እና ከቤተሰብ ጋር መሰባሰብ ይችላሉ።
** ማህበራዊ ፣ ሲቪክ/የከተማ እና ሕዝብ አስተዳደር ፣ ማህበረሰብ፣ በእምነት ላይ የተመሠረተ፣ መዝናኛ፣ ወይም ሃይማኖታዊ ስብሰባዎች ከ 10 በላይ ለሆኑ ሰዎች የተከለከሉ ናቸው።
** እነዚህን ጤናማ ልምዶች መከተልዎን ይቀጥሉ፣
• እጅዎን ቶሎ ቶሎ/ብዙ ጊዜ ይታጠቡ
• የበሽታው ሕመም ስሜቶች ከተሰማዎት ይመርመሩ
• ማህበራዊ ርቀት ይጠብቁ
• ጭምብል ያድርጉ
• ሲቻል ቤት ይቆዩ

ሙሉ ትእዛዙን ለማየት ይህንን ይጫኑ (Click here for order)

Faith Community Health Program of the Holy Trinity EOTC, Minneapolis MN
የምእመናን ጤና አገልግሎት ክፍል health@minnesotaselassie.