መዝሙር (የጠሩሽ) December 30, 2018

  • Print


 የጠሩሽ አንቺን ተማፅነው የዳኑብሽ
 የበላዔ ሰብ እመቤት የአምላክ እናት
 ድንግል አዛኝቱ ማርያም ቅድስት(፪)

በቃል ኪዳንሽ ብዙዎች ድነዋል
በምልጃሽም ፅድቅን አግኝተዋል
የአምላክ ቸርነቱን አይተዋል(፪)

 የጠሩሽ አንቺን ተማፅነው የዳኑብሽ
 የበላዔ ሰብ እመቤት የአምላክ እናት
 ድንግል አዛኝቱ ማርያም ቅድስት(፪)

የእሳት ባህር በአንቺ ተሻግረዋል
የሰይጣንን ቁልፍ በአንቺ ድል ነስተዋል
ለሰማያዊው ክብር በቅተዋል(፪)

 የጠሩሽ አንቺን ተማፅነው የዳኑብሽ
 የበላዔ ሰብ እመቤት የአምላክ እናት
 ድንግል አዛኝቱ ማርያም ቅድስት(፪)

ነፍሳቸውም ፅድቅን አግኝታለች
ህይወታቸውም በአንቺ ትድናለች
ድንግል ሆይ አ ትጣይን ትላለች(፪)

 የጠሩሽ አንቺን ተማፅነው የዳኑብሽ
 የበላዔ ሰብ እመቤት የአምላክ እናት
 ድንግል አዛኝቱ ማርያም ቅድስት(፪)

እኔም በአንቺ እታመናለሁ
የአምላክ እናት አትርሺኝ እላለሁ
በአማላጅነትሽ እድናለሁ(፪)

 የጠሩሽ አንቺን ተማፅነው የዳኑብሽ
 የበላዔ ሰብ እመቤት የአምላክ እናት
 ድንግል አዛኝቱ ማርያም ቅድስት(፪)

እኛም በአንቺ እንታመናለን
የአምላክ እናት አሳስቢ እንላለን
በአማላጅነትሽ እንድናለን (፪)

 የጠሩሽ አንቺን ተማፅነው የዳኑብሽ
 የበላዔ ሰብ እመቤት የአምላክ እናት
 ድንግል አዛኝቱ ማርያም ቅድስት(፪)

ምዕመናንም በአንቺ ይታመናሉ
የአምክ እናት አሳስቢን ይላሉ
በአማላጅነትሽ ይድናሉ (፪)

 የጠሩሽ አንቺን ተማፅነው የዳኑብሽ
 የበላዔ ሰብ እመቤት የአምላክ እናት
 ድንግል አዛኝቱ ማርያም ቅድስት(፪)