እንባና አንደበት -- ግጥም

እንባና አንደበት

እንባና አንደበት ውለው ከአደባባይ፤
ለአምላክ ሊያቀርቡ የደረሰባቸውን…
በደልና ስቃይ፤
እንባ አሸነፈ አሉ በፍጹም ዝምታ፤
እየገነፈለ ሆኖ መንታ መንታ።
‘አንድም’ ብሎ ትርጉም አንደበት ቢያቅተው፤
እንባ ፈተፈተው ምስጢርም አልቀረው።