Parent and Family Program Overview

  • Print

ዓላማ እና እቅድ Objective and Plan

ጽርሃ አርያም ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስትያን የተረካቢ ትውልድ ወላጆችና ቤተስብ ክፍል፣ ቤተክርስትያናችን ውስጥ ሥራ እየሠሩ ካሉት አካላት አንዱ አካል ሲሆን፣ ከቤተክርስትያናችን ወላጆች መካከል የተውጣጡ በጎ ፈቃደኞች በየሳምንቱ እየተወያዩ በመመካከር ሥራዎችን እየሠራ ይገኛል፣
ለጊዜው በእቅድ ከያዛቸው ሥራዎች መካከል የሚከተሉት ይካተታሉ፧
* ቤተሰቦች በልጆችና ቤተሰብ ዙሪያ እንዲወያዩ መድረኮችን ያመቻቻል
* ወላጆች በልጆቻቸው ትምህርት ነክ ጥያቄዎቻቸውን ከሌሎች አባላት ጋር እንዲወያዩ እድል ይፈጥራል
* ወላጆች በልጆች አስተዳደግ ዙሪያ የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች ከባለሙያ ጋር ተማክረው እንዲፈቱ እድሎችን ያመቻቻል ባለሙያዎችንም እየጋበዘ ለወላጆች ትምህርት እንዲያካፍሉ ያደርጋል
* ወላጆች በቤተሰብ ዙሪያ ችግሮቻቸውን በግልፅነት እየተወያዩ መፍትሄ የሚያገኙበትን እድል ይፈጥራል
* የቤተክርስትያናችን አባላት ወደመንፈሳዊ አባቶቻቸው ይበልጥ እንዲቀራረቡና እንዲወያዩ እድል ይፈጥራል
* እንደያስፈላጊነቱና እንደወላጆች ፍላጎትና ጥያቄ ተከታታይ ትምህርቶችን ያዘጋጃል፣ ያወያያል