* በአዲሱ የኦባማ ሕግ መሠረት ማንኛውም ነዋሪ የጤና ኢንሹራንስ (Health Insurance) ሊኖረው ይገባል። በመሆኑም አሠሪዎች ለሠራተኞች በዓመቱ መጨረሻ 1095C ወይም 1094 C ፎርም ይልካሉ። ያም ፎርም አሠሪው ለሠራተኛው በቂ ኢንሹራንስ እንዲኖረው ማድረጉንና ሠራተኛውም ምን ያህል እንደተጠቀመ ለIRS ሪፖርት ያደርግበታል።
* በቀረበው ሪፖርት ላይ ሠራተኛው ሙሉ ዓመት የኢንሹራንስ ተጠቃሚ መሆን ሲገባው በተለያዩ ምክንያቶች የግማሽ ዓመት ብቻ ኢንሹራንስ ካስገባ የዓመቱ ተመላሽ ታክስ ላይ ቅጣት ይኖረዋል።
* ኦባማ ኬር ኢንሹራንስ (Obamacare) በትንሹ $9.00 በሳምንት በመክፈል ማግኘት ይቻላል። ይህም ክፍያ እንደ ገቢዎ መጠን ይወሰናል። በስልክ ቁጥር 1-800-909-0428 ቢደውሉ የመጠየቂያ ፎርሙን ማግኘት ይችላሉ።
* ከኢሚግሬሽን ቢሮ (US Citizenship and Immigration office ) የነዋሪነት መታወቂያ እንዴት ማግኘት እንደሚችሉ ጥያቄ ቢኖርዎ በስልክ ቁጥር 1-800-375-5283 በመደወል ማነጋገር ይችላሉ።
* አፓርትመንት የሚፈልግልዎት ካምፓኒ ቢያስፈልግዎ በስልክ ቁጥር 1-888-658-7368 በመደወል ማነጋገር ይችላሉ።
በወ/ት ዘመናይ ዘሪሁን