የግልዎ መኖሪያ ቤት እንዲኖሮዎ አስበው ያውቃሉ?

የግል ሥራ ኖሮዎት እንዴት የቤት ባለቤት መሆን ይችላሉ?

* ቢያንስ ለሁለት ዓመት የግል ሥራ ላይ መሆንዎን አበዳሪዎች ያጣራሉ

* ታክስ በኋላ ያለውን ገቢ ሳይሆን አጠቃላይ ገቢዎን ያሳያሉ

 Conventional/ Non-governmental የሆነውን ብድር ጥሩ ወይም መጠነኛ Credit ካለዎት አበዳሪዎች እስ 3% ከፍለው ለቤትዎ መግዢያ ብድር ሊያገኙ  ይችላሉ።

የግል ሥራ ኖሮዎት ቤት ለመግዛት ብድር ሲያስቡ፦

* በተቻለ መጠን በዛ ያለ ተቀማጭ ወደ ባንክዎ  በአንዴ አያስቀምጡ  ለምሳሌእቁብ ምክንያቱም አበዳሪዎች ያኛው ገቢ ምንጩ  ምን እንደሆነ ለማጣራት ይፈልጋሉ፤ ያም የብድር ፕሮሰሱን  ያጎትትብዎታል።

* ሁለት ሥራ ካለዎት በሳምንት አርባ ሰዓት (full time) እና በሳምንት ከአርባ ሰዓት በታች (part time) የሚሠሩ ከሆነ

አበዳሪው ባንክ በሳምንት ከአርባ ሰዓት በታች የሚሠሩት ሥራ ገቢ ተቀባይነት እንዲኖረው በሥራው ላይ ቢያንስ ከሁለት በላይ መሆንዎትን ያረጋግጣል። 

* ለሌላ ሰው በስምዎ ፈርመው ተበድረው ከሆነ እርስዎ ላይ እንደ  ራስዎ ዕዳ ሆኖ ይቆጠራል።

Bank statement አኩያ ደግሞ፤

The "Rule of Thumb" የገቢ፤ ወጪ ውህደት፡ ስልሣ ቀኖች ወይም ለሁለት ወር ያህል ተመሳሳይ ሊሆን ይገባል። አለበለዚያ ባንኩ ጥርጣሬ ያድርበትና የብድሩን ጊዜ ያራዝምብዎታል ወይም እስክ መከልክል ድረስ ያደርሳል ማለት ነው።

 

ወ/ት ዘመናይ ዘሪሁን