ዚካ ቫይረስ ምንድን ነው? ዚካ ቫይረስ በትንኝ ንክሻ የሚተላለፍ የበሽታ ዓይነት ነው። የተለመዱ የዚካ ቫይረስ ዋነኛ የበሽታ ምልክቶች ትኩሳት፣ የቆዳ ሽፍታ፣ የመገጣጠሚያ ሕመም፣ እና የዓይን ማዝ (የዓይኖች መቅላት) ናቸው።
ዚካ ቫይረስ እንዴት ነው የሚተላለፈው? ዚካ ቫይረስ በዋነኛነት በበሽታው አምጪ ተሐዋሲያን በታጠቀ ኤዴስ በሚባል የትንኝ ዝርያ አማካይነት ወደ ሰዎች ይተላለፋል። ትንኞቹ በተለምዶ እንደ ባልዲ፣ ማስታጠቢያ ሳፋዎች፣ የእንስሳት መመገቢያ ሣህኖች፣ የአበባ መትከያ ጎድጓዳ ሣህኖች፣ እና በቫዞች ውስጥ ወይም አቅራቢያ እንቁላሎቻቸውን ይጥላሉ። በቀን ሳይቀር የሚናከሱ ኃይለኛ ትንኞች ናቸው፣ ሰዎችን መንከስ እና ከሰዎች አቅራቢያ በቤት ውስጥ እና ከቤት ውጪ መኖርን ይመርጣሉ። ትንኞቹ በቫይረሱ የተጠቃን ግለሰብ ደም በሚመጡበት ጊዜ በበሽታው ይጠቃሉ። ከዚህ በመቀጠል በበሽታው የተጠቁ ትንኞች ቫይረሱን በንክሻ አማካይነት ወደ ሌሎች ጤናማ ሰዎች ማስተላለፍ ይችላሉ። የመውለጃ ጊዜዋ በተቃረበበት ጊዜ በዚካ ቫይረስ የተጠቃች እናት ወደ አዲስ የሚወለደው ልጇ በወሊድ ጊዜ በሽታውን ልታስተላልፍበት ትችላለች። ከዚህ በተጨማሪ የዚካ ቫይረስ በእርግዝና ወቅት ከእናት ወደ ፅንሱ ሊተላለፍ ይችላል።
ዚካ አዲስ መጤ ቫይረስ ነው። እስከ ጃንዋሪ 2016 ድረስ ጡት በመጥባት አማካይነት በዚካ ቫይረስ የተያዙ ጨቅላ ሕፃናቶች እንዳሉ የተደረጉ ምንም ሪፖርቶች የሉም። የተወለዱ ሕፃናትን ጡት ማጥባት ካሉት ጠቀሜታዎች አንፃር፣ ዚካ ቫይረስ በተገኘባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ እናቶችም ሳይቀሩ ልጆቻቸውን ጡት እንዲያጠቡ ይበረታታሉ። እስከ ጃንዋሪ 2016 ድረስ የሰው ደም በመቀበል የተነሳ አንድ ሪፖርት እና በግብረ ሥጋ ግንኙነት በሽታው ስለመተላለፉ የሚያረጋግጥ አንድ ሪፖርት ተገኝቷል።
የዚካ ቫይረስ የበሽታ ምልክቶች ምንድን ናቸው? በዚካ ቫይረስ ከተጠቁ 5 ሰዎች መካከል አንዱ ይታመማል (ማለትም፣ ዚካ ይይዘዋል)። የተለመዱ የዚካ ቫይረስ ዋነኛ የበሽታ ምልክቶች ትኩሳት፣ የቆዳ ሽፍታ፣ የመገጣጠሚያ ሕመም፣ እና የዓይን ማዝ (የዓይኖች መቅላት) ናቸው። ሌሎች የተለመዱ የበሽታ ምልክቶች የጡንቻ ሕመም እና ራስ ምታት ናቸው። በሽታው ብዙውን ጊዜ የበሽታው ምልክቶች ከበርካታ ቀናት እስከ አንድ ሳምንት ሊቆዩ የሚችሉ ቀለል ያሉ የበሽታ ምልክቶች ናቸው። ሆስፒታል ተኝቶ እስከ መታከም የሚያደርስ በሽታ እስካሁን አላጋጠመም። በበሽታው የተነሣ የሚያጋጥም ሞት ብዙም የለም። የበሽታ ምልክቶቹ ካሉብዎት እና ዚካ ቫይረስ እንዳለባቸው በሚታወቁ ቦታዎች ላይ ከነበሩ በእርስዎ የጤና እንክብካቤ ሰጪ ይታዩ። በቅርቡ ጉዞ አድርገው ከነበረ፣ መቼ እና የት ጉዞውን እንዳደረጉ ለእርስዎ የጤና እንክብካቤ ሰጪ ይንገሩ።
የዚካ ቫይረስ እንዴት ነው የሚታከመው? ምንም ክትባት ወይም መድኃኒት የዚካ በሽታን ለመከላከል ወይም ለማከም እስካሁን
አልተገኘም። የበሽታ ምልክቶቹን ያክሙ፦
¨ በጣም ብዙ ዕረፍት ያድርጉ።
¨ የሰውነት ፈሳሽ ክፉኛ መወገድን ለመከላከል ፈሳሽ በብዛት ይጠጡ።
¨ እንደ አሴታሚኖፊን [acetaminophen] ወይም ፓራሴታሞል [paracetamol] የመሳሰሉ መድኃኒቶችን ትኩሳትን እና ሕመምን ለማስታገስ ይውሰዱ።
¨ አስፕሪን እና ሌሎች ስቴሮይዳል የሕመም ማስታገሻ መድኃኒቶች [non-steroidal anti-inflammatory drugs (NSAIDs)]
¨ እንደ ኢቡፕሮፌን [ibuprofen] እና ናፕሮክሴን [naproxen] የመሳሰሉ መድኃኒቶች የደም ያለማቋረጥ መፍሰስን ለመከላከል እስኪቻል እስከ ደንግ [dengue] ድረስ ከመውሰድ መቆጠብ ያስፈልጋል። በሌላ ሕክምና ምክንያት መድኃኒት እየወሰዱ ያሉ ከሆኑ፣ ተጨማሪ መድኃኒት ከመውሰድዎ በፊት የጤና እንክብካቤ ሰጪ ያነጋግሩ።
ዚካ ቫይረስ ካለብኝ ምን ማድረግ አለብኝ? ዚካ ቫይረስ ካለብዎት በሽታው በሚሰማዎት የመጀመሪያው ሳምንት ላይ በትንኝ ከመነከስ ራስዎን ይከላከሉ።
¨ በሽታው በያዘበት የመጀመሪያው ሳምንት ወቅት የዚካ ቫይረስ በደም ውስጥ ሊገኝ እና በትንኝንክሻ አማካይነት ከአንድ ሰው ወደ ሌላ ሊተላለፍ ይችላል።
¨ ከዚህ በመቀጠል በበሽታው የተጠቃ ትንኝ ቫይረሱን ወደ ሌሎች ሰዎች ማስተላለፍ ይችላል።
ዚካ ቫይረስን ለመከላከል የተሻለው አማራጭ በትንኝ ከመነከስ ራስን መጠበቅ ነው።
ምን ማድረግ እችላለሁ? 4ቱን ዲዎች በመጠቀም ይከላከሉ።
በየቀኑ ሙሉ ቀን DEET ይጠቀሙ፦ በማንኛቸውም ጊዜ ከቤት ውጪ በሚሆኑበት ጊዜ DEET ወይም ሌላ በ EPA የተፈቀደ ፀረ ትንኝ ኬሚካል ይጠቀሙ እና መመሪያዎቹን ይከተሉ።
መከላከያ ልብስ ይልበሱ [Dress]፦ ረዥም እጅጌ ያላቸው ሰውነት ላይ የማይጣበቁ ፈዛዛ ቀለም ያላቸውን ልብሶች ከቤት ውጪ ሲሆኑ ይልበሱ።
ውሃ ያቆሩ ቦታዎችን ያድርቁ [Drain]፦ ሁሉንም የተጠራቀመ ውሃ ከቤትዎ ውስጥ እና አካባቢ ያስወግዱ።
ማለዳ እና ምሽት [Dusk & Dawn]፦ ትንኞች በጣም ንቁ በሚሆኑበት የማለዳ እና የምሽት ጊዜዎች ላይ ከቤት ውጪ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን መጠን ገደብ ያብጁላቸው።
ከ4ቱ ዲዎች [4Ds] በተጨማሪ ጉዞ የሚሄዱ ሰዎች የሚከተለውን በማድረግ ራሳቸውን መጠበቅ ይችላሉ፦
¨ የአየር መቆጣጠሪያ ወይም በመስኮቶች ወይም በበሮች ላይ መከላከያ ሽፋን ያላቸውን ሆቴሎች ይምረጡ።
¨ ከቤት ውጪ ከሆኑ በአጎበር ውስጥ ሆነው አልጋ ላይ ይተኙ ወይም ባልተከፋፈተ ክፍል ውስጥ ይተኙ።
ምንጭ፦Dallas CHHS, State of Texas