ነጻ የኢንፍሉዌንዛ ክትባት ይሰጣል

 

*  ቦታ፦   በጽርሐ አርያም ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል

 

*  ቀን፦    Oct. 23,2016

 

*  ጊዜ፦    10:30AM to 12:30PM

 

*  ቼ፦  እሑድ ጥቅምት ፲፫/፳፻፱ ዓ.ም.

 

ለመላው አንባብያን፦

 

ዕድሜው ስድስት ወርና ከዚያም በላይ ያለ በሙሉ ከፍሉ በሽታ ለመከላከል የዓመት ክትባት መውሰድ ይኖርበታል። የበለጠ ለመረዳት እና የት ቦታ ክትባቱን መውሰድ እንደሚገባ ለማወቅ ይኽን ድረ-ገጽ ይጎብኙ፦  www.flu.gov

ዕርጉዝ ሴቶች፣ ወጣት ልጆችና ጎልማሶች ከፍሉ ጋር ተያይዞ በሚመጣ በሽታ ይበልጡን ተጠቂዎች ናቸው። በመሆኑም በአቅራቢያችሁ የሚገኙትን እነዚህን ሰዎች ክትባቱን እንዲወስዱ አበረታቷቸው።

የፍሉ ክትባቱን ይውሰዱ። ደግሞም ጀርሞቹን ከማስተላለፍ እንዲቆጠቡ እጅዎትን በውኃና በሳሙና ይታጠቡ፤ እንዲሁም አልኮልነት ባላቸው ጨርቆችና ማድረቂያዎች ይጠቀሙ።

መደበኛ ዶክተር የለዎትም? ከሌለዎ በአቅራቢያዎ በሚገኙ የክልል ጤና መስጫ ሥፍራዎች፣ መድኃኒት ቤቶች/ ፋርማሲዎች/፣ በትምህርት ቤት ውስጥ በሚገኙ የጤና ክፍሎች በአምልኮ ስፍራዎ በሚገኙ የጤና አገልግሎት ጣቢያዎች ወይም የአስቸኳይ ርዳታ መስጫ ክሊኒኮች በመሄድ ክትባቱን ይውሰዱ። የፍሉ መከላከያ ክትባት ከወሰዱ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ክትባቱ አያገለግልም። የባለፈው ዓመት ክትባትም ለአሁኑ ዓመት አይጠቅምም። በመሆኑም ከበሽታው ለመጠበቅ በየዓመቱ ክትባቱን መውሰድ ያስፈልጋል።

በዓመት ከአርባ ሺህ አማሪካውያን በላይ በፍሉ በሽታ ሰለባ ይሆናሉ። ይኽን ለመከላከል ክትባት መውሰድ ይቻላልና ተከተቡ።

ነፍሰ-ጡር /ዕርጉዝ/ ሴቶች፦

መውለጃ ጊዜዎ ተቃርቧል? በፍሉ በሽታ መያዝ እንደ ንሞንያ pneumonia የመሰለ ውስብስብ ችግሮችን ያስከትላል። ክትባቱን በመውሰድ እርስዎንና ሕፃኑን/ሕፃኗን ከበሽታው ይከላከሉ።

መውለጃ ጊዜዎ ተቃርቧል? የፍሉ ክትባትን በመከተብ በሕፃኑ/በሕፃኗ ላይ በመጀመርያዎቹ ወራት ሊመጣ ከሚችል በሽታ መከላከል ይቻላል። ስለዚህም ዛሬውኑ ይከተቡ።

ወላጆች፦

ዕድሜያቸው ከስድስት ወር በታች ያሉ ሕፃናት የፍሉ ክትባትን መውሰድ ባይችሉም በበሽታው ግን ቶሎ የመጋለጥ ዕድል አላቸው። ልጆቻችሁ ከፍሉ በሽታው ለመጠበቅ የእናንተን አጋዥነት ይፈልጋሉ።

ወላጆች፦ እናንተም ሆናችሁ በሕፃናቱ አቅራቢያዎች የሚገኙት በሙሉ በየዓመቱ ይኽንን የፍሉ ክትባት መውሰዳችሁን እርግጠኖች ሁኑ። ታዳጊ ሕጻናት በከፍተኛ ሁኔታ በበሽታው ይጋለጣሉ።

ወላጆች፦ የፍሉ ክትባትን መውሰድ በቤተሰብዎ መካከል ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባዋል። በሜኒሶታ አካባቢ የፍሉ ክትባት በሰፊው ይገኛል።

 

For more questions visit the source:

* www.flu.gov or www.cdc.gov/fl

* Faith Community Health Program of the Holy Trinity EOTC, 2601 Minnehaha Ave S, Minneapolis MN, 55406.

* health@minnesotaselassie.org

 

ይስሐቅ ቱራ (RN)