የዚህ ወር የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ጥያቄዎቻችንን ለመመለስ የቅዱስ ማቴዎስን ወንጌል ማጥናት ያስፈልግዎታል።
፩. ከአብርሃም እስከ ዳዊት፤ ከዳዊት እስከ ባቢሎን ምርኮ፤ ከባቢሎን ምርኮ እስከ ክርስቶስ በጠቅላላ ስንት ትውልድ አለ?
፪. በሔሮድስ ፈንታ በይሁዳ የነገሠ ንጉሥ ማን ነበር?
፫. የዮሐንስ ወንጌላዊ ልብስ የተሠራው ከምን ነበር?
፬. ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የአባታችን ሆይ ጸሎት ያስተማረበት የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ የትኛው ነዉ?
፭. ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ በመጀመርያ እንዲከተሉት የጠራቸው ሁለት ሐዋርያት እነማን ነበሩ?
፮. “እርሱ ድካማችንን ተቀበለ ደዌያችንንም ተሸከመ የተባለው ይፈጸም ዘንድ፥ መናፍስትን በቃሉ አወጣ፥ የታመሙትንም ሁሉ ፈወሰ” በማለት ትንቢት የተናገረው ማን ነበር?
፯. የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተከታይ ሐዋርያ ከመሆኑ በፊት የቅዱስ ማቴዎስ ሥራ ምን ነበር?
፰. የአሥራ ሁለቱን ሐዋርያት ስሞች ይዘርዝሩ!
፱. “ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከርሱ የሚበልጥ አልተነሣም” ብሎ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተናገረለት ነቢይ ማን ነበር?
፲. ጻፎችና ፈሪሳውያን መምህር ሆይ ከአንተ ምልክት እንድናይ እንወዳለን በማለት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ሲጠይቁት፤ እርሱ ግን “ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይሻል፥ ከነቢዩ ምልክት በቀር ምልክት አይሰጠውም“ በማለት መልስ ሲሰጣቸው ስለየትኛው ነቢይ እየተናገረ ነው?
፲፩. ጌታችን አምስት እንጀራና ሁለት ዓሣ ባርኮ በደቀ መዛሙርቱ በኩል ለሕዝቡ ሲሰጥ ሁሉም በልተው ከጠገቡ በኋላ የተረፈው ቁርስራሽ ምን ያህል ነበር? ከሴቶችና ከልጆች በቀር የተመገቡት ምን ያህል ወንዶች ነበሩ?
፲፪. ከታንኳ ወርዶ ወደ ኢየሱስ ሊደርስ በውኃ ላይ የሄደ ሐዋርያ ማን ነበር?
፲፫. “እናንተስ እኔን ማን እንደሆንሁ ትላላችሁ” በማለት ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን በጠየቀበት ወቅት ማን መለሰለት? ምንስ ብሎ መለሰ?
፲፬. ትንሣኤ ሙታን የለም በማለት የሚያምኑ የእስራኤላዊያን ወገን የትኞቹ ናቸው?
፲፭. “እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው” የሚለው የመጽሐፍ ቅዱስ አንቀጽ የትኛው ነው?