"ጽርሐ አርያም" የተሰኘው ይኽ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ርእሰ አድባራት ጽርሐ አርያም ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እየተዘጋጀ ለምእመናን የሚወጣው ወርኃዊ ጋዜጣ ለመጀመርያ ጊዜ ዛሬ ሚያዝያ ፲፮/፳፻፰ ዓ.ም. (Apr. 24/2016) በሰበካ ጉባኤው አሳሳቢነትና አስተባባሪነት በተዋቀረው የአዘጋጅ ክፍል የቤተ ክርስቲያናችን ቀኖና (ሥርዓት) ተጠብቆ መጓዝ አለብን በማለት የመጨረሻ ውሳኔያችንን በቁርጠኝነት በገለጽንበት በሁለተኛው ዓመት በዕለተ ሆሣዕና በእንዲህ ያለ መልኩ ለምእመናን ቀርቧል። ይኽ ወርኃዊ ጋዜጣ ከተለዋዋጭ ዓምዶቹ ባሻገር  ዜና ርእሰ አድባራት፣ ትምህርተ ሃይማኖት፣ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን፣  ነገረ ቅዱሳን፣ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ፣ ይህን ያውቁ ኖሯል? ቅዱሳት መጻሕፍት፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት (ጥያቄና መልስ)፣ ወጣቶች እና ሕፃናት (Amharic and English)፣ የቤተሰብ ዓምድ፣ የጤና አምድ፣ የወሩ እንግዳ፣ ማስታወቂያ እና ጠቃሚ መረጃዎች የሚሉ ቋሚ ዓምዶች ይኖሩታል። የዚህ ክፍል አዘጋጆች ጋዜጣው የሁላችን መማማሪያ መሆኑን በማመን ሙያዊ እገዛ ለሚያደርጉ እና ከላይ በተዘረዘሩት ዓምዶች ውስጥ የተለያዩ መንፈሳዊ ጽሑፎችን ለሚያቀርቡ ምእመናን የክፍሉን መስፈርት እስካሟሉ ድረስ በሩ ክፍት መሆኑን እናሳውቃለን። 

ወርኃዊ ጋዜጦች ሁልጊዜ በወሩ መጨረሻ ባለው ሳምንት በድረ-ገጻችን www.minnesotaselassie.org/newsletter ላይ ይወጣሉ። አንባብያን ትምህርቱን ከመከታተል፣ መልእክቶቹን ከማወቅና ጠቃሚ መረጃዎችን ከመረዳት ባሻገር የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት በጥያቄና መልስ እንዲሁም በሰንጠረዥ መልኩ ስለሚቀርብ ለልጆቻችሁ ማስተማርያ እንዲሆን ተሳታፊነታችሁ አስፈላጊ ነው እንላለን። ከዚህ በተጨማሪም ወጣቶች እና ሕፃናት በሚለው ዓምዳችን ላይ ሕፃናት የሚሳተፉበት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥያቄዎች ስላሉ የጋዜጣችን ተከታታይ እንድትሆኑ በቤተ ክርስቲያናችን ስም እንጋብዛለን።

የአዘጋጆች መልዕክት

 

What is Tserha Aryam?

"Tserha Aryam" is a monthly newsletter that includes timely religious articles, messages from clergy, youth-focused articles, announcements, and other contents that are relevant to the parishioners of Tserha Aryam Kidist Selassie Cathedral EOTC. Tserha Aryam is distributed monthly through email and the newsletter's website at www.minnesotaselassie.org/newsletter.

Previous newsletter issues can be accessed from the Archives section.

To contact the editors

Please email your comments, questions and suggestions to us at This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it..

Church's Site

Click here to go to the Church's website