የርእሰ አድባራት ጽርሐ አርያም ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን በተለያዩ ተቋማት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ቆይተው ከሁለተኛ ደረጃ እና ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለተመረቁ ምዕመናን ቡራኬ ከደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ አርያም ቆሞስ አባ ኃይለሚካኤል May 21, 2017 እንዲቀበሉ አደረገች። በዓይነቱ የመጀመሪያ በሆነው በዚህ ዝግጅት ላይ 26 ተመራቂዎች በዝርዝር የቀረቡ ሲሆን፤ ከሁለተኛ ደረጃ ጀምሮ እስከ ዶክትሬት ዲግሪ ድረስ ትምህርታቸውንን ያጠናቀቁ ምዕመናን ተገኝተውበታል። ተመራቂዎች ወደ አውደ ምሕረት እየተጠሩ ቡራኬ ሲቀበሉ የቤዛ ኲሉ ሰንበት ትምህርት ቤት ዘማርያን እና ምዕመናን "እግዚአብሔር ይመስገን ለዚህ ላደረሰን" የሚለውን መዝሙር በመዘመር ለእግዚአብሔር ምስጋናን አቅርበዋል።
ከቡራኬው በኋላ የደብሩ አስተዳዳሪ የእንኳን ደስ አላችሁ መል ዕክት አስተላልፈዋል። በመልዕክታቸውም ከሁለተኛ ደረጃ ለተመረቁት በሚቀጥለው የትምህርት ቤት ጉዟቸው ላይ በማተኮር እንዲበረቱ አሳስበው በተጓዳኝ ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሳይርቁ እንዲጓዙ መክረዋል። ወላጆችም በዚህ ጉዳይ ክትትል በማድረግ እንዲያበረቷቸው በአንክሮ አሳስበዋል። ከዛም በመቀጠል በመጀመሪያ እና በከፍተኛ ትምህርት ዲግሪያቸውን የተቀበሉትን ተመራቂዎች በተለያዩ የቤተ ክርስቲያን የአገልግሎት ክፍሎች ው ስጥ በመሳተፍ በየሙያቸው እንዲያገለግሉ በመምከር እግዚአብሔርም በሚሠሩት ሁሉ እንዲረዳቸው አባታዊ ቡራኬ ሰጥተዋል።
ከቅዳሴ በኋላም በደጀ ሰላም ውስጥ በተደረገው ዝግጅት ተመራቂዎች ራሳቸውን በማስተዋወቅ ምን እንደተማሩና ወደፊት ምን ሊማሩ እንዳቀዱ ለተሰበሰበው እድምተኛ ገልጸዋል። በተለይም በመቶዎች የሚቆጠሩ ሕፃናት ከተመራቂዎች ፊት ለፊት ተቀምጠው ይኽንን ደስታ አብረው እንዲካፈሉ መደረጉ ምዕመናንን ካስደሰቱ ጉዳዮች ዋነኛ እንደሆነና ሕፃናቱም ላይ የሚፈጥረው ገንቢ ተጽእኖ በማሰብ ይኽን ዓይነቱ ዝግጅት ሊበረታታ እንደሚገባው ብዙዎች ሐሳብ ለግሰዋል።
በወቅቱ በእንግድነት በቤተ ክርስቲያናችን የተገኙት መጋቢ ጥበብ በእምነት በቀለ ከእራሳቸው የትምህርት ጉዞ ተመክሮ በመነሳት ተመራቂዎችን የበለጠ በትምህርታቸው እንዲገፉ የሚያነሳሳና በተማሩበት ሙያ ሃገራቸውን እና ቤተ ክርስቲያናቸውን እንዲያገለግሉ የማይረሳ ምክር አስተላልፈዋል። በተጨማሪም መጋቢ ጥበብ ፊት ለፊት ተቀምጠው በጥሞና የሚከታተሉትን ሕፃናት እየተደረገ ስላለው ሂደት ሊረዱት በሚችሉበት ቋንቋ አብራርተው፤ ሕፃናቱም በርትተው በመማር በዕለቱ ተመራቂዎች የያዙትን ቦታ እነሱም እንደሚይዙት በእርግጠኝነት ገልጸዋል።
ቀጥለውም ሕፃናቱ ያላቸውን ማንኛውንም ጥያቄ ለተመራቂዎች እንዲጠይቁ እድል ከፍተዋል። በመጀመሪያ እድል የተሰጠው የ6 ዓመት ሕፃን ልጅ "ከተመራቂዎች ፊት የተደረደረውን ኬክ፤ ተመራቂዎች ብቻ ናቸው ወይ የሚበሉት?" ብሎ በመጠየቅ በደጀ ሰላም የተሰበሰበውን ምዕመን በጣም አስቋል። ተመራቂዎች ከሕፃናቱ የቀረቡላቸውን ጥያቄዎች ካስተናገዱ በኋላ በመጋቤ ኅሩያን ቀሲስ መጽናኛዬ ምክር እና የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት የዕለቱ መርሐ-ግብር በደስታ እና በምስጋና መንፈስ ተቋጭቷል። ይህን ላደረገ አምላካችን ክብርና ምስጋና ይግባው። ተመራቂዎች እና ወላጆች እንኳን ደስ አላችሁ። ይኽንን ፕሮግራም እንዲሳካ ላደረጋችሁ ምዕመናን ሁሉ እግዚአብሔር ይስጣችሁ።
High School
1. BedeMariam Tsegaye
2. Dina Teferi
3. Egeziharya Yilma
4. Kidist Chaka
5. Ledet Bayou
6. Meron Negash
7. Michael Mamo
8. Teferi Belete
9. Tensae Mekonnen
10. Yacob Yisehak
11. Zablon Teferi
12. Hana Dereje
College/University
1. Abenet Wordofa (St. Paul College: CNC Machine Tool Making)
2. Bethlehem Alem (St. Cloud State University: Biomedical Science)
3. Daniel Cheriye (University of Minnesota: MD)
4. Daniel Yilma (St. Thomas: MS in Elect. Engineering)
5. Frezer Yimer (Hamline: MBA)
6. Hewan Redie (Metro State University: Comp. Science)
7. Lelna Desta (St. Thomas: MBA)
8. Lilli Terefe (St. Paul College: Licensed Practical Nursing)
9. Mariam Tadesse (Hamline: Political Sci.; Minor Law)
10. Million Woldehawariat (Hamline: MBA)
11. Nuela Elias (St. Cloud State University: International Business Marketing; Minor Economics)
12. Ruth Mamo (University of Minnesota: Biology)
13. Saron Kassahun Chekol (St. Cloud State University፡ Biomedical Sciences and minor in Chemistry)
14. Tsigereda Abebe (University of Minnesota: Biology)