- Written by ወ/ት ዘመናይ ዘሪሁን
ቅዳሴ፣ ማሕሌት፣ ኪዳን፣ ምህላ እና ንግሥ
+ ዓመቱን በሙሉ ኪዳን ይደርሳል (6:00 A.M)
+ ዘወትር እሑድ ቅዳሴ ይቀደሳል
+ በሥላሴ፣ በመድኃኔዓለም፣ በማርያም፣ በሚካኤል እና በዮሐንስ ወርኃዊ በዓላት ይቀደሳል (የክርስትና ማንሳት አገልግሎት ይሰጣል)
+ ጥርና ሐምሌ ሥላሴ፣ ጥቅምት እና መጋቢት መድኃኔዓለም፣
ኅዳር እና ሰኔ ሚካኤል፣ ሰኔና መስከረም ዮሐንስ ይነግሣል
+ በጾመ ፍልሰታ የሱባኤ ወቅት ሰዓታት ይቆማል፣ ውዳሴ ማርያምና ቅዳሴ ማርያም ይተረጎማል፣ ቅዳሴ እና የሰርክ ጸሎት ይደርሳል
+ በአዲስ ዓመት (በዘመን መለወጫ)፣ በልደት በትንሣኤ እና ቤተ ክርስቲያናችን ባሏት ተጨማሪ ዐበይት በዓላት የተለያዩ መርሐ-ግብሮች ይከናወናሉ።
+ በሰሞነ ሕማማት ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ሙሉ አገልግሎት ይሰጣል
ስብከተ ወንጌል እና መንፈሳዊ ትምህርት
+ ዘወትር አርብ ስብከተ ወንጌል ይሰጣል
+ ዘወትር ቅዳሜ መላ ምእመናንን የሚያሳትፍ የሰንበት ትምህርት ቤት መርሐ-ግብር ይደረጋል
+ ዘወትር ቅዳሜ የአብነት ትምህርት እና መሠረታዊ የአማርኛ ቋንቋ ለወጣቶችና ለታዳጊ ሕፃናት ይሰጣል
+ ዘወትር እሑድ ሃይማኖታዊና የሥነ-ምግባር ትምህርት ለሕፃናት እና ለወጣቶች ይሰጣል
ዕድር
+ የቤተ ክርስቲያናችን አባላት የሆኑ ብቻ በአባልነት ተመዝግበው በኀዘናቸው ጊዜ መርጃ እንዲሆናቸው ታስቦ የተቋቋመው ዕድር ለአባላት አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል።
ለከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ፣ ለኮሌጅ እና ዪኒቨርስቲ ተማሪዎች
+ ዘወትር ቅዳሜ በከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ፣ በኮሌጅ እና ዪኒቨርስቲ የቀለም (ዘመናዊ) ትምህርት በመከታተል ላይ ለሚገኙ ተማሪዎች ለሚያነሱት ጥያቄዎች በሙሉ፤ በተለይም የከበዳቸውን እና የተለያዩ የትምህርት ተቋማትን አስመልክቶ ጥያቄ ቢኖራቸው የምክር እና የትምህርት አገልግሎት (mentoring & tutoring programs) ይሰጣል።
በወ/ት ዘመናይ ዘሪሁን