- Written by ወ/ት ዘመናይ ዘሪሁን
ቅዳሴ፣ ማሕሌት፣ ኪዳን፣ ምህላ እና ንግሥ
* ዓመቱን በሙሉ ኪዳን ይደርሳል (6:00 A.M)
* ዘወትር እሑድ ቅዳሴ ይቀደሳል
* በሥላሴ፣ በመድኃኔዓለም፣ በማርያም፣ በሚካኤል እና በዮሐንስ ወርኃዊ በዓላት ይቀደሳል (የክርስትና ማንሳት አገልግሎት ይሰጣል)
* ጥርና ሐምሌ ሥላሴ፣ ጥቅምት እና መጋቢት መድኃኔዓለም፣ ኅዳር እና ሰኔ ሚካኤል፣ ሰኔና መስከረም ዮሐንስ ይነግሣል
* በጾመ ፍልሰታ የሱባኤ ወቅት ሰዓታት ይቆማል፣ ውዳሴ ማርያምና ቅዳሴ ማርያም ይተረጎማል፣ ቅዳሴ እና የሰርክ ጸሎት ይደርሳል
* በአዲስ ዓመት (በዘመን መለወጫ)፣ በልደት በትንሣኤ እና ቤተ ክርስቲያናችን ባሏት ተጨማሪ ዐበይት በዓላት የተለያዩ መርሐ-ግብሮች ይከናወናሉ።
* በሰሞነ ሕማማት ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ሙሉ አገልግሎት ይሰጣል
ክርስትና
* ቤተ ክርስቲያናችን ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ከጀመረበት ጀምሮ በርካታ ሕፃናት የጥምቀተ ክርስትና አገልግሎት አግኝተዋል።
ስብከተ ወንጌል እና መንፈሳዊ ትምህርት
* ዘወትር አርብ ስብከተ ወንጌል ይሰጣል
* ዘወትር ቅዳሜ መላ ምእመናንን የሚያሳትፍ የሰንበት ትምህርት ቤት መርሐ-ግብር ይደረጋል
* ዘወትር ቅዳሜ የአብነት ትምህርት እና መሠረታዊ የአማርኛ ቋንቋ ለወጣቶችና ለታዳጊ ሕፃናት ይሰጣል
* ዘወትር እሑድ ሃይማኖታዊና የሥነ-ምግባር ትምህርት ለሕፃናት እና ለወጣቶች ይሰጣል
ዕድር
* የቤተ ክርስቲያናችን አባላት የሆኑ ብቻ በአባልነት ተመዝግበው በኀዘናቸው ጊዜ መርጃ እንዲሆናቸው ታስቦ የተቋቋመው ዕድር ለአባላት አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል።
ጤና
* የምእመናን የጤና አገልግሎት ክፍል (FAITH COMMUNITY NURSING PROGRAM, EVERY SUNDAY) ዘወትር እሑድ ለምእመናን አገልግሎት ያቀርባል
ወ/ት ዘመናይ ዘሪሁን
- Written by ወ/ት ዘመናይ ዘሪሁን
Spiritual Assembly in English on:
Friday, March 25: 1pm - 5pm
Saturday, March 26: 12pm - 2:30pm