አገባቦች (Prepositions and Conjunctions)
- Details
- Created on Wednesday, 24 September 2014 00:27
- Written by ማሕበረ ቅዱሳን
መስከረም 14 ቀን 2007 ዓ.ም.
መ/ር ደሴ ቀለብ
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፊሎሎጂ መምህር
1. አቢይ አገባብ፣ አገባቦች ማለት ብቻቸውን ሊነበቡ የማይችሉ መስተዋድዶች ናቸው፡፡ እነዚህም እስመ፣ አምጣነ፣ አኮኑ / Since, because, for/ እመ / ቢሆንም/፣ እስከ፣ እንዘ/ ሲ፣ስ/ አመ/ ጊዜ/ ሶበ/ ጊዜ/
እንተ፣ ዘ፣ እለ /የ/ ወ/እና/ የመሳሰሉት ናቸው፡፡
2.ደቂቅ አገባብ
ውስተ / ውስጥ/፣ ምስለ /ጋር/ ዓዲ /ገና ወይም፣ እንከ / ከንግዲህ/
3. ንዑስ አገባብ፣ እም /ን/፣ በ፣ ለ፣ ን
ግስ ላይ የሚያርፍ አገባቦች / ተስማሚ ቃላት/
ሀ. ከቀዳማይና ከካልአይ አንቀጽ ላይ ብቻ የሚያርፉ አገባቦች
ምሳሌ:- ሶበ፣ አመ፣ ጊዜ
ሶበ፣ ሰዓተ፣ ዕለት --- ጊዜ
እምጣነ፣ አኮኑ፣ እስመ --- እና፣ ስለ
እንዘ
እመ
ዘ፣ እንተ
አምሳለ
ህየንተ
አርአያ
መጠነ
ከመ
ኀበ፣ መንግለ
ሶበ ተሰቅለ ክርስቶስ ጸልመ ፀሐይ --- ክርስቶስ በተሰቀለ ጊዜ ፀሐይ ጨለመ፡፡
ዛቲ ብእሲት እንተ ወለደት ወልደ እኅትየ ይእቲ
/ያቺ ወንድ ልጅ የወለደች ሴት እህቴ ናት/
አበው እለ መሀሩ ሃይማኖተ ቅዱሳን ውእቶሙ
ተነበዩ ነቢያት ከመ ይትወለድ ክርስቶስ -- ነቢያት ክርስቶስ እንዲወለድ ትንቢት ተናገሩ
አመ ይመጽእ ክርስቶስ በግርማ መንግስቱ ትርዕድ ምድር
ህየንተ ክብረ ጴጥሮስ ከብረ ጳውሎስ
ርእዩ መጠነ ገብረ ላቲ ተአምረ
ውእቱ ይስሐቅ እንዘ ትበኪ እህቱ
ያነግህ እንዘ ኢይነውም
እፎ ታነብብ እንዘ ኢትሜሀር
እፎኑ ይከውን ሊተ ዝንቱ እንዘ ኢየአምር ብእሴ
ኖመ ወልድየ አምጣነ ደክመ
ሰብሐ አቡየ ፈጥሪሁ አኮኑ ሰምዐ ጸሎቶ
ጸልመ ፀሐይ ሶበ ክርስቶስ ተሰቅለ
ጸልመ ፀሐይ አመ ክርስቶስ ተሰቅለ
ይትፌስሑ ጻድቃን አመ ክርስቶስ ይመጽእ
ተሐዝን እም አመ ወልዳ ይመውት
ዛቲ ብእሲት እንተ ወለደት ወልደ እኅትየ ይእቲ
አበው እለ ሃይማኖተ መሀሩ ቅዱሳን ውእቶሙ
አበው እለ በሌሊት ይተግሁ ይነውሙ በመዓልት
ርኢኩ ብእሴ እንዘ በጾም ይበልዕ
ከዘንድ አንቀጽ ላይ የሚያርፍ አገባቦች እና ሌሎችም ከነዝርዝራቸው
ምሳሌ:-
ከመ --- እንደ፣ ል፣ ዘንድ/ ከዘንድ አንቀጽ ጋር/
እምቅድመ / አፍራሽ/ ሳ/ ሳይመጣ፣ ሳይሄድ፣. . . /
እንበለ / አፍራሽ/ ሳ/ ሳይመጣ፣ ሳይሄድ
ሖረ ኀበ አሕዛብ ከመይንግር ምሕረቶ ለእግዚአብሔር አምላክነ
-
የእግዚአብሔርን ምሕረት እንዲነግር
-
የእግዚአብሔርን ምሕረት ሊነግር
-
የእግዚአብሔርን ምሕረት ይነግር ዘንድ
ጸልዩ ኀቤሁ ከመትረክቡ ዘትፈቅዱ
መኑ ውእቱ እግዚእ ከመ ንእመን ቦቱ
እምቅድመ ይትወለድ አብረሃም ሀሎኩ አነ
ነበረት ዘመናተ ብዙኃተ እንበለ ኢታእምር ረኀበ
አገባቦችን በመዘርዘር መጠቀም ይቻላል
-
እም-- ከ፣ እመኔየ---ከኔ፣እምኔክሙ------ከእናንተ፣ እምኔሆሙ------ከእነሱ
-
ምሥለ --- ጋር፣ ምስሌየ----ከኔ ጋር ፣ ምስሌክሙ----ከእናንተ ጋር፣ ምሥሌሆሙ------ ከነሡ ጋር
-
በእንተ-- ስለ፣ በእንቲአየ----ስለእኔ፣ በእንቲአክሙ----ስለናንተ፣ በእንቲአሆሙ--- ስለእነሱ
-
ህየንተ --- ፈንታ / ስለ/፣ ህየንቴየ / ስለኔ ፈንታ/፣ ህየንቴክሙ / ስለ እናንተ/፣ ህየንቴሆሙ / ስለእነሱ/
የሌሎች ተስማሚ ቃላት ትርጉማቸው
ወ --- እና
ወ --- ከግሡ ጋር የሚገባበት ጊዜ አለው፡፡ምሳሌ ወሖረ፤ነገር ግን ግሡን ይለውጠዋል ማለት አይደለም፡፡
ወ --- ም
ወ --- በሁለት ግሦች መሃል ሲገባ የነገሩን አወንታዊነት ይጠብቃል ወይም ያጎለብታል፡፡
ምሳሌ፡ ተሰብአ ወተሠገወ / ተሠብአ ማለት ሰው ሆነ/
/ ተሠገወ ማለት ሰው ሆነ/
ሂ --- ም/ አና
ኒ --- ትራስ ማለት የንባቡን ቃና ላለማበላሸት ምሳሌ ውእቱኒ
ኬ -- ውእቱኬ
ነገር ግን እንደ “ ም” ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
አይ፣ ምንት፣ ሚ፣ ኦ -- በምን ብሂል --- ማለት
ምንታት / አያት/ --- ምኖች በ --- በ
አይ --- ማናቸው ለ -- ን ፣የ
አያት --- ማናቸው መ፣ ሂ፣ ኒ -- ም
አይቴ --- ወዴት ዮም ---- ዛሬ
ማእዜ --- መቼ ወትረ/ ዘልፈ/ -- ሁል ጊዜ
እፎ --- እንዴት ዝየ --- በዚህ፣ በዚያ
በእፎ ---- ለምን ህየ --- በዚህ፣ በዚያ
አሌ፣ አ፣ ወይ -- ወየ ናሁ፣ ነዋ-- እነሆ
ባሕቱ -- ነገር ግን
ነየ -- እነሆኝ
እመ፣ አመ--- ወይም እስኩ -- እስኪ እንጋ / እንዳኢ/ -- እንጃ
ዕንቋዕ፣ ጥቀ --- ስንኳ አመ፣ ጊዜ አሜን፣ አሜን -- አሜን
ሰ፣ ሳ፣ ስ --- ማ ነዓ --- ና
ንስቲት፣ሕዳጥ፣ሕቀ ---ትንሽ ሀብ፣ ህንባ -- እንካ
ጥቀ --- እጅግ አንቢ ---- እምቢ
ፅሚተ --- ቀስ ብሎ አንቋዕ --- እሰይ፣ አበጀ
ቅድም --- ፊት ኩሉ --- ሁሉ
እንዘ ---- እየ፣ ሰ፣ ሳ፣ ስ እመ -- ለ፣ ባ፣ ብ
ዳዕሙ----አላ፣ እንበለ --- ያለ፣ ሳይቀር
ባሕቱ -- እንጂ፣ ነገር ግን
ዘ፣ እንተ፣ እለ፣ ለ የተባሉት እነዚህ አገባቦች ዘርፍ አያያዥ ይባላሉ፡፡ ከ “ ለ” ውጭ ያሉት ሦስቱ ዘርፍ ደፊ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ የዘርፍ ደፊም ሆነ የዘርፍ አያያዥ ዓላማ “ የ” የሚል ትርጉምን ለማምጣት ነው፡፡
ምሳሌ፡-
በ “ ለ” ሲገኝ በ “ ዘ” ሲገኝ በተናባቢ ሲገኝ ወልዳ ለማርያም ወልድ ዘማርያም ወልደ ማርያም (የማርያም ልጅ)
- በተናባቢ ጊዜ የተናባቢው መሪ የሚሆነው ቃል መድረሻው ሳድስ እንደሆነ / ወልድ/ ሳድሱ ወደ ግእዝ ይለወጣል፡፡ ይህ ሕግ ከተሳቢ ህግ የለየው ተሳቢው የሚጎላ ድምፅ ሲኖረው የተናባቢው መሪ የሚነሳ ድምፅ የሌለው በመሆኑ ነው፡፡ የተናባቢው መሪና ዘርፍ እንደ አንድ ቃል አብረው መነበብ አለባቸው በተናባቢ ጊዜ ዘርፍ ምንም ለውጥ አይደርስበትም፡፡
-
አብረሃም ብእሴ እግዚአብሔር ውእቱ መኑ ውእቱ ጸሐፌ ትእዛዝ ዘንጉሥ
-
ሕግ - በተናባቢ ጊዜ የተናባቢው መሪ የሚሆነው ቃል መድረሻው ሣልስ እንደሆነ / ብእሲ፣ጸሐፊ፣ ወራሲ፣ ቀታሊ፣ ሰባኪ ወዘተ/
-
ሕግ - ሌሎች ቃላት የተናባቢ መሪ ሲሆኑ ምንም ዓይነት ለውጥ አይደርስባቸውም፡፡
አናባቢ
ደብተራ ዘኦሪት ደብተራ ኦሪት
ሠረገላ ዘኤልያስ ሠረገላ ኤልያስ
ዝማሬ ዘመላእክት ዝማሬ መላእክት
ውዳሴ ዘማርያም ውዳሴ ማርያም
ዶርሆ ዘመስተገብር ዶርሆ መስተገብር
ከበሮ ዘማኅሌት ከበሮ ማኅሌት
Read more http://www.eotcmk.org/site/--mainmenu-56/1565--prepositions-and-conjunctions