የአቡነ ጎርጎሪዎስ ካልዕ ምኞት በነቅዓ ጥበብ አቡነ ጎርጎሪዎስ ትምህርት ቤት እየተተገበረ ነው፡፡

የአቡነ ጎርጎሪዎስ ካልዕ ምኞት በነቅዓ ጥበብ አቡነ ጎርጎሪዎስ ትምህርት ቤት እየተተገበረ ነው፡፡ አትም ኢሜይል

መ/ር ሳሙኤል ተስፋዬ

ታኅሣሥ 25 ቀን 2007 ዓ.ም.

አቡነ ጎርጎሪዎስ ካልዕ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሐዋርያዊ አገልግሎት ከፍተኛ ጥረት ያደርጉ ነበር፡፡ ምኞታቸውና ጥረታቸው ከነበረው አንዱ ህጻናት ቤተክርስቲያናቸውን ቀርበውና አውቀው እንዲያገለግሏት ማድረግ ነበር፡፡img 19201

ሚያዚያ 23 ቀን 1983 ዓ.ም ሻሸመኔ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ተገኝተው እንዲህ ብለው ነበር፡፡ “ቤተክርስቲያን ስትመጡ ልጆቻችሁን ይዛችሁ ኑ ያስቀድሱ ዕጣኑ ይሽተታቸው፡፡ ሥጋ ወደሙን እየተቀበሉ ይደጉ፡፡…”

 

ይህ ምኞታቸው በየጊዜው እየተተገበረ ከሀያ ዓመታት በላይ ቀጥሎ በዛሬው እለት በነቅዓ ጥበብ አቡነ ጎርጎሪዎስ ትምህርት ቤት በመምህራኑና በቤቴል ቅዱስ ሚካኤል ካህናት አማካኝነት ህጻናቱ በሙሉ አስቀድሰው ሊቆርቡ ችለዋል፡፡ ወላጆቻቸውም ለልጆቻቸው ሲሉ ሊያስቀድሱና ሊቆርቡ ችለዋል፡፡

img 19301

 

የአቡነ ጎርጎሪዎስ ትምህርት ቤትን ያብዛልን፡፡ ህጻናቱን በስርዓት ያሳድጋልናልና፡፡

 

 

Read more http://www.eotcmk.org/site/-mainmenu-18/1672-2015-01-03-13-10-28