1ዐ.4 ቦ / አለ/ በመራሕያን ሲረባ/ Verb to have/
- Details
- Created on Friday, 02 January 2015 04:08
- Written by ቀዳሚ ገጽ
ግእዝን ይማሩ
ታኅሣሥ 24 ቀን 2007 ዓ.
1ዐ.4 ቦ / አለ/ በመራሕያን ሲረባ/ Verb to have/
ብየ= አለኝ ምሳሌ ምንት ብየ ምስሌኪ ካንቺ ጋር ምን አለኝ
ብከ= አለህ ምንት ብከ ምስሌሃ ከርሷ ጋር ምን አለህ
ብኪ = አለሽ ምንት ብኪ ምስሌሃ ከርሷ ጋር ምን አለሽ
ብነ = አለን ምንት ብነ ምስሌክሙ ከእናንተ ጋር ምን አለን
ብክሙ=አላችሁ ምንት ብክሙ ምስሌሆሙ ከእነርሱ/ ከወንዶች/
ጋር ምን አላችሁ
ብክን= አላችሁ / ለሴት/ ምንት ብክን ምስሌየ ከእኔ ጋር ምን አላቸው
ቦሙ= አላቸው ምንት ቦሙ ምስሌየ ከእኔ ጋር ምን አላቸው
ቦን = አላቸው / ለሴት/ ምንት ቦን ምስሌኪ ከአንቺ ጋር ምን አላቸው
ከላይ ለጠቀስናቸው አፍራሻቸው አል ነው፡፡
ለምሳሌ:-
አልብየ = የለኝም
አልብከ = የለህም
አልብኪ = የለሽም
አልብነ = የለንም
አልቦ = የለንም፣ የሉም፣ የለም
ቦ = አለ ፣አለው
ዘቦ = ያለው
1ዐ.5 ባለቤት ተውላጠ ስም (Subjective Pronoun)
እግዚአብሔር ለሊሁ ፈጠረ ዓለመ / እግዚአብሔር እርሱ ራሱ ዓለምን ፈጠረ/
ለሊሁ የአምር
ለሊከ እግዚኦ ተአምር እበድየ
ለሊከ እግዚኦ ተአምር ጽእለትየ
ለሊከሰ ሕይወተ ታሐዩ
ለሊኪ አውሰብኪ
ለሊሃ ትበልዕ ኩሎ ዘትረክብ
ትአምሩ ለሊክሙ ኩሎ ነገረ ዘኮነ በይሁዳ
ለሊሁሰ እግዚእ ኢየሱስ ኢያጥመቀ ዳእሙ አርዳኢሁ/ ዳእሙ -- እንጂ/
ነጠላ ብዙ
ለሊሁ = እርሱ እራሱ / Himself/ ለሊሆሙ = እነርሱ እራሳቸው
(Themselves)
ለሊሃ = እርሷ እራሷ (Herself) ለሊሆን = እነርሱ / ለሴቶች/
(Themselves)
ለሊከ = አንተ እራስህ (Yourself) ለሊክሙ = እናንተ እራሳችሁ
( Yourselves)
ለሊኪ = አንቺ እራስሽ (Yourself) ለሊክን = እናንተ እራሳችሁ /ለሴቶች/
( Yourselves)
ለሊየ /ለልየ = እኔ እራሴ/ ( My self) ለሊነ = እኛ እራሳችን
( 0urselves)
1ዐ.6 ተሳቢ ተውላጠ ስሞች ( Objective Pronouns)
ነጠላ ብዙ
ኪያየ = እኔን ( Me) ኪያነ = እኛን (Us)
ኪያከ = አንተን ( You) ኪያክሙ = እናንተን (You)
ኪያኪ = አንቺን ( You) ኪያክን = እናንተን ( You) ለሴቶች
ኪያሁ = እሱን ( Him) ኪያሆሙ = እነርሱን ( Them)
ኪያሃ = እሷን ( Her) ኪያሆን = እነርሱን ( Them ለሴቶች/
ምሳሌ
ዘርእየ ኪያየ ርእየ አቡየ
መኑ ይጼውእ ኪያከ
ኪያኪ ሰናይተ ዘፈጠረ እግዚአብሔር ይትባረክ
ቀድሱ ኪያሁ ወባርኩ ስሞ
አምላክነ አድኀነ ኪያነ እሞት
ዘተወክፈ ኪያክሙ ተወክፈ ኪያየ
ፈኑ ኪያሆሙ ኀበ አሕዛብ
ርእየ ኪያክን ወተፈስሐ ብክን
® ስለዚህ ተሳቢ ማለት “ን” የሚለውን ቃል ወይም ፊደል
የሚያመጣ ማለት ነው፡፡
የሚያበዙ ፊደላት
አ፡-
ነጠላ ብዙ የብዙ ብዙ
ደብር አድባር አድባራት
ርእስ አርእስት
ከዚህ ላይ የቃላቱን መጨረሻ ሁለት ፊደላት ማስተዋል ነው፡፡
ብር፣ እስ / ሳድስ ናቸው፡፡/
ን፡- ሀ. ደራሲ + ያን = ደራስያን
ሠዓሊ + ያን = ሠዓልያን
ለ. ኢትዮጵያዊ +ያን = ኢትዮጵያውያን
ሐ. ቅዱስ = ቅዱሳን
ብፁዕ = ብፁዓን
መዘምር = መዘምራን
ከዚህ ላይ የቃላቱ የመጨረሻው ሁለት ፊደላት ራብዕና ሣልስ ናቸው፡፡
ራሲ፣ ዓሊ፣ እንደገና የመጨረሻዎቹ ሁለት ፊደላት ፁዕና ዱስ ይላል፡፡
ት፡- ኢትዮጵያዊት+ ያት - ኢትዮጵያውያት
ሰማይ = ሰማያት
ቅድስት = ቅዱሳት
ሠናይት = ሠናያት
v አሁንም ቢሆን የቃላቱን ሁኔታ ማስተዋል ነው፡፡
መ፡- ኩሉ -- ኩሎሙ ለሊሁ -- ለሊሆሙ
አንተ --አንትሙ ለሊከ --ለሊክሙ
እ፡- ኃጢአት -- ኃጣውእ
ይ፡- መርዔት= መራዕይ ል፡- ኪሩብ = ኪሩቤል
ሌሊት = ለያልይ ሱራፊ = ሱራፌል
ው፡- ዕፅ = ዕፀው
አብ = አበው
እድ = እደው
የጸያፍ አበዛዝ ምሳሌ
መምህራን፡ መምህራኖች
ደራሲያን ፡ ደራስያኖች
ቅዱሳን ፡ ቅዱሳኖች
ማስታወሻ፡- የጸያፍ አበዛዝ ማለት ፈጽሞ
ግእዝም አማርኛም ያልሆነና ከሕግ
ውጭ የሆነ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ
ከላይ የተጠቀሱት ቃላት
አላዋቂነት ካልሆነ በቀር ፈጽሞ
አይባሉም፡፡
Read more http://www.eotcmk.org/site/--mainmenu-56/1671-14-verb-to-have