የማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ሥርጭት በሰሜን አሜሪካ ግዛቶች እያደገ መሆኑ ተገለጸ

የማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ሥርጭት በሰሜን አሜሪካ ግዛቶች እያደገ መሆኑ ተገለጸ አትም ኢሜይል

የካቲት 19 ቀን 2007 ዓ.ም.

በመ/ር ሳሙኤል ተስፋዬ

001 mk logo በኢቢኤስ /EBS/ በመሠራጨት ላይ የሚገኘው የማኅበረ ቅዱሳን የቴሌቪዥን መርሐ ግብር በሰሜን አሜሪካ በሚገኙ ሦስት ግዛቶች በቦስተን፤ በካምብሪጅ እና ሲያትል ይተላለፍ የነበረውን ሥርጭት በማሳደግ አራተኛውንና አምስተኛውን ሥርጭት በመንትያ ከተሞች /twin cites/ በሚናፖሊስ እና ሴንት ፖል ግዛቶች የካቲት 15 ቀን 2007 ዓ.ም. ሥርጭት መጀመሩን የማኅበሩ የኅትመትና ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ ዋና ክፍል ሓላፊ ዲያቆን ዶክተር መርሻ አለኸኝ ገለጹ፡፡

 

እንደ ዲያቆን ዶክተር መርሻ ገለጻ ዋና ክፍሉ ለአሜሪካ ማእከል በሰጠው አቅጣጫ መሠረት ከቤተ ክርስቲያን መዋቅር ጋር በመቀናጀት ሥርጭቱ በሁሉም ግዛቶች እንዲያድግና ተግባራዊ እንዲሆን የማእከሉ አባላት አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው፤ ዝግጅቶቹን ለማሰራጨት የግዛቶቹ ባለሥልጣናት ስቱዲዮ በመስጠት ድጋፍ እያደረጉ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡


በአሁኑ ወቅት በኢቢኤስ የሚተላለፈው የማኅበሩ የቴሌቪዥን ሥርጭት ከአንድ ሰዓት በላይ ለማሳደግ ጥረት እየተደረገ ሲሆን፤ ከዚህ በተጨማሪም የኢንተርኔት ቴሌቪዥን መርሐ ግብር ለመጀመር ዝግጅቱ እየተጠናቀቀ እንደሚገኙም ዲያቆን ዶክተር መርሻ ገልጸዋል::

 

 

 

 

Read more http://www.eotcmk.org/site/-mainmenu-18/1743-2015-02-26-09-15-35