አምልኮተ ሰይጣን - ፍጻሜ “ተሐድሶ”?

አምልኮተ ሰይጣን - ፍጻሜ “ተሐድሶ”? አትም አምልኮተ ሰይጣን - ፍጻሜ “ተሐድሶ”?

ባለፉት ተከታታይ ዕትሞች ስለ ተሐድሶ መናፍቃን እንቅስቃሴ አጠቃላይ ሁኔታ እና የትኩረት አቅጣጫዎች እንዳ ቀረብንላችሁ ይታወቃል፡፡ በዚህ ዕትም ደግሞ የተሐድሶ መናፍቃን ግብ ምን እንደሆነ እናስነብባችኋለን፤ መልካም ንባብ ይሁንላችሁ፡፡
እሱባለው በለጠ የተባሉ ጸሐፊ "የገሃነም ደጆች ፕሮቴስታንታዊ ጅሃድ በኢትዮጵያዊነት - ተዋሕዶነት ላይ ሲፋ ፋም" በሚለው መጽሐፋቸው አውሮፓ ውያን፣ የካቶሊክና የፕሮቴስታንት እንዲሁም የተሐድሶ መናፍቃን የኢት ዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስ ቲያንን ለማጥቃት የፈለጉበትን ምክን ያት ሲገልጡ "ፈረንጆች ሃይማኖታ ችንን ከገደሉ፣ ቅድስት ኢትዮጵያን በባርነት ለመያዝ ቀላል መሆኑን ስለ ሚያውቁ ነው ቤተ ክርስቲያንን የጥ ቃት ዒላማቸው ያደረጓት" (ገጽ ፳፯) ብለዋል፡፡ በተጨማሪም "ሁሉም ወራሪ ዎች ከግራ ይምጡ ከቀኝ፣ በነጮችም ይፈጸሙ በዐረብ/ቱርክ፣ ወረራው በጦር ይሁን ወይም በሐሳብ፣ ሁሉም ወራሪዎች የጥቃታቸው ዋና ዒላማ የሚያደርጓት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ነው፡፡ ግን ሁሉም ወራሪዎች ድል የተደረጉት የአንድነትና የነጻነት ምንጭ በሆነችው በዚች መከረኛ ቤተ ክርስቲያን ነው" (ገጽ ፳፫-፳፬) በማለት ጽፈዋል፡፡


ጸሓፊው ባለፉት አምስት መቶ ዓመታት በኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ላይ የተቃጡት የውጪ ወረራዎች፣ በነጮች አማካኝነት የተቀሰቀሱ የእርስ በእርስ ጦርነቶች፣ የካቶሊክ ሚሲዮና ውያን ቅሰጣ፣ ኮሚኒስታዊ ርእዮተ ዓለምና ፕሮቴስታንታዊ ዘመቻዎች ሁሉ አንድ ዓይነት እና ጸረ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አቋም ያላቸው ናቸው፡፡ ሁሉም የቅድስት ኢትዮጵያ ተዋሕዶ ሃይማኖትን "በደንቆሮነት"፣ "በጸረ ሕዝብነት"፣ በኋላ ቀርነት"፣ "በጣ ዖት አምላኪነት"፣ በ"ኦሪታዊነት"፣ አሁን አሁንማ የልብ ልብ አግኝተዋልና በይፋ በየቤተ አምልኮውና ማለቂያ በሌላቸው ዕለታዊ፣ ሳምንታዊ፣ â€Â¦ ልሳኖቻቸው "በሰይጣንነት" ይከሷታል ይላሉ (ገጽ ፳፬)፡፡
ምዕራባውያን በኢትዮጵያ ላይ ሊያ ሳኩት የፈለጉትን ግባቸውን ሲናገሩ ደግሞ እንዲህ ብለዋል፡፡ "በእምነታቸው ፍርድ ቤትም የሚጠይቁት አንድ ነገር ነው - የቅድስት ኢትዮጵያ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን የስቅላት ሞት፡፡ ይህም ተፈርዶላቸው፣ የመስቀያ ገመዱን አዘ ጋጅተው፣ የመስቀያ ቦታውን መር ጠው፣ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን እግር ተወርች አስረው ዐይኖችዋን ሸፍ ነው፣ ከእስር ቤት አውጥተው ወደ መስ ቀያ ቦታ እየነዷት ይገኛሉ፡፡ በዚህ የቅድ ስት ኢትዮጵያ ተዋሕዶ ሃይማኖት ወደ ሞት መነዳት፣ አጃቢ ወታደር በመሆን ብዙ መቶ ሺ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ አስፈጻሚ፣ ካድሬ፣ ጽንፈኛ፣ ጅሀደኛ፣ ፕሮፖጋንዲስት በመሆን እርማቸውን ለመብላት እየተቅበዘበዙ ነው፡፡ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ የፕሮቴስታንት ርእዮተ ዓለም ሰለባ ኢትዮጵያውያን ጀሌዎችም â€Â¦ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስ ቲያንን ተዝካር ለመብላት ከወዲሁ እየጓጉ ነው" (ገጽ ፳፬-፳፭) በማለት አስቀምጠዋል፡፡
የካቶሊክና የፕሮቴስታንት ሚሲዮ ናውያን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ለማፍረስ በየዘመናቱ ብዙ ደክመዋል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ አስይ ዘው ወንጌል እንስበክላችሁ ያሉበት ጊዜ ነበር፡፡ በኀይል ለመደምሰስ መትረየስና ታንክ ባርከው የላኩበትም ጊዜ ነበር፡፡ በዘመናዊ ሥልጣኔ ወደ ፊት እናራምዳ ችሁ ብለው መጥተው በመርዝ ጋዝ እንድናልቅ ያደረጉበት ጊዜ ነበር፡፡ የሞ ከሩት ሁሉ አላዋጣ ብሏቸው ሌላ ዘዴ ሲፈልጉ የፕሮቴስታንት ድርጅቶችን ተገን አድርገው በመግባት ለሆዳቸው ያደሩ "መሪጌታ፣ መነኩሴ፣ ዲያቆን፣ ወዘተ" ነን ባዮችን መጠቀም ቤተ ክር ስቲያንን ለማፍረስ እንደሚጠቅማቸው ተረዱት፡፡ ስለዚህ የተሐድሶ መናፍቃን እንቅስቃሴ በጦርና በሰይፍ ለማሳካት ያልተቻለውን የምዕራባውያንን ምኞት "በኢትዮጵያዊ ፈረንጆች" ለማሳካት ታልሞ የተነደፈ እንቅስቃሴ ነው፡፡ የመ ጨረሻ ዓላማው ምዕራባውያን የራሳቸ ውን አብያተ ክርስቲያናት" ጭፈራ ቤት እንዳደረጓቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ወደ ጭፈራ አዳራሽነት መቀየር፣ ምእመናንን ደግሞ ፍጹም ዓለማውያን (ሴኩላር) በማድረግ ለግብረ ሰዶማዊነትና ለአምልኮተ ሰይ ጣን ማዘጋጀት ነው፡፡ የተሐድሶ እንቅስቃ ሴው ግብ አንድና ብቸኛ ሳይሆን ዘርፈ ብዙ ነው፡፡ ከእግዚአብሔር መንግሥት በመለየት የሰይጣን ተገዢዎች በሚያ ደርጉ አስነዋሪ ድርጊቶች ውስጥ ማስገ ባት ነው፡፡ ክርስቶስን እንሰብካለን ብለው የተነሡት ፕሮቴስታንቶች፣ ሚሲዮኖቻ ቸውን እየላኩ እኛን "ወንጌል እናስተ ምራችሁ" የሚሉን የተሐድሶ መናፍቃን የጥፋት አባቶች እየደረሱባቸው ያሉትን እና ሊደርሱባቸው የሚፈልጓቸውን ግቦች እንመልከት፡፡
፩. ዓለማዊነት (Secularism)፡- የተሐድሶ መናፍቃን እንቅስቃሴ የመጨ ረሻ ግብ "ክርስትና በልብ ነው" በሚል ፈሊጥ ልባቸው የፈቀደውን ሁሉ ማድ ረግ ነው፡፡ ሃይማኖት የሰው ልጅ አንዱ ማንነቱና ምንነቱ መገለጫ ነው፡፡ ነቢዩ ዮናስ ምንድን ነህ? ሥራህስ ምንድን ነው? ተብሎ ሲጠየቅ "ዕብራዊ ነኝ፤ ሥራዬም ሰማይና ምድርን የፈጠረ እግዚአብሔርን ማምለክ ነው" ብሎ የተናገረው ሃይማኖት የሰው ልጅ ማን ነት መገለጫ መሆኑን ማረጋገጫ ነው፡፡ ሰው ከቀለሙ፣ ከተወለደበት ዘር፣ ከተወለደበት ቦታ በላይ አምኖና ፈልጎ የተቀበለው ሃይማኖት እውነተኛ የማን ነቱ መገለጫ ነው፡፡ የሰው ልጅ ከፈለ ገው እናትና አባት፣ ከፈለገው ቦታ፣ ከፈለገው ዘር፣ የሚፈልገውን ቀለም ይዞ መወለድ አይችልም፡፡ ይህ በፈቃደ እግዚአብሔር የሚከናወን ስለሆነ ከሰው ልጆች ቁጥጥርና ከአቅማቸው በላይ የሆነ አምላካዊ ጥበብ ነው፡፡ ስለዚህ ሰው ስለ ማንነቱ ሲጠየቅ በትክክል የሚያውቀውና የሚያምንበት ማንነቱ ሃይማኖቱ ነው፡፡ የሰው ሰብእ ናም የሚወሰነው ሊገራው፣ ሊያሸንፈ ውና ሊያስተካክለው በሚችለው በውሳ ጣዊ ማንነቱ እንጂ በሥነ ፍጥረት በተለገሰው ውጫዊ ገጹ አይደለም፡፡
ይህን የሚያውቁ ምዕራባውያን ሰው ውስጣዊ ማንነቱን ረስቶ በውጫዊ ነገሮች ማለትም በአለባበሱ፣ በአመጋ ገቡ፣ በአነጋገሩ፣ ወዘተ ላይ ትኩረት እንዲያደርግ በመሥራት ላይ ናቸው፡፡ ሃይማኖት በእኛ በደካሞች እጅ ወድቆ የሆነውን ሳይሆን ዋኖቻችን ኖረው ባሳዩን መሠረት ለዓለም ሙት ሆኖ ለክርስቶስ ሕያው መሆን ነው፡፡ ለመጥፎ ነገር ሞቶ ለመልካም ነገር ሕያው መሆን ነው፡፡ ሰው ሁሉ በእግዚአብሔር ካመነና በእግዚአብሔር ከታመነ (ፍቅረ እግዚአብሔርን እና ፍቅረ ቢጽን ገንዘብ ካደረገ) የእርስ በእርስ ጦርነት፣ ክህ ደት፣ በሌሎች ጉዳት መደሰት፣ ግዴለ ሽነት፣ የሞራል ዝቅጠት፣ ዝሙት፣ ክፋት፣ ወዘተ አይኖርም፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን መብታችንን ለማስከበር ብለን ለምናቋቁማቸው የፍትሕ ተቋማት፣ ራሳችንን ለመከላለክል ብለን ለመሣሪያ መግዣ የምናወጣው ገንዘብ ለበጎ አድራ ጎት ይውል ነበር፡፡ ያደጉ አገራትም የድሀ አገራት ሕዝቦችን ከምድረ ገጽ ለማጥ ፋት የሚያግዙ የበሽታ መፈልፈያ ቤተ ሙከራዎችን ለመገንባት የሚያወጡት ወጪ ለበጎ ዓላማ ቢውል ስንት ድሆ ችን መመገብ በቻለ ነበር፡፡
የምዕራባውያን "ቸርቾች" ከላይ የጠቀስናቸው ችግሮች እንዲፈጠሩና እንዲባባሱ ታላቅ አስተዋጽኦ አድርገ ዋል፡፡ ሰው በጋራ የሚያምነው እውነት እንዳይኖር "ክርስቶስን በገባህ መልኩ ግለጠው/ አምልከው" እየተባለ ግለኝነት የተስፋፋው በፕሮቴስታንት ቸርቾች ነው፡፡ ቸርቾቻቸው የአምልኮ ቦታነታ ቸው ቀርቶ ቡና ቤት፣ ፊልም ቤት፣ ጭፈራ ቤት፣ ሙዚየም፣ የገበያ አዳራሽ ሆነዋል፡፡ ክርስቶስን እንደ ግል አዳኝ አድርጎ በመቀበል ፈሊጥ የተጀመረው እምነት ቤተ ክርስቲያን ባለመሔድና እግዚአብሔር የለም በሚል ፍልስፍና ተደመደመ፡፡ ዛሬ ላይ የካቶሊክም ሆኑ "ካቶሊክ ኢየሱስን ጥላለች" ብሎ ሉተር የመሠረተው የፕሮቴስታንት እምነት ቸርቾች ወደ ፍጹም ዓለማዊነት (Secularism) "አድገዋል"፡፡ ፕሮቴስታን ቲዝም ከእምነት ደረጃ ወጥቶ ወደ ፖለቲካ ርእዮተ ዓለምነት ተሸጋግ ሯል፡፡
ጥናቶች እንደሚያመለክቱት የካቶ ሊክና ፕሮቴስታንት እምነት ተስፋፍ ቶባቸው የነበሩ አገራት ዛሬ ላይ እግዚ አብሔር የለም የሚል ፍልስፍና የሚከ ተሉ ሆነዋል፡፡ ለምሳሌ፡- የራሷን ሕዝብ ኢ-አማኒ አድርጋ አሁንም ድረስ በተለ ያዩ የልማት ፕሮጀክቶች ስም ወደ ድሀ አገራት በመግባት (በተለይም አፍሪካውያንን) ፕሮቴስታንት በማድረግ የምትታወቀው ስዊድን ከሕዝቧ ቁጥር ፴፬ በመቶ የሚሆነው እግዚአብሔር የለም የሚል ነው፡፡ ፴፱ በመቶው ስለ እምነት ግድ የሌለው ነው፡፡ በፈረንሳይም እንዲሁ ፵ በመቶ የሚሆነው ሕዝብ የእግዚአብሔርን ህልውና የማይቀበል ነው፡፡ በስመ ክርስትና የሚኖሩትም ወደ ቤተ እምነታቸው አይሔዱም፡፡ ለምሳሌ፡- በታላቋ ብሪታንያ ክርስቲያን ነኝ ብሎ የሚያምነው ሕዝብ ፸፪ በመቶ ሲሆን "ቤተ ክርስቲያን" የሚሔደው ሕዝብ ግን 1.4 በመቶ ብቻ ነው፡፡ የሉተር "ሃይማኖት" በተፈጠረባት አገር በጀር መን ፸፪ በመቶ በተመሳሳይ ሁኔታ ክርስቲያን ነኝ ብሎ የሚያምን ሲሆን "ቤተ ክርስቲያን" የሚሔደው ግን 1.2 በመቶ ብቻ ነው፡፡
ዓለሙ በአሁኑ ሰዓት በዘመናዊ ነት ስም ግለኝነትን እያበረታታና ተደ ጋግፎና ተባብሮ የመኖርን መልካም እሴት እያጠፋ ነው፡፡ የሦስተኛው ዓለም አገራት በምግብ፣ በንጹሕ ውኃ አቅ ርቦት፣ በመጠለያ አቅርቦት፣ በመጀመ ሪያ ደረጃ የትምህርት አገልግሎት፣ በጤና አገልግሎት፣ በአጠቃላይ ለመ ኖር በመሠረታዊነት የሚያስፈልጉ ነገሮችን ማሟላት አቅቷቸው በሺ ዎች የሚቆጠሩ ነፍሳት በየቀኑ ይሞ ታሉ፡፡ ያደጉ አገራት ደግሞ እነዚ ህን መሠረታዊ የሥጋ ፍላጎቶች ለማ ሟላት ከሚያስፈልገው ወጪ በዐሥር እጥፍ የሚበልጥ ገንዘብ ለኮስሞቲክ ስና ለውሻ ምግብ ያወጣሉ፡፡ ዓለም አንዱን በቁንጣን ሌላውን በጠኔ መግደል ጠባይዋ መሆኑን ከዚህ ተግባር መረ ዳት ይቻላል፡፡
የሚቀነቀኑ ርእዮተ ዓለሞች (ፌሚ ኒዝም፣ ሊበራሊዝም፣ ሴኪዩላር ሂውማ ኒዝም፣ ወዘተ) እና የሚቀረፁ ሥር ዓተ ትምህርቶች መንፈሳዊነትና ሥነ ምግባራዊ እሴት እንዳይኖራቸው እየ ተደረጉ ነው፡፡ ለምሳሌ፡- በአገራችን እግዚአብሔር የለም የሚል ርእዮተ ዓለም ነግሦ በነበረበት ጊዜ "ሳይማር ያስተማረንን ሕዝብ ማገልገል አለብን" የሚል አስተሳሰብ ነበር፡፡ ይህም የአብ ነት ትምህርቱን እንደ ትምህርት ላለ መቁጠር የምዕራቡን ትምህርት ባጠኑ ልሒቃን መነገር የጀመረ አስተሳሰብ ነበር፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሕፃናት የሚዘጋጁ የመዝናኛ ቁሳቁሶች፣ ለሴቶች የሚዘጋጁ አልባሳት፣ ለሕ ዝብ ዐይን የሚደርሱ ፊልሞችና ማስ ታወቂያዎች፣ ወዘተ በአጠቃላይ መል ካም ሥነ ምግባርን የሚያስረሱ ናቸው፡፡ እነዚህ ሁሉ ድርጊቶች እስካሁን ድረስ በተወሰኑ ቡድኖች አነሣሽነት የሚቀነቀኑ ነበሩ፡፡ አሁን ግን "ሃይማኖታዊ መልክ" እየተሰጣቸው በእምነት ድርጅቶች በዓላማ እየተከናወኑ ነው፡፡ ለምሳሌ፡- ተሐድሶ መናፍቃን የኢትዮጵያ ኦርቶዶ ክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ለማቃ ለልና አስተምህሮዋን ለመንቀፍ ሲፈ ልጉ፡-
ከወንጌል ተልእኮ አንጻር ፋይዳ ያላቸው ባይሆኑም በርካታ የሥነ ጽሑፍ ውጤቶች በኢትዮጵያ ኦርቶዶ ክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተከማችተው ይገኛሉ፡፡ የብዙዎች ዐይን ያላያቸውና ተነበው ያላለቁ ድርሳና ቶቿም ብዙ ናቸው፡፡ ከግዝፈታቸው የተነሣ ለዐራት ተይዘው የሚከፈቱ የአንድ ሰው ትክሻ ስለማይችላቸው በአህያ የሚጫኑ መጻሕፍቶች አሉ፡፡ አሳዛኙ ነገር ግን ከእነዚህ ሁሉ መጻ ሕፍት ዘጠና በመቶ የሚሆኑቱ ክር ስቶስ ኢየሱስን በማመንና በማወቅ ወደሚገኝ የመረዳት ነጻነት የሚያደ ርሱ አይደሉም፡፡ (ከሣቴ ብርሃን ጋዜጣ መጋቢት ፳፻ወ፮ ዓ.ም) በማለት ይጽ ፋሉ፡፡
ይህ አሳብ ቤተ ክርስቲያንን በኢየ ሱስ ክርስቶስ የማታምን አድርጎ ከማቅረብ ያለፈ በምዕራባውያን እየተቀነ ቀነ ያለውን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲ ያንን በጎ እሴት፣ መልካም ሥነ ምግባ ርና ሰብአዊነት ለመናድ ምሰሶዋን ለመነቅነቅ ታልሞ የተጻፈ ነው፡፡ መጻ ሕፍቱ ጥቅም ስለሌላቸው አታንብቧ ቸው የሚል መልእክት ማስተላለፍ፣ ምግባር ትሩፋት አያስፈልግም ብሎ መስበክ ሳያስፈልግ ሰዎች በተለያዩ ሱሶች (ፊልም፣ ሙዚቃ፣ እግር ኳስ፣ ጫት፣ ወዘተ) ተጠምደው ከሥራ ውጪ እዲሆኑ ማድረግ ይቻላል የሚል ዓላማ ይዘው ለተነሡ አካላት ድጋፍ መስጠት ነው፡፡ ይህ ደግሞ በቀጥታ ዓለማዊነ ትን ማበረታታት ነው፡፡
፪. ሥርዓት አልበኝነት፡- ዓለምን ሁሉ ለዓለማዊነት እያዘጋጁ ያሉት ምዕራባውያን በመጀመሪያ ደረጃ የሚ ሠሩት ሥራ ለዶግማ፣ ለሥርዓት፣ ለቀኖና፣ ለትውፊትና ለታሪክ ትኩረት በመስጠት ትውልድን የሚያገለግለውንና የሚያስተካክለውን ሃይማኖት ማጥ ፋት ነው፡፡ በዚህ ምክንያት የተሐድሶ መናፍቃን ሰይፍ ያነጣጠረው ለዶግማ፣ ለሥርዓት፣ ለቀኖና፣ ለትውፊትና ለታ ሪክ ዋጋ በምትሰጠው ኦርቶዶክሳዊነት ቤተ ክርስቲያን ላይ ነው፡፡ ተሐድሶ መናፍቃን ማመን ብቻ በቂ ነው፤ ስለሚሉ ቤተ ክርስቲያን መሔድ፣ ቅዳሴ ማስቀደስ፣ ቅዱስ ቁርባን መቀ በል፣ መጾም መጸለይ፣ መስገድ፣ መመ ጽወት፣ ምግባር ትሩፋት መሥራት አያስፈልግም፤ ባይ ናቸው፡፡ የቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ መዋቅር፣ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን፣ የክህነት ደረጃ፣ ለሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን መታዘዝ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም፤ በማለት ሰው ሕይወቱን በሥርዓት አልበኝነት እንዲመራ ያበረታታሉ፡፡
በተሐድሶ መናፍቃንን በመንገድ ጠራጊነት በሚያገለግሏቸው ሚዲያ ዎች የሚተላለፉ "ትምህርቶች" ሥር ዓት አልበኝነትን የሚያሰፍኑ መሆናቸ ውን የሚከተለው አባባላቸው ማሳያ ነው፡፡
ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃል፣ በአፉ መስክሮ ይድናልና፣ መንገዱ ረጅም አይደለም ወገኖቼ፤ ውጣ ውረድ የለበትም፡፡ የምትከፍለው አይደለም፣ የተከፈለበት ነው፡፡ አንተ የምታደር ገው ነገር አይደለም፣ የተደረገልህ ነው፡፡ የምትሆነው አይደለም፣ የሆነልህ ነው፡፡ ይህንን ብታምን በአፍህ ብት መሰክር ትድናለህ፡፡ የእግዚአብሔር ቃል የሚነግረን መዳን ማለት በልብ ማመ ንና በአፍ መመስከር እንጂ እኛ በድ ካም የለመድነውን አይደለም፡፡ እየታገ ልን አንዴ ሲሳካ አንዴ ሳይሳካ እያለ ቃቀስን የምንኖረውን አይደለም፡፡
ይህ ንግግር መዳን በእምነት ብቻ ብሎ የተነሣው የሉተር ትምህ ርት እንጂ የቤተ ክርስቲያን አስተም ህሮ አይደለም፡፡ የቤተ ክርስቲያን አስተ ምህሮ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንደ ተናገረው "በብዙ ድካምና በብዙ መከራ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት እንገባ ዘንድ ይገባናል" የሚል ነው፡፡ ሥርዓት አልበኝነትን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለማስገባት ቆርጠው የተነሡት የተሐድሶ መናፍቃን ግን ኦርቶዶክሳዊነትን እን ዲህ ያቃልሉታል፡፡
"ጌታን የምናመልከው የሃይማኖት ድርጅት በመቀያየር አይደለም፡፡ ጴን ጤም መሆን ኦርቶዶክስም መሆን አያጸድቅም፡፡ ሕይወት እና ጽድቅ ክርስቶስ ኢየሱስን በማመን ብቻ ነው የሚገኘው። ጴንጤም ሆነ ኦርቶ ዶክስ መሆን ለእውነተኛ ወንጌል መረ ዳት ዋስትና አይደለም፡፡ ክርስቶስ በመ ጨረሻ ለፍርድ ሲመጣ ጴንጤ በዚህ፣ ኦርቶዶክስ በዚህ፣ ተሐድሶ በዚያ በኩል ብሎ አያሰልፍም፡፡ ሃይማኖት ማለት በእግዚአብሔር ልጅ አምኖ መመስከር ነው እንጂ ድርጅት መከተል አይደለም" በማለት ሃይማኖት አን ዲት ናት ያለውን የቅዱስ ጳውሎስን ቃል ሽረው፣ ብዙ መንገድ እንዳለ አድ ርገው አልፎ ተርፎም ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ሃይማኖትን ድርጅት ብለው አቃለው ይናገራሉ፡፡
የዚህ ሁሉ ዓላማ ሥርዓት አልበ ኝነት የነገሠበት ግላዊ ሕይወትን በም እመናን ላይ ለማንበር ነው፡፡ የጥ ፋት አባቶቻቸው ምዕራባውያን የሰው ልጆች የእግዚአብሔር አጋዥነት ሳያስ ፈልጋቸው ሓለፊነት ያለው "ሞራ ላዊ" ሕይወት በመምራት ለሰው ልጆች ፍጹም ጥቅምና ደህንነት የመብቃት ዐቅምና ሓላፊነት አላቸው፡፡ በምክንያታዊነት በመመራት፣ ጥልቅ በመሆነ መረዳትና በተግባራዊ የሕይወት ልምምድ ሕይወትን ፍጹምና ደስታ የሞላበት ለማድረግ ይችላሉ፡፡ ይህም አስተሳሰብ በየጊዜው በዝግመተ ለውጥ እያደገ የሚሔድ ነው፡፡ አስተሳሰቡ በእሴቶች መሠረት በሚቀመጡ ግቦች እንዲመራ በሚያደርጉ አስተዋይ ሰዎች መሪነት በጥንቃቄ ቅርፅ እያገኘና ከዕውቀታችን ማደግ ጋር እየተለወጠ የሚሔድ ነው፡፡ እሳቤውም እንደ ሰው ልጅ ሕይወት ያላማቋረጥ የሚሻሻ ልና የሚዘምን ነው፤ በማለት ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉም የሚለ ውን የጌታ ቃል ለማፍረስ ይሠራሉ (ምንጭ፣ የ፲፱፻፺፫ /እ.ኤ.አ/ የሰብአ ዊነት መግለጫ) በማለት ጽፈዋል፡፡
የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ የሚ ለው "ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አት ችሉም" ነው፡፡ ሁሉ በእርሱ ሆነ፤ ከሆነ ውስ አንዳች እንኳን ያለ እርሱ የሆነ የለም፡፡ ምድርና ሞላዋ በእግዚአብሔር ተፈጠሩ፡፡ እግዚአብሔር ቢፈቅድ ይህን ወይም ያን እናደርጋለን በሉ፡፡ ሁሉ የእርሱ፣ በእርሱ፣ ለእርሱ የሆነ አም ላክ የተመሰገነ ይሁን፤ የሚል ነው፡፡ የመልእክቱ አስተላላፊዎች እነዚህን ጥቅሶች ውሸት ለማድረግ የሚሠሩ መሆናቸውን ድርጊታቸው ይመሰክ ራል፡፡
፫. አክራሪነት፡- አክራሪነት ማለት ከእኔ የተለየ አስተሳሰብ ያለው አካል በምድር ላይ ሊኖር አይገባም የሚል ጽንፈኝነት ነው፡፡ ምዕራባውያን አክራሪነ ትን በመዋጋት ስም እያስፋፉ የሚገ ኙት አክራሪነትን ነው፡፡ ልዩነቱ ምዕራ ባውያን አክራሪነትን የሚያስፋፉበት መንገድ እስልምናን ሽፋን አድር ገው አክራሪነትን እንደሚያራምዱ ወገ ኖች በጦር መሣሪያ ሳይሆን በኢኮ ኖሚ፣ በትምህርት፣ በሥልጠና፣ በል ማት፣ በባህልና ሃይማኖት ተሐድሶ፣ በሰብአዊ መብት ማስከበር፣ አክራሪነ ትን በመከላከል፣ ወዘተ ሽፋን መሆኑ ነው፡፡ ምዕራባውያን በዓለም ላይ ፕሮቴ ስታንት ብቸኛ እምነት እንዲሆን፣ ምዕራባዊ ባህልና አስተሳሰብ በዓ ለም ሁሉ እንዲንሰራፋ፣ "በነጻነት" ስም የሚሰበከው ዓለማዊነት እንዲስፋፋ፣ ወዘተ እየሠሩ ነው፡፡ እነዚህ ሁሉ ተግ ባራት የመጨረሻ ዓላማቸው የሌሎ ችን አገራት እምነት፣ እሴት፣ አስተ ሳሰብ፣ ባህል፣ ወግ፣ ወዘተ በማፍረስ በፕሮቴስታንታዊ ባህል ለመተካት ከተቻለ ደግሞ ፈጽሞ ዓለማዊ ለማድ ረግ ነው፡፡
በዓለም ላይ ማንነታቸውን እንዲ ያጡ፣ ያላቸው የተፈጥሮ ሀብት በሌ ሎች እንዲወሰድባቸው የተደረጉ አገ ራት ዜጎች አሸባሪዎች ሆነዋል፡፡ አሸባ ሪዎች የሆኑት ግን ተፈጥሯቸው ለሽብር የሚስማማ ሆኖ ወይም አሸባ ሪነትን መርጠውት ሳይሆን አማራጭ ስለሌላቸው ነው፡፡ ጆን ፐርኪንስ በኢኳ ዶር የሆነውን ጠቅሶ ሲናገር እንዲህ ነበር ያለው፡-
â€Â¦ ነዳጅ ለማውጣት ሲባል ከቦ ታቸው ለተፈናቀሉትና ጫካቸው ተመን ጥሮ አካባቢያቸው ወድሞ በእጅጉ ለተጎዱት፣ ገንዘቡም ለዕለት ኑሯቸው እጅግ አስፈላጊያቸው ለሆነውና የሚበላ ምግብና የሚጠጣ ውኃ በማጣት ለሚሰቃዩት ነዋሪዎች የሚደርሳቸው ከአገሪቱ ከሚወጣው ነዳጅ ሽያጭ ከእያንዳንዱ መቶ ዶላር ውስጥ ከ2.5 ዶላር በታች ነው፡፡ እነዚህ ሕዝቦች በሙሉ - በኢኳዶር ያሉ ሚሊዮኖች እና በዓለም ዙሪያ ያሉ ቢሊዮኖች አንድ ቀን አሸባሪዎች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ እንዲህ የሚሆኑት ግን በኮሚዩኒዝም ወይም በነውጠኛነት ስለሚያምኑ አይደ ለም፤ ወይም በተፈጥሯቸው ክፉዎች ስለሆነ አይደለም፤ የእኛ ድርጊት ተስፋ ስላስቆረጣቸው ብቻ ነው እንጂ፡፡ (የተሐ ድሶ መናፍቃን ዘመቻ ገጽ ፳፫)
የካቶሊክና የፕሮቴስታንት ሚሲዮ ናውያን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ለማፍረስ በእነርሱ ቋንቋ "ለማደስ" ብዙ ጊዜ ተመላልሰ ዋል፡፡ በዚህ ምልልሳቸው የመጨረሻ ግባቸው ተሳክቶ ቤተ ክርስቲያንን ሙሉ በሙሉ ፕሮቴስታንት ማድረግ ባይች ሉም ብዙ የፕሮቴስታንት ችርቾችን አቋቁመዋል፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምእመና ንን ዘርፈዋል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥም የሚፈልጉት ልክ በምዕራቡ ዓለም እንዳደረጉት የኢትዮጵያ ቤተ ክርስ ቲያንን ዶግማ፣ ቀኖና፣ ትውፊት፣ ታሪክና ሥርዓት በማጥፋት ወጥ የሆነ ፕሮቴስታንታዊ አስተሳሰብን ማንበር ነው፡፡ ይህ በእነርሱ ቋንቋ "ሰዎች እጃቸውን ለጌታ እንዲሰጡ ማድረግ ነው" እየተደረገ ያለው ግን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን ማንነት ማጥፋት ነው፡፡
ከዚህ በላይ አክራሪነት፣ አክራሪነ ትንም የሚያስፋፋ ተግባር የለም፡፡ ማንም ሰው የፈለገውን እምነት የመከ ተል፣ የፈለገውን አስተሳሰብ የመያዝ መብት አለው፡፡ ይህ ለሁሉም በሥነ ፍጥረት የታደለ መብት ነው፡፡ በተሐድሶ መናፍቃን ዘንድ ግን ይህ አይሠራም፡፡ የእምነቱ ተከታዮች ሳይሆኑ "ኦርቶዶክ ሳውያን ነን" በማለት ምእመናንን ከቤተ ክርስቲያን እያስወጡ ለሌሎች ቤተ እምነቶች ይገብራሉ፡፡ በገንዘብ በማታ ለል፣ በትውውቅ በመቀራረብ አልፎ ተርፎም በጉልበት በማስፈራራት ጭምር ምእመናንን ከበረታቸው የማስወጣት ሰፊ ዕቅድ ይዘው ይሠራሉ፡፡ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ቁጭ ብለው ቤተ ክርስቲያንን ይሳደባሉ፤ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ሃይማኖትን የሚከተሉ ምእ መናንን ደግሞ ደንቆሮ፣ ያልበራላቸው፣ ኋላ ቀር፣ ጣዖት አምላኪ፣ ግብዝ፣ ወዘተ በማለት ሰው የፈለገውን እምነት የመከተል ሰብአዊ መብቱን ይጋፋሉ፡፡ እንግዲህ ከሰው ቤት ገብቶ አዛዥና ናዛዥ ለመሆን ከመፈለግ እና አልወ ጣም ብሎ ከመሟገት በላይ፣ "ኦርቶዶ ክሳዊ ነኝ" የሚል ጭንብል ለብሰው የማያምኑበትን እምነት ከመሳደብ በላይ፣ የራስን እውነት ከመናገር አልፎ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ትክክል አይደለችም እያሉ ከመሳደብ በላይ አክ ራሪነት ምንድን ነው?
፬. ግብረ ሰዶማዊነት፡- ግብረ ሰዶ ማዊነት ከተፈጥሮ ሕግ ውጭ የሆነ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ነው፡፡ እግዚ አብሔር በዚህ ዐመጽ ውስጥ የነበሩ የሰዶምንና የገሞራን ሕዝቦች በእሳት ዲን አጥፍቷቸዋል፡፡ እግዚአብሔርን ከሚያስቆጡ የሥጋ ሥራዎች ውስጥ አንዱ ግብረ ሰዶም ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ በሮሜ መልእክቱ ምዕራፍ ፩፣፳፬-፳፰ "â€Â¦ እግዚአብሔር ለሚያስነውር ምኞት አሳልፎ ሰጣቸው፤ ሴቶቻቸ ውም ለባሕርያቸው የሚገባውን ሥራ ለባሕርያቸው በማይገባው ለወጡ፤ እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱት መጠን እግዚአብሔር የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው" በማለት ግብረ ሰዶማዊ ነት ትልቅ ኀጢአት መሆኑን ነግሮናል፡፡ "ለባሕርያቸው የማይገባውን" የሚለው ግብረ ሰዶማዊነት የተፈጥሮን ሥርዐት የሚቃረን፣ የርኩሰት ሥራ፣ ጸያፍ፣ ሥጋን የሚያዋርድ፣ እግዚአብሔርን የሚያስቆጣና ቅጣትን የሚያስከትል መሆኑን ያስረዳናል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ግብረ ሰዶማዊነት ከእግዚአብሔር መን ግሥት የሚያስወጣ መጥፎ ድርጊት መሆኑንም እንዲህ በማለት ነግሮ ናል፡፡ "ዐመጸኞች የእግዚአብሔርን መን ግሥት እንዳይወርሱ አታውቁምን? አትሳቱ፤ ሴሰኞች ቢሆን ወይም ጣዖ ትን የሚያመልኩ ወይም አመንዝ ሮች ወይም ቀላጮች ወይም ከወንድ ጋር ዝሙት የሚሠሩ â€Â¦ የእግዚአብ ሔርን መንግሥት አይወርሱም" (፩ኛ ቆሮ. ፮፣፱)፡፡
አማናዊውና ተፈጥሯዊው ትምህ ርት ይህ ሆኖ ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መጣላትን እንደ ነጻነት የሚቆጥ ሩት ምዕራባውያን ግብረ ሰዶማዊ ነት በሰብአዊ መብት፣ በፍቅር፣ ወዘተ ስም ሕጋዊ እንዲሆን እየጣሩ ነው፡፡ በዓለም ታዋቂ የሚባሉ ሰዎችም ግብረ ሰዶማዊነትን አስመልክቶ በበጎ ጎን ጽፈዋል፡፡ ለምሳሌ፡- ሲግመንድ ፍሮ ይድ የሚባል የሥነ ልቡና ባለሙያ፡-
ግብረ ሰዶምን እንደ ወንጀል መቁ ጠር ትልቅ ኢፍትሐዊነት ነው፡፡ በጥን ቱም ሆነ በዘመናዊ ዓለም በጣም የሚ ከበሩ ግለሰቦች (ለምሳሌ፡- ፕላቶ፣ ሚካ ኤል አንጀሎ፣ ሊኦናርዶ ዳቪንቺ፣ ወዘተ) ግብረ ሰዶማውያን ነበሩ፡፡ ግብረ ሰዶም ጥቅም የለውም፤ ነገር ግን የሚ ያሳፍር፣ የሚያስጠላ፣ የሚያስቀጣና እንደ በሽታ የሚቆጠር ነገር ሳይሆን እንደ አንድ አማራጭ የሥራ ዘርፍ መታየት አለበት፤ ብሏል፡፡
ካረን ሁከር የምትባል ሴት በጥናት ደረስኩበት የምትለውን "ግብረ ሰዶማው ያን በሕይወታቸው የሥነ ልቡና ቀውስ አልደረሰ ባቸውም፡፡ ስለዚህ ግብረ ሰዶምና ሥነ ልቡናዊ ቀውስ ቀጥተኛ ግንኙነት የላቸውም" ብላ በመገለጽ ግብረ ሰዶማዊነትን ተፈጥ ሯዊ ለማስመሰል ሞክራለች፡፡ ሐቭሎክ ኢሊስ ደግሞ "አብዛኞቹ ግብረ ሰዶ ማውያን ለሚኖሩበት ማኅበረሰብ ከፍ ተኛ አስተዋጽኦ አድርገዋል"፤ ይላል፡፡ እነዚህ ሁሉ አስተሳሰቦች የእግዚአብ ሔርን መኖር በማያምኑ ወይም በሚጠ ራጠሩ አካላት የሚቀነቀኑ ስለሆነ ብዙ ላያስገርሙን ይችላሉ፡፡ የሚያሳዝነው ግን እግዚአብሔርን እናውቃለን፤ "ክርስ ቶስን እንሰብካለን" በሚሉ አካላት እነ ዚህ አስተሳሰቦች ትክክል ናቸው ተብ ለው መወሰዳቸው ነው፡፡
አብዛኛዎቹ የአውሮፓ ኅብረት አገራት ግብረሰዶማዊነትን የሚደግፉ ናቸው፡፡ ስፔን፣ ጀርመን፣ ቼክ ሪፐብ ሊክ፣ ፈረንሣይ፣ እንግሊዝ፣ ኢጣሊያ፣ ግሪክ፣ ፖላንድ የመሳሰሉ አገራት ግብረ ሰዶማዊነትን የሚደግፉ ናቸው፡፡ በሌላው ዓለም ስናይ አሜሪካ፣ አርጀን ቲና፣ ቺሊ፣ ሜክሲኮ፣ ብራዚል፣ ቬንዙ ዌላ፣ አውስትራሊያ፣ ፊሊፒንስና ጃፓን ደጋፊ አገራት ናቸው፡፡ ግብረ ሰዶማ ዊነትን በሕግ ከፈቀዱ አገራት መካከል ደግሞ፡- አሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ ኔዘርላ ንድ፣ ስዊድን፣ ኖርዌይ፣ ካናዳ፣ ቤልጂ የም፣ አውስትራሊያና ደቡብ አፍሪካ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ግብረ ሰዶማዊነትን በመቃወም ኢትዮጵያ ከናይጀሪያ ቀጥሎ ሁለተኛ ናት፡፡
በእነዚህ አገራት የሚገኙ እና ወን ጌልን እንስበክላችሁ የሚሉን የካቶሊ ክና የፕሮቴስታንት ቸርቾች ግብረ ሰዶማዊነት የሰውን ልጅ የሚያጠፋ መሆኑን የሚናገረውን የቅዱስ ጳውሎ ስን መልእክት እያስተማሩ ግብረ ሰዶ ማዊነትን በዐዋጅ ተቀብለዋል፡፡ በክር ስትና ስም የሚጠሩ "አብያተ ክርስቲ ያናት" የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን ኀጢአት ወይም የሥነ ምግባር ግድ ፈት አድርገው አያዩትም፡፡ እንዲያ ውም ግንኙነቱን በመባረክ እንደ ጋብቻ እየቆጠሩት ነው፡፡ ግብረ ሰዶማዊነትን ፈቅደው በቸርቾቻቸው ወንድን ከወ ንድ፣ ሴትን ከሴት እያጋቡ ነው፡፡ ወን ጌል ገልጠው እያስተማሩ፣ የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ነን እያሉ ግብረ ሰዶ ማውያንን በመቅደሳቸው አቁመው የሚያጋቡ የእምነት ድርጅቶች ስለ መኖራቸው ብዙ የተባለበት ነው፡፡ ለም ሳሌ፡- ፈረንሳይ ውስጥ የሚገኙ የፕሮ ቴስታንት "አብያተ ክርስቲያናት" ጠቅ ላይ ሲኖዶስ ግብረ ሰዶማውያን ጋብ ቻቸውን "በቤተ ክርስቲያን" ውስጥ እንዲፈጽሙ ፺፬ በመቶ በሆነ ድምፅ አሳልፏል፡፡
"የአብያተ ክርስቲያናቱ" መሪ ሲኖዶሳቸው ወደፊት እያንዳንዳንዱ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ይህን የግብረ ሰዶማውያን ጋብቻ በማጽደቅ ፍላጎታ ቸው ከሆነ ባርኮ ለማጋባት መንገዱ ተከፍቷል ብለዋል፡፡ የስኮትላንድ ሉተ ራን "ቤተ ክርስቲያን" ደግሞ ተመሳ ሳይ ጾታ ካላቸው ተጋቢዎች መካከል ዲያቆናትንና ካህናትን መሾም የሚቻል በትን ሕግ አጽድቃለች፡፡ በስዊድን የሚገ ኘው የፕሮቴስታንት "አብያተ ክርስቲ ያናት ሲኖዶስ" የግብረ ሰዶማውያንን ጋብቻ ለመባረክ በ፳፻፲፪ ውሳኔ ሲያስተላ ልፍ፣ የዴንማርክ "ሲኖዶስ" በበኩሉ እያንዳንዱ የፕሮቴስታንት "ቤተ ክርስቲ ያን" ይህን ጋብቻ መፈጸም ግዴታው እንደሆነ በመግለጽ ውሳኔውን በሥሩ ላሉ "አብያተ ክርስቲያናት" አስተላ ልፏል፡፡ የኖርዌይ ፕሮቴስታንት "ቤተ ክርስቲያንም" ከዴንማርክ ቀጥሎ ተመሳ ሳይ ውሳኔ አስተላልፋለች፡፡
በአጠቃላይ የካናዳ የተባበሩት "ቤተ ክርስቲያን" (the United Church of Canada)፣ የክርስቶስ የተባበሩት "ቤተ ክርስቲያን" (The United Church of Christ)፣ የጀርመን ሉተራን "አብ ያተ ክርስቲያናት" (all German Lutheran)፣ የኢኬዲ ተሐድሶና የተባ በሩት "አብያተ ክርስቲያናት" (refor med and united churches in EKD)፣ የስዊዘርላንድ ተሐድሶ "አብያተ ክርስቲያናት" (all Swiss reform ed churches)፣ የኔዘርላንድ ፕሮቴ ስታንት "ቤተ ክርስቲያን" (the Protestant Church in the Netherlands)፣ የቤልጂየም የተባበሩት ፕሮ ቴስታንት "ቤተ ክርስቲያን" (the Uni ted Protestant Church in Belgium)፣ የፈረንሣይ የተባበሩት ፕሮቴስታንት "ቤተ ክርስቲያን" (the Unit ed Protestant Church of France)፣ የዴንማርክ "ቤተ ክርስ ቲ,ያን" (the Church of Denmark)፣ የስዊድን "ቤተ ክር ስቲያን" (the Church of Sweden)፣ የአይስላንድ "ቤተ ክርስቲ ያን" (The Church of Iceland)፣ የኖርዌይ "ቤተ ክርስቲያን" (the Church of Norway)፣ የፊንላንድ ወንጌላ ዊት ሉተራን "ቤተ ክርስቲያን" (The Eva ngelical Lutheran Church of Finland)፣ የሜትሮፖሊታን ኅብረት "ቤተ ክር ስቲያን" (The Metropolitan Community Church)፣ የሐዋርያት ጴንጤ ቆስታል አጋዥ ዓለም አቀፋዊ ኅብ ረት (The Global Alliance of Affirming Apostolic Pentecostals (GAAAP)) ግብረ ሰዶማዊ ነትን ያጸደቁና ግብረ ሰዶማውያንን በጸሎት የሚያጋቡ "አብያተ ክርስቲ ያናት" ናቸው፡፡
በዓለም አቀፍ ደረጃ ለወንድም ለሴትም ግብረ ሰዶማውያን ክህነት የሰጡ "አብያተ ክርስቲያናት" ደግሞ፡- የስኮትላንድ፣ የእንግሊዝ፣ የዌልስ፣ የስዊድን፣ የኖርዌይ፣ የዴንማርክና የአይስላንድ "አብያተ ክርስቲያናት"፣ የፊንላንድ ወንጌላዊት ሉተራን "ቤተ ክርስቲያን"፣ የጀርመን ወንጌላዊት ሉተ ራን "ቤተ ክርስቲያን"፣ የኔዘርላንድ ፕሮቴስታንት "ቤተ ክርስቲያን"፣ የቤል ጂየም የተባበሩት ፕሮቴስታንት "ቤተ ክርስቲያን"፣ የስዊዘርላንድ ተሐድሶ "ቤተ ክርስቲያን"፣ የፈረንሣይ የተባ በሩት ፕሮቴስታንት "ቤተ ክርስቲ ያን"፣ የካናዳ ወንጌላዊት ሉተራን "ቤተ ክርስቲያን"፣ የካናዳ አንግሊካን ቤተ ክርስቲያን፣ የጥንቷ ካቶሊክ "ቤተ ክርስቲያን" እና የጃፓን የተባበሩት የክርስቶስ "ቤተ ክርስቲያን" ናቸው፡፡
፭. አምልኮተ ሰይጣን፡- ምዕራባው ያን የሥልጣኔያቸው የመጨረሻ ጥግ "አምልኮተ ሰይጣን" ሆኗል፡፡ በተለያዩ አገራት የሚገኙ በተለይም በዘመናዊ የቴክኖሎጂ ውጤቶች በመላው ዓለም የሚታዩት ሙዚቀኞች፣ የእግር ኳስ ተጨዋቾች፣ ሞዴሊስቶች፣ የፊልም ተዋናዮች፣ ወዘተ ሰይጣንን ወደ ማም ለክ ደረጃ ደርሰዋል፡፡ እነዚህ አገራት ግን "የአፍሪካውያንን ዐይን ለማብራት በሚል" ብዙ ሚሲዮኖችን ወደ አፍሪካ ይልካሉ፡፡ አበው የራሷ አሮባት የሰው ታማስላለች እንዲሉ የራሳቸው ዜጎች በነጻነት፣ በዲሞክራሲያና ሰብአዊ መብት፣ በሥልጣኔ፣ በልማት፣ ወዘተ ስም ከአምልኮተ እግዚአብሔር ወጥ ተው ወደ አምልኮተ ሰይጣን እየገቡ፣ የእምነቱ ተከታይ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን መድረክ ላይ ቆመው የክርስቶስን ወን ጌል ገልጠው የሚያስተምሩ ፓስተሮ ቻቸው በአምልኮተ ሰይጣን እየታሙ በአርአያቸውና በአምሳላቸው የፈጠ ሯቸው ተሐድሶ መናፍቃን ለእኛ "ወንጌል ካልሰበክን" ይላሉ፡፡
የተሐድሶ መናፍቃን የመጨረሻ ግባቸው ይህ ነው፡፡ ምክንያቱም ገለጻ ሲያደርጉ በአምኮተ ሰይጣን የሚታ ሙትን ጆሹዋንና ፓስተር ክሪስን እንደ አርአያ ይጠቅሷቸዋልና፡፡ መጽ ሐፍ ቅዱስ የሚያዝዘው "የእግዚአ ብሔርን ቃል የተናገሯችሁን ዋኖቻች ሁን አስቡ፣ የኑሯቸውንም ፍሬ እየ ተመለከታችሁ በእምነት ምሰሏቸው" በማለት ነው፡፡ የተሐድሶ መናፍቃን ዋኖቻችን ብለው የሚጠሯቸው ግን ምግባር የሌላቸው ብቻ ሳይሆኑ በእግ ዚአብሔር ማመናቸው እንኳን የማይ ታወቁ ሰዎችን ጭምር ነው፡፡ ጆሹዋና ፓስተር ክሪስ ርኩሳን መናፍስትን በመጥራት አጋንንትን እናወጣለን የሚሉ እንደሆኑ ብዙ ማስረጃዎች እየ ወጡ ነው፡፡ ስለዚህ የተሐድሶ መናፍ ቃን የመጨረሻ ግብ ዓለማዊነትን አልፎ ሰው በዘቀጠ የሕይወት ማንነት ውስጥ እንዲኖር የሚያደርጉ እኩይ ተግባራትን በውስጡ በማንገሥ ግብረ ሰዶማዊና ሰይጣን አምላኪ እንዲሆን ማድረግ ነው፡፡

 

Read more http://www.eotcmk.org/site/-mainmenu-24/--mainmenu-26/2059-2016-01-06-tehadeso-amelekote-seyetane