መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ
- Written by ሊቀ ብርሃናት ቀሲስ ሄኖክ ያሬድ
በመንፈስ ቅዱስ የተሞላ ቤተሰብ
- ሕፃኑም ዮሐንስ በጌታ ፊት ታላቅ ይሆናልና፥ የወይን ጠጅና የሚያሰክር መጠጥ አይጠጣም፤ ገናም በእናቱ ማኅፀን ሳለ መንፈስ ቅዱስ ይሞላበታል። (ሉቃ ፩፥፲፭)
- ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ ፅንሱ በማኅፀንዋ ውስጥ ዘለለ፤ በኤልሳቤጥም መንፈስ ቅዱስ ሞላባት። (ሉቃ ፩፥፵፩)
- አባቱ ዘካርያስም መንፈስ ቅዱስ ሞላበትና ትንቢት ተናገረ። (ሉቃ ፩፥፷፯)
መጽሐፍ ቅዱስ የዚህን ታላቅ ቤተሰብ ታሪክ በሉቃስ ወንጌል ላይ ካህኑ ዘካርያስ እና ከካህኑ ከአሮን ወገን የሆነች ኤልሳቤጥ ሁለቱም በጌታ ትእዛዝና ሕግጋት ሁሉ ያለ ነቀፋ እየሄዱ በእግዚአብሔር ፊት ጻድቃን ነበሩ በማለት ይገልፃል። የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ የልደት ታሪክም እንዲህ በሚለው በቅዱስ ገብርኤል ብሥራት ይጀምራል፦ ዘካርያስ ሆይ፥ ጸሎትህ ተሰምቶልሃልና አትፍራ ሚስትህ ኤልሳቤጥም ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፥ ስሙንም ዮሐንስ ትለዋለህ። ደስታና ተድላም ይሆንልሃል፥ በመወለዱም ብዙዎች ደስ ይላቸዋል። በጌታ ፊት ታላቅ ይሆናልና፥ የወይን ጠጅና የሚያሰክር መጠጥ አይጠጣም፤ ገናም በእናቱ ማኅፀን ሳለ መንፈስ ቅዱስ ይሞላበታል፤ ከእስራኤልም ልጆች ብዙዎችን ወደ ጌታ ወደ አምላካቸው ይመልሳል። እርሱም የተዘጋጁትን ሕዝብ ለጌታ እንዲያሰናዳ፥ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች የማይታዘዙትንም ወደ ጻድቃን ጥበብ ይመልስ ዘንድ በኤልያስ መንፈስና ኃይል በፊቱ ይሄዳል። (ሉቃ ፩፥፲፭-፲፯)
የእግዚአብሔርን ትእዛዝና ሕግጋት እየጠበቀ በቅድስና ይኖር የነበረው ካህኑ ዘካርያስ ከእግዚአብሔር ተልኮ የመጣውን የቅዱስ ገብርኤል ቃል ባለመስማቱ ሕፃኑ እስከሚወለድ ድረስ ድዳ እንደሚሆን በአብሳሪው መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ተነገረው። ይወለዳል የተባለው መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስን የኤልሳቤጥ መፅነስ በቤተሰቡ መካከል ለረጅም ጊዜ ይፈለግ የነበረ ስለነበር ደስታ ሲፈጥር የካህኑ ዘካርያስ ድዳ መሆን ደግሞ ቤተሰቡን የሚያስጨንቅ ሌላ ክስተት ሆነ። ቅድስት ኤልሳቤጥም ባለመውለዷ ምክንያት በአካባቢው ሰዎች ግን እግዚአብሔር እንዳዘነባትና ልጅ እንደከለከላት ይነገርባት ስለነበር የልምላሜዋ ዘመን ካለፈ በኋላ መፅነስ በመቻሏ ነቀፌታዬን ከሰው መካከል ያስወግድልኝ ዘንድ ጌታ በተመለከተበት ወራት እንዲህ አድርጎልኛል (ሉቃ ፩፥፳፭) በማለት ደስታዋን ገልፃለች።
አስቀድሞ በነቢዩ በኢሳይያስ የአዋጅ ነጋሪ ቃል ተብሎ እንደተነገረው የእግዚአብሔርን መንገድ በምድረ በዳ ጥረጉ፥ ለአምላካችንም ጐዳና በበረሀ አስተካክሉ በማለት ፊት አውራሪ ሆኖ የሚላከውን ቅዱስ ዮሐንስን የፀነሰችው ቅድስት ኤልሳቤጥ በፀነሰች በስድስተኛው ወር እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ልትጠይቃት ወደ እርሷ በሔደች ጊዜ እጅግ የሚያስገርም ሁኔታ ተፈጠረ። ይኸውም ቅዱስ ዮሐንስ በማኅፀን ውስጥ ኾኖ ለቅድስት ድንግል ማርያም እና በማኅፀኗ ላለው ለዓለም መድኃኒት ለኢየሱስ ክርስቶስ ሰግዷል (ሉቃ. ፩፥፳፮-፵፩) ።
ጴጥሮስ ወጳውሎስ
- Written by አቶ አብርሃም ሰሎሞን
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በየዓመቱ ሐምሌ ፭ ቀን ጴጥሮስ ወጳውሎስ በማለት ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ እና ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ መልካሙን የክርስትና ገድል ተጋድለው ሰማዕትነት የተቀበሉበትን ቀን በታላቅና በተለየ ሁኔታ ታከብራለች። ክርስትናን በማስፋፋት ከፍተኛውን ሚና የተጫወቱት እነዚህ ቅዱሳን አባቶች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ መልእክታትን ጽፈዋል። ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ስምንት ምዕራፎችን የያዘ ሁለት መልእክታትን ሲጽፍ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ደግሞ አንድ መቶ ምዕራፎችን የያዘ አሥራ-አራት መልእክታትን ጽፏል። ለአግልግሎት የጠራቸውም የክብር ባለቤት የሆነው አምላካችን ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
ቅዱስ ቁርባን ከመቀበል አስቀድሞ እና ቅዱስ ቁርባን ከተቀበሉ በኋላ የሚጸለይ ጸሎት
- Written by ሊቀ ብርሃናት ቀሲስ ሄኖክ ያሬድ
ቅዱስ ቁርባን ከመቀበል አስቀድሞ ከቅዱስ ምሥጢር የሚቀበሉ ሁሉ እንዲህ ይበሉ፤
አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! ርኵስት ከሆነች ከቤቴ ጠፈር በታች ትገባ ዘንድ የሚገባኝ አይደለም።
እኔ አሳዝኜሃለሁና በፊትህም ክፉ ሥራ ሠርቻለሁና በአርኣያህና በአምሳልህ የፈጠርኸው ሥጋዬንና ነፍሴን ትእዛዝህን በማፍረስ አሳድፌአለሁና ሥራም ምንም ምን የለኝምና። ነገር ግን ስለ መፍጠርህና እኔን ለማዳን ሰው ስለ መሆንህ፣ ስለ ክቡር መስቀልህም፣ ማሕየዊት ስለ ምትሆን ስለ ሞትህ፣ በሦስተኛው ቀን ስለ መነሣትህም ጌታዬ ሆይ ከበደልና ከመርገም ሁሉ፣ ከኃጢአትና ከርኵሰትም ሁሉ ታነጻኝ ዘንድ እለምንሃለሁ እማልድሃለሁም።
የቅድስናህንም ምሥጢር በተቀበልኩ ጊዜ ለወቀሳ ለመፈራረጃ አይሁንብኝ ማረኝ ይቅርም በለኝ እንጂ።
Read more: ቅዱስ ቁርባን ከመቀበል አስቀድሞ እና ቅዱስ ቁርባን ከተቀበሉ በኋላ የሚጸለይ ጸሎት
ጥያቄ ስለ ጴጥሮስ ወጳውሎስ
- Written by አቶ አብርሃም ሰሎሞን
፩- በገሊላ ባሕር አጠገብ አሳ በማጥመድ ላይ ሳለ የተጠራው፦
ሀ) ቅዱስ ጳውሎስ
ለ) ቅዱስ ጴጥሮስ
ሐ) ሁለቱም
፪- ጌታችን ስለ ምን ታሳድደኛለህ በማለት ከክፉ ሥራው ላይ ለአገልግሎት የመረጠው ሐዋርያ ማነው?
ሀ) ቅዱስ ጳውሎስ
ለ) ቅዱስ ጴጥሮስ
ሐ) ሁለቱም
የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እና ጤና
- Written by አቶ ይስሐቅ ቱራ (RN)
የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ጤናማ ክብደትን ከመጠበቅ ባሻገር የኮለስትሮልንና የደም ግፊትን መጠን ለመቀነስ ያስችላል። እድሜያቸው ከአሥራ ስምንት ዓመት በላይ ያሉ ጎልማሶች በሳምንት ውስጥ ባሉት አብዛኛው ቀናት ከግማሽ ሰዓት ያላነሰ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ እንደሚገባቸው የ ዩናይትድ ስቴትስ ዋና የጤና ጥበቃ ማእከል ያዛል።
መደበኛና ተከታታይ የሆነ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ለጤናዎ መጠበቅ ከሚያደርጉዋቸው ነገሮች ሁሉ በዋነኛነት ሊከተታተሉት የሚገባ ነው።
- የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ዋና ዋና ጥቅሞች፦
- ክብደትዎን ለመቆጣጠር
- በልብ በሽታ የመታመም እድልዎን ለመቀነስ
ሥራህን ለእግዚአብሔር አደራ ስጥ፥ አሳብህም ትጸናለች። ምሣ ፲፮፥፫
- Written by ዶ/ር ኤልያስ አያና
የርእሰ አድባራት ጽርሐ አርያም ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን በተለያዩ ተቋማት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ቆይተው ከሁለተኛ ደረጃ እና ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለተመረቁ ምዕመናን ቡራኬ ከደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ አርያም ቆሞስ አባ ኃይለሚካኤል May 21, 2017 እንዲቀበሉ አደረገች። በዓይነቱ የመጀመሪያ በሆነው በዚህ ዝግጅት ላይ 26 ተመራቂዎች በዝርዝር የቀረቡ ሲሆን፤ ከሁለተኛ ደረጃ ጀምሮ እስከ ዶክትሬት ዲግሪ ድረስ ትምህርታቸውንን ያጠናቀቁ ምዕመናን ተገኝተውበታል። ተመራቂዎች ወደ አውደ ምሕረት እየተጠሩ ቡራኬ ሲቀበሉ የቤዛ ኲሉ ሰንበት ትምህርት ቤት ዘማርያን እና ምዕመናን "እግዚአብሔር ይመስገን ለዚህ ላደረሰን" የሚለውን መዝሙር በመዘመር ለእግዚአብሔር ምስጋናን አቅርበዋል።
ስማችሁ ግን በሰማያት ስለተጻፈ ደስ ይበላችሁ። ሉቃ ፲፥ ፳
- Written by ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ
ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ምድር ላይ ከቦታ ቦታ እየተመላለሰ ካከናወናቸው ድርጊቶች አንዱ ደቀ መዛሙርትን እንዲሁም ሌሎችን አርድእት (ረዳቶችን)በመምረጥ ሥራ እንዲሠሩ ማድረግ ነበር። በምክርም ሲያጸናቸው የሚልካቸው እንደ በጎች በተኵላዎች መካከል እንደሆነና ሥራቸውም ቀላል እንዳልሆነ አስተምሯቸዋል። ወደ ከተሞች በመሄድ በዚያ ድውይ እንዲፈውሱና የእግዚአብሔርን ቃል እያስተማሩ ወደ መንግሥቱ እንዲያቀርቡ ሥልጣን ሰጣቸው።በተለይም አጋንንት በእርሱ ስም ከሰዎች እንዲወጡ ማድረጋቸው ያስደሰታቸው አርድእት፥ “ጌታ ሆይ፥ አጋንንት ስንኳ በስምህ ተገዝተውልናል” ባሉት ጊዜ ጌታችን ሲመልስ “... በጠላትም ኃይል ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጥቻችኋለሁ፥ የሚጎዳችሁም ምንም የለም። ነገር ግን መናፍስት ስለተገዙላችሁ በዚህ ደስ አይበላችሁ፥ ስማችሁ ግን በሰማያት ስለተጻፈ ደስ ይበላችሁ።” ብሏቸዋል። (ሉቃ ፩፥ ፱-፳)
Kidist Selassie Annual Celebration (ሐምሌ ሥላሴ)
- Written by አዘጋጆች
የጽርሐ አርያም ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን የቅድስት ሥላሴን ዓመታዊ ክብረ በዓል የፊታችን ሐምሌ ፲፮ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም (July 23, 2017) የሃገረ ስብከታችን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዘካሪያስ እና ከተለያዩ ስቴቶች የተጋበዙ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እንዲሁም ምእመናን በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ያከበራል።
ስለዚህም በቦታው በመገኘት የዚህ መንፈሳዊ በረከት ተሳታፊ እንድትሆኑ መንፈሳዊ ጥሪያችንን በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስም እናስተላልፋለን።