- Written by ሊቀ ብርሃናት ቀሲስ ሄኖክ ያሬድ
የአሥራ ስድስቱም ጥያቄዎች መልስ በሉቃስ ወንጌል ላይ በእያንዳንዱ ምእራፍ ላይ ስለሚገኝ የመልሱን ቦታ ፈልጋችሁ ብታነቡት መጽሐፍ ቅዱስን ለማወቅ ያስችላችኋል።
፩) መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት ኤልሳቤጥ |
፱) ሐዋርያትን |
፪) ቅድስት ኤልሳቤጥ |
፲) ሌሊቱን ሁሉ ደክመው አንዳች ሳይዙ በኢየሱስ ክርስቶስ ትእዛዝ መረባቸውን ለማጥመድ ጥለው መረባቸው እስኪቀደድ ዓሣ በማጥመዳቸው ምክንያት |
፫) ኢየሱስ ክርስቶስ |
፲፩) ጻፎችና ፈሪሳውያን |
፬) አረጋዊው ስምዖን |
፲፪ ጴጥሮስ፥ እንድርያስ፥ ያዕቆብ፥ ዮሐንስ፥ፊልጶስ፥ በርተሎሜዎስ፥ ማቴዎስ፥ ቶማስ፥ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብ፥ ቀናተኛ የሚባለው ስምዖን፥ የያዕቆብ ይሁዳም፥ የአስቆሮቱ ይሁዳ። |
፭) መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ |
፲፫ ናይን |
፮) ከታዘዘላችሁ አብልጣችሁ አትውሰዱ |
፲፬ ፈሪሳውያንና ሕግ አዋቂዎች |
፯) የቅዱስ ጴጥሮስ አማት |
፲፭ ከአሥራ ሁለት ዓመት ጀምሮ ደም የሚፈስሳት ሴት |
፰) የኢሳይያስን (ትንቢተ ኢሳይያስ) |
፲፮ ጴጥሮስ፣ ያዕቆብና ዮሐንስ |
ሊቀ ብርሃናት ቀሲስ ሄኖክ ያሬድ
- Written by ዶ/ር ሰሎሞን ፎሌ
በባለፈው እትም ላይ ከማርቆስ ወንጌል ለወጣው ጥያቄ መልስ፦ (የአሥራ ስድስቱም ጥያቄዎች መልስ በማርቆስ ወንጌል ላይ በእያንዳንዱ ምእራፍ ላይ ስለሚገኝ የመልሱን ቦታ ፈልጋችሁ ብታነቡት መጽሐፍ ቅዱስን ለማወቅ ያስችላችኋል።)
፩) መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ |
፱) ጴጥሮስ፣ ያዕቆብ፣ ዮሐንስ፣ ሙሴና ኤልያስ |
፪) ስለ ሐዋርያት |
፲) ያዕቆብና ዮሐንስ |
፫) አምላካችን ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ |
፲፩) በማንም ላይ አንዳች ቢኖርባችሁ ይቅር በሉት። እናንተ ግን ይቅር ባትሉ በሰማያት ያለው አባታችሁም ኃጢአታችሁን ይቅር አይላችሁም። |
፬) ሐዋርያት |
፲፪ ሰዱቃውያን |
፭) ጴጥሮስ፣ ያዕቆብና ዮሐንስ |
፲፫ ጴጥሮስ፣ ያዕቆብ፣ ዮሐንስና እንድርያስ |
፮) ሔሮድስ |
፲፬ ሊቀ ካህናቱ |
፯) ክፉ አሳብ፥ ዝሙት፥ መስረቅ፥ መግደል፥ ምንዝርነት፥ መጐምጀት፥ ክፋት፥ ተንኰል፥ መዳራት፥ ምቀኝነት፥ ስድብ፥ ትዕቢት፥ ስንፍና |
፲፭ በርባን
|
፰) ቅዱስ ጴጥሮስን |
፲፮ መግደላዊት ማርያም |
- Written by ዶ/ር ሰሎሞን ፎሌ
፩) መቋሚያን ለመጀመርያ ጊዜ ለመዝሙር የዜማ መሣሪያነት ያዋለ ኢትዮጵያዊ ቅዱስ ያሬድ ነበር።
፪) መቋሚያ የያዕቆብ በትር ምሳሌ ነው፤ ያዕቆብ የመስቀል ምልክት ያለበትን በትሩን ከፊቱ አቁሞ ይሰግድ፥ይጸልይ ነበር (ዕብ፡፲፩፥፳፩)።
በትረ ያዕቆብም፥መቋሚያም የመስቀል ምሳሌዎች ናቸው። ጌታችን መስቀሉን በትከሻው እንደተሸከመ፥ መቋሚያውን በትከሻችን ተሸክመን እንዘምራለን። መቋሚያውን የምንደገፈው፥ መስቀል ኃይላችን መሆኑን ለመግለጥ ነው።
፫) የመቋሚያ ሥርዓተ ማሕሌት አጠቃቀም ምሳሌያዊ ትርጉም
ሀ) በሥርዓተ ማሕሌት ጊዜ መዘምራን መቋሚያን በመጀመሪያ ከላይ ወደታች ያደርጉታል። ይህም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከስማየ ስማያት መውረዱን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍስዋ ነፍስ ነስቶ መወለዱን ያመለክታል። ከዚያም መቋሚያውን ከግራ ወደ ቀኝ፤ ከቀኝ ወደ ግራ የሚያደርጉት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሐና ቀያፋ ከጲላጦስ ወደ ሔሮድስ መመላለሱን መከራ መቀበሉን ለማስብ ነው። መቋሚያን ከግራ ወደ ቀኝ ሲያሽከረክሩትም ዓለምን ዞሮ ማስተማሩን ለማጠየቅ ነው።
ለ) መዘምራን መቋምያን መሬት ላይ የሚደስቁት የማይሞት ጌታ ወደ መቃብር ወረደ ለማለት ሲሆን ወደ መሬት የደሰቁትን መልሰው ወደ ላይ ማንሣታቸው ደግሞ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ መነሣቱን ለመመስከር ነው።
ሐ) መዘምራን ከቀድሞ በበለጠ መቋምያን ከፍ አድርገው በኋላ ረጋ ብለው የሚመልሱት ዕርገቱን እና ዳግም ምጻቱን ለማዘከር ነው፥ሞቶ የተነሣው ተነሥቶም ያረገው ዳግመኛ ይመጣል ሲሉ ነው።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፣ ወለወላዲቱ ድንግል፣
ወለመስቀሉ ክቡር። አሜን!
በዶ/ር ሰሎሞን ፎሌ
- Written by ዶ/ር ሰሎሞን ፎሌ
የከበሮ ክፍሎች ትርጉም/ምሥጢር
፩) ሰፊው የከበሮ ጎን ፡- የመለኮት ምሳሌ ሲሆን የጌታችንን የባሕርይ አምላክነት ምሉዕ በኵለሄ መሆኑን እና ስልጣኑም ወሰን ድንበር እንደሌለው ሊያስታውሰን ነው። የአፉን መስፋት ስንመለከት በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት ተወስኖ የተገለጠው ኢየሱስ ክርስቶስ በህልውና ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የተስተካከለ ሁሉን የያዘ ሁሉን የሚገዛ መሆኑን ለማሳሰብ ነው።
፪) ጠባቡ የከበሮ ጎን፡- የትስብእት ምሳሌ ነው በመዝሙር ጊዜ እየተቆረቆረ ድምጽ የሚሰጠው ጠባቡ የከበሮ ጎን የወልድ በጠባብ ደረት በአጭር ቁመት ተወስኖ መገለጥን የሚያመለክት ነው። ፍጥረታትን ሁሉ የሚገዛ እሱ በስልጣኑ ሽረት በመለኮቱ ኅልፈት የሌለበት ቢሆንም ሥጋን ተዋሕዶ በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት ተወስኖ ተገልጧል።
፫) ከበሮ የሚለብሰው ጨርቅ/ ግምጃ፡- ከበሮ የጌታችን ምሳሌ እንደሆነ ከላይ አይተናል። ከዚህ አንጻር የለበሰው ጨርቅ ደግሞ በዕለተ ዓርብ አይሁድ ጌታችንን ያለበሱት ጨርቅ (ቀይ ከለሜዳ) ምሳሌ ነው። ለመዘባበቻ አይሁድ ሸፍነው “መኑ ጸፍዓከ ወመኑ ኮርአከ ተነበይ ለነ ክርስቶስ፡ በጥፊ የመታህ ማን ነው? ትንቢት ተናገር እያሉ ይጠይቁት ነበር።” ሉቃ. ፳፪፡፷፬ እያሉ የሸፈኑበት ግምጃ ምሳሌ ነው።
''ልብሱንም ገፈው ቀይ ልብስ አለበሱት'' ማቴ. ፳፮፡፳፰
፬) ከበሮ ማሰሪያ ጠፍር፡- በጌታችን ጀርባ ላይ የታየው የግርፋት ሰንበር ምሳሌ ነው። ጠፍሩን በከበሮው ላይ ስንመለከት በጌታችን ጀርባ ላይ የታየውን ሰንበር እናስታውሳለን። ''እጆቼን እና እግሮቼን ቸነከሩኝ አጥንቶቼ ሁሉ ተቆጠሩ'' መዝ. ፳፩(፳፪)፡፲፮ እንዲል ጌታችን አጥንቱ እስኪቆጠር ጀርባው እስኪቆስልተገርፏልና የዚያ ምሳሌ ነው።
፭) የከበሮው ማንገቻ፡- ከበሮ ስንመታ አንገታችን ላይ የምናስገባው ማንገቻ ጌታችንን አስረው የጎተቱበት ገመድ ምሳሌ ነው። አይሁድ ጌታችንን ወደ ቀራንዮ ሲወስዱት የእጁ መጋፊያና መጋፊያ እስኪገጥም ድረስ በገመድ የእንግርግሪት አስረው ጎትተውታል ማገቻውን ከበሮው ላይ ስናይ ይኽንን ጌታችን የታሰረበትን ገመድ እናስታውሳለን።
፮) በከበሮ ውስጥ የሚደረጉ 3 ወይም 5 ጠጠሮች ፡- ሦስት ጠጠሮች ከሆኑ ምሥጢረ ሥላሴን አምስት ጠጠሮች ከሆኑ አምስቱን አዕማደ ምሥጢራትን ያስረዳል።
የከበሮ አጠቃቀም ምሳሌያዊ ትርጉም/ምሥጢር!
፩) ከበሮ ግራና ቀኝ መመታቱ፡-“ዘበእንቲአሃ ለቤተክርስቲያን ተጸፋእከ በውስተ ዓውድ ከመትቀድሳ“ ያለውን በማስታወስ የግራና የቀኝ ጉንጩ ምሳሌ ነው።
፪) መዘምራን ግራና ቀኝ እያሸበሸቡ ከበሮ መምታታቸው፡- ይህ የሚያሳየዉ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሐና ቀያፋ፣ ከቀያፋ ወደ ጲላጦስ ያደረገው እንግልት ነው።
፫) ከበሮ መጀመሪያ በርጋታ መመታቱ ከዚያም በፍጥነት መዘዋወሩ፡- ይህ ምሳሌነቱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን አይሁድ እንደያዙት መጀመሪያ በቀስታ እየዘበቱ እንደመቱት፣ በኋላም ጲላጦስ ተመራምሮ ነፃ ሳያወጣው፣ የሰንበት ቀን ሳይገባብን ኑ እንደብድበው የማለታቸው ምሳሌ ነው ።
፬) በማሕሌት ላይ ከበሮ መሬት ላይ ተቀምጦ መመታቱ፡- ምሳሌነቱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መሬት ላይ ወድቆ መንገላታቱን ለማሳሰብ ነዉ።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፣ ወለወላዲቱ ድንግል፣ ወለመስቀሉ ክቡር። አሜን!
በዶ/ር ስሎሞን ፎሌ
- Written by ወ/ሮ ሰብለወንጌል ደምሴ
1) Who fought against King David? Goliath
2) What was the name of the short man who climbed a tree so that he can see Jesus Christ? Zacchaeus
3) Who received the ten commandments from God? Moses
4) Who has ascended into heaven ? Elijah
5) Who is The Mother of Jesus Christ? Mary
6) Where was Jesus Christ born? Bethlehem
7) Who baptized Jesus Christ? John
8) Who among the disciples/apostles had
betrayed Jesus Christ? Juda
9) What was the country the Mother of Christ fled to so as to escape from King Herod? Egypt
10) What is the name of our Church? Selassie
- Written by አቶ አብርሃም ሰሎሞን
፩- ስድስተኛው የኢትዮጵያ ቅዱስ ፓትርያርክ (አቡነ ማቲያስ)
፪- ካህኑ የመጥምቀ መለኮት አባት (ዘካርያስ)
፫- የነቢዩ ኤልያስ ደቀ መዝሙር (ነቢዩ ኤልሳዕ)
፬- በቃና ዘገሊላ ያማለደችው እናት (ቅድስት ድንግል ማርያም)
፭- የቅዱስ ጳውሎስ ስም በጌታችን ከመጠራቱ በፊት (ሳውል)
፮- በመምሬ አድባር ዛፍ ሥር እግዚአብሔር የተገለጠለት
(አብርሃም)
፯- ስምንተኛው የዐቢይ ጾም ሳምንት (ሆሣዕና)
፰- እግዚአብሔርን ከፍ ባለ ዙፋን ላይ ተቀምጦ ያየው ነቢይ
(ነቢዩ ኢሳይያስ)
፱- ጌታችን ከበለስ ዛፍ ሥር አየሁህ ያለው (ናትናኤል)
፲- በካህኑ ዔሊ ፊት ሲያገለግል የነበረው ብላቴና (ካህኑ ዔሊ)
፲፩- ጌታችን በዲያብሎስ የተፈተነበት ገዳም (ገዳመ ቆሮንቶስ)
፲፪- የጌታዬ እናት ወደኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆናል ያለች
(ቅድስት ኤልሳቤጥ)
፲፫- እግዚአብሔር ከሚጠላቸው ፮ ነገሮች አንዱ (መጽ.ምሳሌ)
(ትዕቢተኛ ዓይን)
፲፬- የቅዱስ ጴጥሮስ የቀደመ ስሙ (ስምዖን)
፲፭- በሙሴ እግር የተተካው (ነቢዩ ኢያሱ)
- Written by ዶ/ር ሰሎሞን ፎሌ
፩- መ) ጾም የምግብ ለውጥ አይደለም
፪- መ) ሁሉም ልክ ነው፤
፫- መ) ሁሉም ልክ ነው፤
፬- ለ ) ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጾመው ጾም በመሆኑ (ማቴ ፬:፪)
፭- መ) ሁሉም ልክ ነው፤
፮- ሐ) ዘወረደ
፯- መ) ሆሣዕና
፰- ሐ) ጾመ ሕርቃል እና ሰሙነ ሕማማት 15 ተጨማሪ ቀናት፤
፱- ሀ) ሙሴ እና ኤልያስ፤
፲- ሀ) ፈሪሳዊ ቢሆንም ከ፲፪ቱ ሐዋርያት አንዱ አልነበረም።