- Written by ዶ/ር ሰሎሞን ፎሌ
ባለፈው ወር ጋዜጣችን በከበሮ የጀመርነውን የቅኔ ማሕሌት የዜማ መሣሪያዎች መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትርጓሜ፤ ተምሳሌት እና ምሥጢር በመቀጠል በዚህ ወር መቋሚያን አስመልክቶ ጥያቄዎች ይኖሩናል።
መቋሚያን አስመልክቶ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ይመልሱ!
፩) መቋሚያን ለመጀመሪያ ጊዜ ለመዝሙር የዜማ ማሣሪያነት ያዋለ ኢትዮጵያዊ ማነው?
፪) መቋሚያ የምን ምሳሌ ነው?
፫) የመቋሚያን ሥርዓተ ማሕሌት አጠቃቀም አስመልክቶ የሚከተሉትን ምሳሌያዊ ትርጉም/ምሥጢር ይግለጹ!
ሀ) መቋሚያን መጀመሪያ ከላይ ወደታች ማውረድ ከዚያም መቋሚያውን ከግራ ወደ ቀኝ ማሽከርከር፤
ለ) መቋምያን መሬት ላይ መደሰቅ ከዚያም ወደ መሬት የደሰቁትን መልሰው ወደ ላይ ማንሣት፡
ሐ) ከቀድሞ በበለጠ ከፍ ማድረግ ከዚያም ረጋ ብሎ መመለስ።