- Written by ዶ/ር ሰሎሞን ፎሌ
በዚህ ወር የጥያቄ እና መልስ አምዳችን የምናተኩረዉ ከቤተ ክርስቲያናችን የቅኔ ማኅሌት ንዋያተ ቅድሳት አንዱ በሆነው የዜማ መሣሪያ ከበሮ ላይ ይሆናል። ከበሮ የሚለው ቃል አታሞ፣ ነጋሪት፣ የሚመታ፣ ትእምርተ ክብር፣ ጯሂ፣ ተሰሚ ማለት ሲሆን ምሥጢራዊ ትርጉሙም የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ነው።
ከበሮ በመጽሐፍ ቅዱሳችን በርካታ ቦታዎች ተጠቅሷል፤ ለምሳሌ፦
¨ ዘጸ. ፲፭፡፳ “የአሮን እኅት ነቢይቱ ማሪያምም ከበሮ በእጅዋ ወሰደች ሴቶችም ሁሉ በከበሮና በዘፈን በኋላዋ ወጡ።”
¨ መዝ. ፻፶፡፬ “በከበሮና በዘፈን አመስግኑት በአውታርና በእምቢልታ አመስግኑት።”
¨ መዝ. ፹ (፹፩)፡ ፪ “ዝማሬውን አንሡ ከበሮንም ስጡ፥ ደስ የሚያሰኘውን በገና ከመሰንቆ ጋር በመባቻ ቀን በከፍተኛው በዓላችን ቀን መለከትን ንፉ።”
¨ መዝ. ፻፵፱፡፫ “ስሙን በዘፈን ያመስግኑ፥ በከበሮና በመሰንቆም ይዘምሩለት።”
¨ ዮዲት ፲፮፡፪ “ዮዲትም ፈጣሪያችንን እግዚአብሔርን ከበሮ እየመታችሁ አመስግኑት። ብላለች”
የተዘረዘሩትን የከበሮ ክፍሎች ትርጉም/ምሥጢር ይግለጹ!
፩) ሰፊው የከበሮ ጎን
፪) ጠባቡ የከበሮ ጎን
፫) ከበሮ የሚለብሰው ጨርቅ/ ግምጃ
፬) ከበሮ ማሰሪያ ጠፍር
፭) የከበሮው ማንገቻ
፮) በከበሮ ዉስጥ የሚደረጉ 3 ወይም 5 ጠጠሮች
የከበሮ አጠቃቀምን አስመልክቶ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ምሳሌያዊ ትርጉም/ምሥጢር ይግለጹ!
፩) ከበሮ ግራና ቀኝ መመታቱ
፪) መዘምራን ግራና ቀኝ እያሸበሸቡ ከበሮ መምታታቸው
፫) ከበሮ መጀመሪያ በርጋታ መመታቱ ከዚያም በፍጥነት መዘዋወሩ
፬) በማሕሌት ላይ ከበሮ መሬት ላይ ተቀምጦ መመታቱ
በዶ/ር ሰሎሞን ፎሌ