Forgiveness and Reinstatement of Priesthood

የይቅርታ እና የክህነት መመለስ ብስራት በዚህም መሠረት መስከረም ፲ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም. በዳላስ ከተማ ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ የሰሜን ምስራቅ የደቡብ ምስራቅና የመካከለኛው አሜሪካ የኒውዮርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ፤ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል የዋሺንግተን ዲሲና ካሊፎርኒያ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል እንዲሁም በዳላስ የሚገኙ ስድስት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪዎችና አገልጋይ ካህናት በተገኙበት መልአከ ምሕረት አባ ምሕረት ዘውዴ በዝርዝር ለቀረቡላቸው ነጥቦች በሙሉ ጥፋተኛነታቸውን ስለአመኑና በፍጹም ትህትና ይቅርታ ስለጠየቁ ተይዞባቸው የነበረው ሥልጣነ ክህነት የተመለሰላቸው መሆኑን የሚገልጹ ደብዳቤዎችን ለመረጃ ምእመናን እንድታዩ እናሳስባለን።



ከሁሉ በላይ ይህን መልካም ሥራ በአባቶቻችን ላይ አድሮ የሠራ የሥርዓት ባለቤት የሆነ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስሙ የተመሰገነ ይሁን እያልን፤ ይህ ጉዳይ ከፍጻሜ እንዲደርስና ለቤተ ክርስቲያን ምእመናን አንድ የተስፋ ቀን እንዲታይ የደከሙትን ብጹዐን ሊቃነ ጳጳሳትንና የዳላስ ከተማ ካህናት አባቶቻችንን እግዚአብሔር ረዥም የአገልግሎት ዘመን ከጤና ጋር ይስጥልን በማለት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የጽርሐ አርያም ቅድስት ሥላስ ቤተክርስቲያን ምእመናን መልእክታችንን እናስተላልፋለን።

ለማንበብ እዚህ ይጫኑ Click here to read