መዝሙር (ኑ እንቅረብ) April 21, 2024 (First Mezmur)

በሥራዬ የት ይሆን መግቢያዬ
==============
 ኑ እንቅረብ መጠራት ሳይመጣ (2)
 ሥጋውን እንብላ (3) ደሙንም እንጠጣ

የቀራንዮ በግ የአምላክ ሥጋው
ተፈትቶልናል እንመገበው፤
እድፉን ኃጢአታችን በንስሐ አንጽተን
እንቀበል አምነን በልጅነታችን፤
መቅረብ ወደ ጌታ በእውነት የሚገባው
በስተ እርጅና አይደለም በወጣትነት ነው፤

 ኑ እንቅረብ መጠራት ሳይመጣ (2)
 ሥጋውን እንብላ (3) ደሙንም እንጠጣ

ጨረቃና ፀሐይ ደም የለበሱለት
ከዋክብት ከሰማይ የተነጠፉለት
ይኸው ተፈተተ እሳተ መለኮት

 በሥራዬ የት ይሆን መግቢያዬ (4)
 ጨነቀኝ ጠበበኝ ነፍስየ ወዲያልኝ (2)

ቅድስት እናታችን ቤተ ክርስቲያን
ትጋብዘናለች ሥጋና ደሙን
የአማኑኤል ሥጋ ይኸው ተዘጋጀ
ከግብዣው ተጠራን አዋጁ ታወጀ፤

 በሥራዬ የት ይሆን መግቢያዬ (4)
 ጨነቀኝ ጠበበኝ ነፍስየ ወዲያልኝ (2)

መጥቁ ተደወለ እንቅረብ በልልታ
በኋላ አይረባንም ዋይታና ጫጫታ፤
ይህች ዕድል ፈጥነን እንጠቀምባት
ዓለምን አልያዝንም ብዚ ልንቈይባት፤

 በሥራዬ የት ይሆን መግቢያዬ (4)
 ጨነቀኝ ጠበበኝ ነፍስየ ወዲያልኝ (2)

ካሁኑ ቅረቡ ታውጇል አዋጁ
የይኢለፍ ደብዳቤ ስንቅን አዘጋጁ፤
ይህ ዓለም ጠፊ ነው በሐብት አትመኩ
ብሏል አምላካችን ተስፋችሁን እንኩ፤

 በሥራዬ የት ይሆን መግቢያዬ (4)
 ጨነቀኝ ጠበበኝ ነፍስየ ወዲያልኝ (2)