መዝሙር (ኑ እንቅረብ) April 21, 2024 (First Mezmur)

በሥራዬ የት ይሆን መግቢያዬ
==============
 ኑ እንቅረብ መጠራት ሳይመጣ (2)
 ሥጋውን እንብላ (3) ደሙንም እንጠጣ

የቀራንዮ በግ የአምላክ ሥጋው
ተፈትቶልናል እንመገበው፤
እድፉን ኃጢአታችን በንስሐ አንጽተን
እንቀበል አምነን በልጅነታችን፤
መቅረብ ወደ ጌታ በእውነት የሚገባው
በስተ እርጅና አይደለም በወጣትነት ነው፤

መዝሙር (እያለፈ ነው ዘመኔ) April 14, 2024 (Second Mezmur)

እያለፈ ነው ዘመኔ ትዕዛዙን ሳልፈፅም ወየው ለኔ/2/
በጠራኝ ጊዜ ምን እላለሁ ና/ነይ/ ብሎ ወደ እኔ/2/

በወጣትነቴ ሳልሠራ እያየሁ አለፈኝ ብዙ አዝመራ/2/
ከእንግዲህ በመሥራት ጌታ ሆይ ልኑር ካንተ ጋራ/2/

የማስብበት በየዕለቱ ንፁህ ልብ ስጠኝ አቤቱ/2/
ከትዕዛዝህ ውጪ በመሆን እንዳልቀር በከንቱ/2/

እንደየሥራው ለመስጠት በግርማ መንግሥቱ ሲመጣ/2/
ማን ይሆን የሚቆም ከፊቱ ፈተናን የወጣ/2/

እንዳያስቷችሁ ተጠንቀቁ የተማራችሁ ከቃሉ/2/
ይመጣሉና በእርሱ ስም አምላክነን የሚሉ/2/

ትዕግስትን በመያዝ ሁላችሁ እስከመጨረሻው ጠንክሩ/2/
ያንጊዜ ይሆናል በሱ ዘንድ የማዳን ተግባሩ/2/

መዝሙር (በሥራዬ የት ይሆን መግቢያዬ) April 14, 2024 (First Mezmur)

በሥራዬ የት ይሆን መግቢያዬ
==============
 በሥራዬ የት ይሆን መግቢያዬ (4)
 ጨነቀኝ ጠበበኝ ነፍስየ ወዲያልኝ (2)

ተሸክሜ የኃጢአት ክምር (2)
ይመሻል ይነጋል በከንቱ ሰዞር (2)
ገሰገሰ ቀኑ ጨለመብኝ (2)
ዋ ለነፍሴ ምንም ስንቅ አልያዝኩኝ (2)

መዝሙር (ከካራን ውጡ) March 10, 2024 (Second Mezmur)

ከካራን ውጡ
==============
 ከካራን ውጡ ከነዓን ግቡ
 ወደ ጽድቅ ሕይወት ዛሬ ቅረቡ
 ካራን ጣኦት ነው የሚመለከው
 የአህዛብ ሀገር የሞት መንደር ነው /2/

እንደ አባታችን እንደ አብርሃም
ወገኖች ውጡ ከካራን ዓለም
የግፍ እንጀራ ይብቃችሁና
ከካራን ውጡ በአምላክ ጎዳና