Parent and Family Program Overview
ዓላማ እና እቅድ Objective and Plan
ጽርሃ አርያም ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስትያን የተረካቢ ትውልድ ወላጆችና ቤተስብ ክፍል፣ ቤተክርስትያናችን ውስጥ ሥራ እየሠሩ ካሉት አካላት አንዱ አካል ሲሆን፣ ከቤተክርስትያናችን ወላጆች መካከል የተውጣጡ በጎ ፈቃደኞች በየሳምንቱ እየተወያዩ በመመካከር ሥራዎችን እየሠራ ይገኛል፣
ለጊዜው በእቅድ ከያዛቸው ሥራዎች መካከል የሚከተሉት ይካተታሉ፧
* ቤተሰቦች በልጆችና ቤተሰብ ዙሪያ እንዲወያዩ መድረኮችን ያመቻቻል
* ወላጆች በልጆቻቸው ትምህርት ነክ ጥያቄዎቻቸውን ከሌሎች አባላት ጋር እንዲወያዩ እድል ይፈጥራል
* ወላጆች በልጆች አስተዳደግ ዙሪያ የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች ከባለሙያ ጋር ተማክረው እንዲፈቱ እድሎችን ያመቻቻል ባለሙያዎችንም እየጋበዘ ለወላጆች ትምህርት እንዲያካፍሉ ያደርጋል
* ወላጆች በቤተሰብ ዙሪያ ችግሮቻቸውን በግልፅነት እየተወያዩ መፍትሄ የሚያገኙበትን እድል ይፈጥራል
* የቤተክርስትያናችን አባላት ወደመንፈሳዊ አባቶቻቸው ይበልጥ እንዲቀራረቡና እንዲወያዩ እድል ይፈጥራል
* እንደያስፈላጊነቱና እንደወላጆች ፍላጎትና ጥያቄ ተከታታይ ትምህርቶችን ያዘጋጃል፣ ያወያያል
Parent and Family Program Contact
Contact:
Email us at:
This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.
Autism Awareness Event April 2023
What: Autism Awareness ስለኦቲዝም መረጃ ለመስጠጥ
Who: በParent and Family Program እና የምዕመናን ጤና ክፍል
When: April 30, 2023
Details: ለሁሉም ልጆች ለወላጆች የተዘጋጀ ሲሆን
Objective: አላማውም ልጆቻች የኦትስቲክ እድገት መዘግየት ሲያሳዩ በፍቅር እና በህብረት እንዲያድጉ ሁላችንም የበኩላችንን እገዛ እና ኃላፊነት እንድንወጣ ለማድረ ነው::