የኮሮና ቫይረስ ሥጋት፤ አራቱ ፍርሃትን የማስወገጃ መንገዶች
የኮሮና ቫይረስ ሥጋት፤ አራቱ ፍርሃትን የማስወገጃ መንገዶች
By John M. Grohol, Psy.D.
የኮሮና ቫይረስ በየቀኑ መዛመት በርካታ ሰዎች በሕይወታቸው ሊያደርስ የሚችለውን አደጋ እያሰቡ ለሥጋት እንዲዳረጉ እያደረገ ነው። እየደረሰ ባለው የጤና ቀውስ የሰዎች በሥጋት ውስጥ መሆን እንግዳ ነገር አይደለም። ይህም በመሆኑ በወረርሽኙ ምክንያት እየደረሰብን ላለው ፍርሃት በተመለከተ ከዚህ የሚከተሉትን አራት የማስወገጃ መንገዶች ማጤን አስፈላጊ ነው፤
1. አደጋውን አለማጋነን
አእምሮአችን የማይታወቅ ወይንም የሚያስፈራ ነገረን ለመቀበል የለመደ በመሆኑ የደረሰውን ነገር በማጋነን የአደጋ ስሜት በራሳችን ላይ ይፈጥርብናል። አብዛኛውን ጊዜ ትላልቅ እና አስፈሪ ክሥተቶች ቀልባችንን ይስቡናል። የተለመዱ የሚመስሉ ነገር ግን ለጤንነታችን አደጋ ሊያደርሱ የሚችሉትን ብዙ ትኩረት አንሰጣቸውም።
2. የተለመዱ ጤናማ ቅድመ ጥንቃቄዎችን መውሰድ
ሁለቱም ኢንፍሉዌንዛ እና ኮሮና ቫይረሶች የሚተላለፉት በየቀኑ በሚደረግ ንክኪ፣ ሳል እና ማስነጠስ ነው። እርስዎ ከታመሙ ወይንም ስሜቱ ከተሰማዎት ቤትዎ ውስጥ በመወሰን ብሎም ከቤት በመሥራት ያሳልፉ። ያልታመሙ ከሆነ ደግሞ የተለመዱ የንጽሕና አጠቃቀም ዘዴዎችን ከወትሮው በተለየ ይጠቀሙ።
ከንጽሕና አጠቃቀሞች ዋነኛው እጅን በየጊዜው በሳሙና በደንብ መታጠብ መሆኑ መዘንጋት የለበትም። ገበያም እንኳን ሄደን ቢሆን ቤት ስንገባ መታጠብ እንዳንረሳ። እየተመከረ ያለው 20 ሰከንድ በመሆኑ እርሱን ከግምት ውስት በማስገባት መታጠብ ያስፈልጋል። ምናልባት ውኃ እንደልብ የማያገኙበት አካባቢ ሊሆኑ ስለሚችሉ ምንጊዜም ቢሆን አነስ ባለ ብልቃጥ ሳኒታይዘር በመያዝ መጠቀሙ አስፈላጊ ነው። የተመጣጠነ ምግብ በመመገብ እና በቂ የሆነ እንቅልፍ በመተኛት ሰውነታችን በቀላሉ እንዳይጎዳ ማድረግ እንችላለን። የሙቀት መጠኑ ዝቅ በሚልበት በክረምት ወራትም ቢሆን በሰውነት እንቅስቃሴ መጠመድ ለጤናችን ጠቃሚ ነው።
3. መገናኛ አውታሮችን ከመጠን በላይ አንጠቀም
ስለ በሽታው በመገናኛ ብዙኃን የሚለቀቁ መረጃዎችን ሁሉ ሳንመረምር ወደ ውስጣችን ከማስገባት ይልቅ በተለይ የጤና ባለሙያዎች የሚሰጡትን ምክር በመቀበል ልንተገብር ይገባል። እነዚህ የጤና ባለሙያዎች እና ሌሎች ሳይንቲስቶች ያለ ማቋረጥ ጥናት በማካሄድ የበለጠ በሽታውን ለማወቅ ጥረት በማድረግ ላይ ናቸው። ከእነዚህም በተጨማሪ ዋነኛው የመረጃ ምንጫችን መሆን ያለበት የአሜሪካው የበሽታ መቆጣጠር እና መከላከል መሥሪያ ቤት (CDC) ነው። ይህ ማዕከል በየጊዜው ቋቱን በአዳዲስ መረጃዎች ስለሚሞላ ወቅታዊ የሆኑ እና ያልተዛቡ መረጃዎችን ማግኘት ይቻላል።
4. የከዚህ ቀደም ልምድ መጠቀም ምንም
ዓይነት ፈተና እና ሥጋት ቢገጥመን የሕይወት ልምዳችን ብዙ እንዳስተማረን ሁሉ ይህም ወረርሽኝ ከዚህ በፊት ተከሥተው እንዳለፉት በሽታዎች ሁሉ ጊዜውን ጠብቆ መጥፋቱ ስለማይቀር ከዚህ በፊት የተወሰዱትን የጥንቃቄ ዘዴዎች ልምድ መጠቀም እጅግ ጠቃሚ ነው። ምናልባት ለራስ ጊዜ ሰጥቶ ከራስ ጋር መነጋገር፣ በወሬ ላይ የተመሠረቱ ምንም ጭብጥ የሌላቸውን ሀሳቦች በማስረጃ በተደገፉ መረጃዎች መቀየር እና በጥንቃቄ መጓዝ፣ ወዘተ ናቸው። ከዚህም በተጨማሪ ከቤተሰቦች ወይንም ከታማኝ ጓደኞች ጋር ስለ ሥጋቱ መነጋገር በራስ ላይ ሊፈጠር የሚችለውን ሥጋት ይቀንሰዋል።
Faith Community Health Program of the Holy Trinity EOTC, Minneapolis MN የምእመናን ጤና አገልግሎት ክፍል This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.