የ ኮቪድ-19 ክትባት መረጃ

የ ቪኮድ 19 ክትባትን አሁን መከተብ የሚችለው ማነው?

እድሜያቸው 65 እና ከዛ በላይ የሆኑ የሚኔሶታ ነዋሪዎች
ከቅድመ መዋእለ ሕጻናት እስከ 12ኛ ክፍል አስተማሪዎች
መዋእለ ህጻናት ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች
አስተማሪዎችና የመዋእለ ሕጻናት ሰራተኞች - ቀጣሪዎቻችሁ የክትባት ተራችሁ ደርሶ እስኪያሳውቋችሁ ድረስ ቀጠሮ ለመያዝ እትሞክሩ።

-------
ቀጠሮ ለመያዝ መስፈርቱ ምንድነው?

ሐኪምዎ ጋር ቀጠሮ መያዝ ለጊዜው ወደ ሃኪምዎ እንዲደውሉ አይመከርም። ሃኪምዎ የጤና ጥበቃ ባወጣው መመሪያ ተራዎ ሲደርስ ያሳውቅዎታል።
በጊዜያዊ የማህረሰብ ክትባት ጣቢያ መከተብ ከፈለጉ ከ January 19 እኩለ ቀን ጀምሮ በስልክ ቀጠሮ መያዝ ይቻላል።

-------
በአሁኑ ጊዜ ቀጠሮ መያዝ የሚችሉ እነማን ናቸው?

እድሜያቸው 65 እና ከዛ በላይ የሆኑ የሚኔሶታ ነዋሪዎች ወይም
ከቅድመ መዋእለ ሕጻናት እስከ 12ኛ ክፍል አስተማሪዎች ወይም የመዋእለ ህጻናት ውስጥ የሚሰሩ ከሆነና በቀጣሪዎ በኩል ክትባት ለመውሰድ ተራ እንደደረሰዎና ጥሪ ከቀረበልዎ ብቻ።
የስልክ ቁጥር፦
612-426-7230 ወይም 833-431-2053

የመመዝገቢያ ድረ ገጽ -
mn.gov/vaccine
ዘጠኙ ጊዜያዊ የክትባት ጣቢያዎች በሚከተሉት ከተማዎች ይገኛሉ
Andover, Brooklyn Center, Fergus Falls, Marshall, Mountain Iron, North Mankato, Rochester, St. Cloud, and Thief River Falls.

------
በቀጠሮዎ ጊዜ ምን ማድረግ አለብዎ?

በቀጠርዎ ይገኙ ፤ ከ ፲፭ (15) ደቂቃ በላይ ቀድመው አይድረሱ
አስተማሪዎችና የመዋእለ ህጻናት ሰራተኞች ቀጠሮ ሲይዙ ያቀረቡትን የሥራ ፈቃድ ወይም የመስሪያ ቤት መታወቂያ ማቅረብ ይኖርባቸዋል
የደሞዝ ክፍያ ማረጋገጫ (pay stub) ማቅረብ ይቻላል
ከክትባቱ ከተሰጠዎት በኋሏ ለ፲፭ (15) ደቂቃ ለክትትል መቆየት ይኖርቦታል (የተለያየ አለርጂ ያለባቸው ደግሞ ለ፴ (30) ደቂቃ መቆየት ይኖርባቸዋል)
ክትባቱ ያለ ቀጠሮ አይሰጥም። ለበለጠ ማብራርያ የሚከተለውን ድረ ገጽ ይመልከቱ

Source: https://mn.gov/covid19/vaccine/find-vaccine/index.jsp
Faith Community Health Program of the Holy Trinity, EOTC, Minneapolis MN. Email: This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.