የአብነት ትምህርት ቤት እርዳታ ፕሮጀክት ማመልከቻ (2025)

Request for Proposal የአብነት ትምህርት ቤት እርዳታ ፕሮጀክት ማመልከቻ እዝህ ይጫኑ!
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የርእሰ አድባራት ጽርሐ አርያም ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል (Minneapolis, MN)

የቤተ ክርስቲያናችን የምግባረ ሠናይ(በጎ አድራጎት)እና ጤና አገልግሎት ክፍል በ፳፻፲፯ ዓ.ም. ስር በተያዘው እቅድ መሰረት የአብነት ትምህርት ቤቶችን ለመርዳት የ$2ሺ ዶላር በጀት በአጠቃላይ ጉባኤ መፈቀዱ ይታወሳል። ይህንን እቅድ ለመተግበር እንዲያስችል ምዕመናን እና ካህናት የተሟላ ሀሳብ/ፕሮጀክት (project proposal) እንዲያቀርቡ ክፍሉ በትህትና ይጠይቃል።

ክፍሉ ፕሮጀችት ማመልከቻዎችን ከሰበሰበ በኋላ፦
1. የቤተ ክርስቲያናችንን ራዕይ የሚያሟላውን (25%)፣
2. በስራ የሚውለውን ገንዘብ ተከታትሎ ሪፖርት ማድረግ የሚችል የአስፈጻሚ ብቃት ያለውን(25%)፣
3. ሰፊ ተደራሽነት ያለውን(25%) እና
4. የሚቀርፈውን ችግር እና ለአስተዳደር የሚውለውን የገንዘብ መጠን (25%) ግምት ውስጥ በማስገባት በኮሚቴ ተገምግሞ እና በሰበካ ጉባኤው ውሳኔ የተመደበውን በጀት ለተመረጠው ፕሮጀክት ያውላል።

በዚህም መሰረት ፕሮጀክት እንዲያቀርቡ እየጠየቅን፤ የሚከተሉትን ጥያቄዎች በቀጥታ የሚመልስ የተሟላ ማመልከቻ ከFebruary 2, 2024 (እኤአ) 11:59pm በፊት በዚህ ቅጽ እንዲያቀቡ በትህትና እንጠይቃለን።

Summer Spiritual Conference

Click to Register
Re'ese Adbarat Tserha Aryam Kidist Selassie Cathedral Sebkete Wengel Department will be holding a 3-day Summer Spiritual Conference from Friday, August 2nd to Sunday, August 4th for ages 13 and up. Please fill out this form to let us know which days you are able to attend so we can prepare accordingly.
እንደምን አላችሁ
በር/አ/ጽ/አ/ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የስብከተ ወንጌል ከ13ዓመት በላይ ለሆኑ ልጆች ለሦስት ቀናት በሚዘጋጀው መርሐ ግብር ላይ ለሚሳተፉ ልጆች የተዘጋጀ ፎርም። ለዝግጅት እንዲረዳ እባክዎ ይህንን ፎርም እንዲሞሉ ልጆችዎን ያድርጉልን።