መዝሙር (ሠርዓ ለነ) December 16, 2018

 ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለእረፍተዚአ (፪)
 ሠርዓለነ ሰንበተ ለእረፍተዚአ ኧኸ ሠርዓለነ ሰንበተ ለእረፍተዚአ
 ሠራልን ሰንበትን ለእረፍታችን (፪)
 ሠራልን ሰንበትን ለእረፍታችን ኧኸ ሠራልን ሰነበትን ለእረፍታችን

በስድስቱ ቀናት ሁሉን ነገር ሰርቶ
ሰባተኛው ቀን ለእረፍት አዘጋጅቶ
ለሁላችን ሰጠን ከቀናት ለይቶ
 ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለእረፍተዚአ ኧኸ ሠርዓለነ ሰንበተ ለእረፍተዚአ

እንድንሰባሰብ በቤተ መቅደሱ
በወንጌል ትምህርቱ አስረዳን ንጉሱ
ጨለማን አርቆ ብርሃንን ልበሱ
 ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለእረፍተዚአ ኧኸ ሠርዓለነ ሰንበተ ለእረፍተዚአ

ሞትን ድል አድርጎ እርሱ የተነሳባት
ተስፋ የሰጠችን የጌታችን ቀን ናት
ትንሳኤ እንዳለ የመሰከረባት
 ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለእረፍተዚአ ኧኸ ሠርዓለነ ሰንበተ ለእረፍተዚአ

ከዕለታት መርጦ አርፎባታልና
የሞትንም ስልጣን ሽሮባታል እና
ይቺ ቅድስት ዕለት ክብርት ናት ገናና
 ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለእረፍተዚአ ኧኸ ሠርዓለነ ሰንበተ ለእረፍተዚአ

 ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለእረፍተዚአ (፪)
 ሠርዓለነ ሰንበተ ለእረፍተዚአ ኧኸ ሠርዓለነ ሰንበተ ለእረፍተዚአ
 ሠራልን ሰንበትን ለእረፍታችን (፪)
 ሠራልን ሰንበትን ለእረፍታችን ኧኸ ሠራልን ሰነበትን ለእረፍታችን