የቅዱስ ሚካኤል ጽላት መቀበያ መዝሙሮች
1 እልል እልል ደስ ይበለን (2)
አጅበን መጣን ሚካኤልን እልል ብላችሁ ተቀበሉን
2 ሚካኤል አማልደን ከአምላካችን (2)
እንዳንጠፋ እንዳንሞት በነፍሳችን
አደራህን ቁምልን ከጎናችን
3 አትለይን (2) ድንግል ሆይ ድረሽልን (2)
ከዲይብሎስ እጅ አንቺ አድኝን ምህረት ከልጅሽ ለምኝልን
4 ውእቱ ሊቆሙ ለመላእክት ወመልአኮሙ ስሙ ሚካኤል
ልብሱ ዘመብረቅ ዓይኑ ዘርግብ ሊቀ መላእክት
ትርጉም ... የመላእክት አለቃቸው ቅዱስ ሚካኤል ልብሱ የመረቅ አይኑ የርግብ ነው
5 ንሴንሖ (2) ለእግዚአብሔር (2)
ስቡሐ ዘተሰብሐ (2)
እናመስግነው (2) እግዚአብሔርን
ምስጉን ነው የተመሰገነ (2)
6 ልዑል ውእቱ ልዑለ መንበር (4)
ሚካኤል (2) ልዑለ መንበር (2)
ትርጉም... ከፍ ከፍ ያለ ነው መቀመጫውም ከፍ ከፍ ያለ ነው ሚካኤል መቀመጫውም ከፍ ከፍ ያለ ነው
7 ለጌታዬ ለእግዚአብሔር ስላደረገልኝ ምን እከፍለዋለሁ(2)
ምስጋና ነው እንጂ (2) ሌላ ምን እላለሁ (4)
8 አይኑ ዘርግብ ልብሱ ዘመብረቅ (2)
ሚካኤል ሐመልማለ ወርቅ
9 ኩሎ ዘፈቀደ ገብረ እግዚአብሔር (2)
በሰማይኒ ወበምድርኒ በባሕርኒወበኩሉ ቀላያት (4)
ትርጉም እግዚአብሔር በሰማይና በምድር በባሕርም በፈሳሾችም ሁሉ የወደደውን አደረገ
10 ሚካኤል ሊቅ ልብሱ ዘመብረቅ (2)
ዓይኑ ዘርግብ ዓይኑ (4) ሚካኤል ሐመልማለ ወርቅ
ትርጉም ... አለቃ የሆነው ሚካኤል ልብሱ መብረቅ ነው ዓይኖቹም የርግብ ዓይን ይመስላሉ ሚካኤል የወርቅ ሐመልማል ነው
11 መንክር ግርማ ሐይለ ልዑል ፀለላ
አማን (2) መላእክት ይኬልልዋ (2)
መሚያስደንቅ ግርማ የልዑል ሐይል ጋረዳት
አማን (2) መላእክት አመሰገንኗት (2)
12 ማኀደረ መለኮት (2)
ማርያም እመብዙኃን(4)
ትርጉም... የመለኮት ማደርያ የሆንሽ እመቤታችን ማርያም የብዙኃን እናት ነሽ
13 ይዌድስዋ መላእክት (2) ለማርያም (2)
በውስተ ውሳጤ መንጦላዕት ወይብልዋ
በሐኪ ማርያም ሐዳስዩ ጣዕዋ
ትርጉም... በመጋረጃ ውስጥ መላእክት ማርያምን ያመሰግኗታል ስላምታ ይገባሻል ማርያም ስዲሲቷ እንቦሳ ይሏታል