የተረካቢ ትውልድ አውደ ጥናት ዘገባ Successor Generation Task Force Report
በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተረካቢ ትውልድ ለማፍራት እየተሰሩ ባሉት ጠንካራ መሰረቶች ላይ በመቆም የልጆችን ተረካቢነት በአንድ እርምጃ ወደፊት ለማሻገር እንዲረዳ የአጭር እና የረዥም ጊዜ እቅድ ማውጣት እንደሚገባ በመረዳት በ2022-2024 የሚያገለግለው የሰበካ ጉባኤ በ December 2021 አወደ ጥናት እንዲደረግና የ5 ዓመት እቅድ ግብአት እንዲቀርብ ኮሚቴ ማቋቋሙ ይታወሳል። አወደ ጥናቱ የሄደባቸውን መንገዶች እና ለሰበካ ጉባኤው ያቀረባቸውን መፍትሄ ሃሳቦች በሚቀጥለው ሊንክ በመጫን ይመልከቱ፡፡
ሰበካ ጉባኤው የቀረበውን ጥናት መሰረት በማድረግ እና ከቤተ ክርስቲያኒቱ ልዩ ልዩ ክፍሎች ጋር ተወያይቶ የልጆችን ተረካቢነት በአንድ እርምጃ ወደፊት ለማሻገር እንዲረዳ በሚመጣው አጠቃላይ ጉባኤው በJuly 31, 2022 ላይ ለውይይት እና ለውሳኔ የሚያቀርባቸው ሃሳቦች ስለሚኖሩ አባላቱም በተባለው ቀን በስብሰባው ላይ እንዲገኙ በድጋሚ የአክብሮት ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡ ከቤተ ክርስቲያናችን አራቱ የትኩረት አቅጣጫዎቻች መሃከል አንዱ የሆነውን ጠንካራ ተረካቢ ትውልድ የማፍራት አላማ በአንድ እርምጃ ለማሻገር
1. ከእግዚአብሔር እርዳታ ጋር
2. ጠንካራ በሆኑ የቤተ ክርስቲያናችን ክፍሎች (ማኅበረ ካህናት፣ የቤዛ ኩሉ ሰንበት ትምህርት ቤት፣ መምህራን፣ የበጎ አድራጎት አገልጋዮች፣ ወዘተ) በመታገዝ
3. ወላጆች እና የቤተ ክርስቲያን አባላት ትልቅ ሚና ስለሚጫወቱ፤
በህብረት የሚቀጥለውን እርምጃ እንድንራመድ ቤተ ክርስቲያን ታላቅ ጥሪ ታስተላልፋለች፡፡