ኢዛናና የነገረ ክርስቶስ እምነቱ
- Details
- Created on Tuesday, 08 December 2015 05:40
- Written by ዳንኤል ክብረት
በኢትዮጵያ ታሪክ ክርስትናውን በይፋ ያወጀው ንጉሥ ኢዛና ነው፡፡ ኢዛና ክርስትናውን በይፋ በማወጅ ብቻ ሳይሆን በድንጋይ ላይ የጦርነት ታሪኩን መዝግቦ በማቆየትም ይታወቃል፡፡ ምንም እንኳን የታሪክ ሊቃውንት በኢትዮጵያ ክርስትና የተሰበከበትን ጊዜ ከ4ኛው መክዘ ቢጀምሩትም የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ግን ከጃንደረባው መጠመቅ አንሥተው ይቆጥሩታል፡፡
በኢትዮጵያ የክርስትና ትምህርት ቀደም ብሎ የተጀመረ ቢሆንም ኦፊሴላዊ እምነት የሆነውና መሠረት ባለው ጽኑ ዐለት ላይ የተተከለው ግን በ4ኛው መክዘ የፍሬምናጦስን ስብከትና
...Read more: ኢዛናና የነገረ ክርስቶስ እምነቱ
ላስቬጋስ - ጎንደር
- Details
- Created on Friday, 30 October 2015 22:05
- Written by ዳንኤል ክብረት
አሜሪካ ስመጣ ሦስት ቦታ ያለው የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ይማርከኛል፡፡ ላስቬጋስ ኪዳነ ምሕረትና ቅዱስ ሚካኤል፣ ዴንቨር መድኃኔዓለምና ሚነሶታ ቅድስት ሥላሴ፡፡ ሃይማኖታቸውን የተረዱ፣ ለአገልግሎት የተጉና ምራቃቸውን የዋጡ ክርስቲያኖች ያሉበት ቦታ፡፡ ወደነዚህ ቦታዎች ስመጣ ከማስተምረው የምማረው ይበልጣል፡፡ በአስቸጋሪው የአሜሪካ ኑሮና ፈተና ውስጥ የቤተ ክርስቲያን እምነትን፣ ሥርዓትና ትውፊትን ጠብቆ፣ ጊዜን
...ስለ ገና በዓል እና ጾም አንዳንድ ጥያቄዎች
- Details
- Created on Wednesday, 31 December 2014 05:54
- Written by ዳንኤል ክብረት
(በብዙ አንባቢያን ጥያቄ በድጋሚ የታተመ)
<!--[if gte mso 10]> /* Style Definitions */ table.MsoNormalTable {mso-style-name:"Table Normal"; mso-tstyle-rowband-size:0; mso-tstyle-colband-size:0; mso-style-noshow:yes; mso-style-priority:99; mso-style-qformat:yes; mso-style-parent:""; mso-padding-alt:0in...
አርሴማ
- Details
- Created on Wednesday, 08 October 2014 07:12
- Written by ዳንኤል ክብረት
ዐጽሟ ያረፈበት አርመን የሚገኘው ቤተ ክርስቲያን |
ቅድስት አርሴማ በ290 ዓም በአርመን በሰማዕትነት ያረፈች ወጣት ክርስቲያን ሰማዕት ናት፡፡ ትውልዷ ሮም ሲሆን ሰማዕትነት የተቀበለችው አርመን ነው፡፡ እኛ አርሴማ ስንላት እነርሱ Saint Hripsime ይሏታል፡፡ ታሪኳን የፈለገ ሰው በዚህ ስሟ ጎጉል ላይ ቢፈልግ በቀላሉ ያገኘዋል፡፡ጥንታውያን አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ መስከረም 29 ቀን ወይም ኦክቶበር 9 ሰማዕትነት የተቀበለችበትን ቀን ያከብራሉ፡፡ የመጀመሪያው ቤተ ክርስቲያን በስሟ የተሠራውም አርመን ኤችሚዚን ውስጥ በ395 ዓም ነው፡፡ ይህ የአርሴማ
...ፍቅር፣ ቁልፍና ድልድይ
- Details
- Created on Tuesday, 30 September 2014 21:15
- Written by ዳንኤል ክብረት
በሜልበርን እምብርት እየተሽረከርን በያራ ወንዝ ዳርቻ ስንዋብ ወደ ሌላ አቅጣጫ የመሻገሪያ የእግረኞች ድልድይ ላይ ደረስን፡፡ የያራ ወንዝ ዓባይን በሰኔ መስሏል፡፡ እዚህ ወንዝ ዳር ነው የዛሬ 179 ዓም እኤአ 1835 የሜልበርን ከተማ የተቆረቆረችው፡፡ ከ242 ኪሎ ሜትር በላይ ይጓዛል ያራ ወንዝ፡፡ የመሻገሪያው ድልድይ ወንዙ መካከል በአንዲት አነስተኛ ጀልባ በምትመስል ኮንክሪት መሬት ላይ ቆሟል፡፡ ሀገሬዎቹ ደሴት ብርቃቸው ነው መሰለኝ ‹ፖኒ ፊሽ ደሴት› ይሏታል፡፡ መቼም ፈረንጅ ትንሽን ነገር ታላቅ በማድረግ የሚተካከለው
...ጨረቃና ጨለማ
- Details
- Created on Thursday, 25 September 2014 08:16
- Written by ዳንኤል ክብረት
በ1768 እኤአ የተጻፈና ጥንታዊ አባባሎችን የያዘ አንድ ‹‹AN ETHIOPIAN SAGA›› የተሰኘ መጽሐፍ ሳነብ ‹‹ጨረቃዋን እያየህ፣ ጨለማውን ግን እየተጠነቀቅ ተጓዝ›› የሚል ጥንታዊ ብሂል አየሁ፡፡ ይህ ለጥንቱ መንገደኛ የተሰጠ የጠቢብ ምክር ነው፡፡
የጥንቱ ተጓዥ ጤፍ በምታስለቅመው ጨረቃ መጓዙ ሁለት ጥቅሞች ይሰጡት ነበር፡፡ በአንድ በኩል በቀን ከሚገጥመው ሙቀትና የፀሐይ ቃጠሎ ይድናል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ መንገዱን በሩቁ ስለማያየው ‹ለካ ገና ብዙ መንገድ ይቀረኛል› እያለ መንፈሱ እንዳይደክም ያደርገዋል፡፡
በተለይም
...ሰነቦ
- Details
- Created on Friday, 12 September 2014 08:59
- Written by ዳንኤል ክብረት
ነሐሴ 23 ቀን 2006 ዓም ማለዳ 10 ሰዓት ነው ከዕንቅልፌ የነቃሁት፡፡ ዲያቆን ሙሉቀን ብርሃን ከጎንደር፣ ሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ ከፍኖተ ሰላም መንገድ ላይ ይጠብቁኛል፡፡ ለመንገዱ የሚሆነውን የቱሪስት መኪና ያዘጋጀልኝ የኦሪጂንስ ኢትዮጵያ አስጎብኝ ድርጅትባለቤት ሳምሶን ተሾመ ነው፡፡ ክብር ይስጥልኝ ብያለሁ፡፡ የምተርክላችሁን ታሪክ ስትጨርሱ ትመርቁታላችሁ ብየ አምናለሁ፡፡ የምጓዘው አቡነ ተክለ ሃይማኖትን በተመለከተ ለማደርገው ጥናት ተጨማሪ መረጃዎችን ፍለጋ ነው፡፡
ሾፌራችን ደምስ ይባላል፡፡ ዝምታና ትኩረት
...ጳጉሜን - አምስት፣ ስድስት፣ ሰባት
- Details
- Created on Friday, 05 September 2014 07:39
- Written by ዳንኤል ክብረት
በጽሑፉ ውስጥ በግእዝ ቁጥሮች በቅንፍ ውስጥ የተጻፉት ሐሳቡን እንዲወክሉ ብቻ ነው፡፡ በኋላ (ቁጥር ፭ ተመልከት ቢል ያንን ሐሳብ መልሶ ለማየት እንዲረዳ ነው፡፡
የኢትዮጵያን የዘመን አቆጣጠር ለየት ከሚያደርጉት ነገሮች አንዱ ጳጉሜ የምትባል አሥራ ሦስተኛ ወር ስላለችን ነው፡፡ የቤት ኪራይና የወር ደመወዝ የማንከፍልባትና የማንቀበልባት፤ መብራትና ውኃ ግን ከነሐሴ ወር ጋር ጨምረው የሚያስከፍሉባት፤ ሲሻት አምስት፣ ሲያስፈልጋት ስድስት፣ ስትፈልግ ደግሞ ሰባት የምትሆን ወር ናት፡፡ እንዲያውም ከአሥራ ሁለቱ የኢ
...ሕግና ሥርዓት - በሐበሻ አሜሪካ
- Details
- Created on Friday, 15 August 2014 09:11
- Written by ዳንኤል ክብረት
አሜሪካ ውስጥ በተለያዩ ከተሞች በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ስዘዋወር ከአስተባባሪዎቹ የምሰማው ተመሳሳይ ሮሮ አለ፡፡ ብዙዎቹ አብያተ ክርስቲያናት የራሳቸው ሕንጻ እስኪያገኙ ድረስ ከሌሎች አብያተ ክርስቲያናት ተከራይተው ይገለገላሉ፡፡ የራሳቸው ሕንጸ ያላቸውም ቢሆኑ ከአሜሪካዊው ማኅበረሰብ ጋር ይጎራበታሉ፡፡ በሰንበት ቅዳሴና የንግሥ በዓላት በሚከበሩባቸው ቀናት በመኪና ማቆሚያ፣ በድምጽ፣ በአካባቢው በብዛት በመገኘትና በጽዳት ጉዳዮች አብያተ ክርስቲያናቱ ካሉባቸው መንደሮች ነዋሪዎች ጋር ይገናኛሉ፡፡
እነዚህ ግንኙነቶች ግን ብዙ
ንሥር (ክፍል ሁለት)
- Details
- Created on Thursday, 07 August 2014 05:55
- Written by ዳንኤል ክብረት
ንሥር ሳይፈትን አያምንም፤ አይተማመንምም፡፡ ሴቷ ንሥር ባል ማግባት ስትፈልግ አንድ እንጨት ታነሣና ወንዱ እየተከተላት ወደ ላይ ትመጥቃለች፡፡ እስከ ሰማይ ጥግ ከደረሰች በኋላም ያንን እንጨት ትለቀዋለች፡፡ ያን ጊዜ ወንዱ እንጨቱ መሬት ከመድረሱ በፊት በፍጥነት በመወርወር መያዝና ለሴቷ መልሶ ማምጣት ይጠበቅበታል፡፡ ሴቷም እንጨቱን ተቀብላ እንደገና ወደ ቀጣዩ ከፍታ ትመጥቅና እንጨቱን መልሳ ትጥለዋለች፡፡ አሁንም ወንዱ ንሥር ከእንጨቱ የውድቀት ፍጥነት ቀድሞ ያንን እንጨት በመያዝ ለሴቷ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡ እንዲህ ያለው ፈተና ወንዱን ለሰዓታት ያህል ይጠብቃዋል፡፡ ከፍታው እየጨመረ፣ እንጨቱም ይበልጥ እየተወረወረ ይሄዳል፡፡ ሴቷ ንሥር ወንዱ ንሥር ፈጣንና የተወረወረለትን ለመያዝ ያለውን ቆራጥነት እስክታረጋግጥ ድረስ ፈተናው ይቀጥላል፡፡ በመጨረሻም ቆራጥና ፈጣን፣ ማንኛውም ችግር የማይበግረው መሆኑን ስታረጋግጥ ባልነቱን ትፈቅድለታለች፡፡
ንሥር
- Details
- Created on Wednesday, 06 August 2014 00:00
- Written by ዳንኤል ክብረት
ንሥር እጅግ ግዙፍ ከሆኑ የአዕዋፍ ዝርያዎች አንዱ ነው፡፡ ክብደቱ እስከ 6.7 ኪሎ ሲደርስ ቁመቱ ደግሞ ከአንዱ ክንፉ ጫፍ እስከ ሌላው ጫፍ ድረስ 2 ሜትር ተኩል ይደርሳል፡፡ በዓለም ላይ እስከ ስድሳ የሚደርሱ የንሥር ዝርያዎች ይገኛሉ፡፡
በኢትዮጵያ ጥንታዊ ሥነ ጽሑፍ ውስጥ ንሥር የትንሣኤ ሙታን፣ አርቆ የማሰብ፣ ወደ ላይ የመምጠቅና የመነጠቅ፣ የጥበቃና የምናኔ ተምሳሌት ሆኖ ተገልጧል፡፡ ግብጻውያን ደግሞ የተቀበሩ ሰዎችን አጋንንት እንዳይደርሱባቸው በመቃብራቸው በር በድንጋይ ላይ የንሥርን ምስል ያስቀርጹ ነበር፡፡ ይጠብቃቸዋል ብለው፡፡ በግሪክ አፈ ታሪክ የአማልክት ንጉሥ የሚባለው ዜውስ በንሥር የሚመሰል ነበር፡፡ ጥንታውያን የአሜሪካ ሕዝቦች እጅግ ለሚያከብሩት የሌላ ወገን ሰው የንሥርን ላባ በመስጠት ክብራቸውንና ፍቅራቸውን ይገልጡ ነበር፡፡ ሞቼ የተባሉት የፔሩ ሕዝቦችም ንሥርን ያመልኩት ነበር ይባላል፡፡
ሃይማኖታውያን ያልሆኑ የግእዝ ጽሑፎች (ግንቦት 2006 ዓም አኩስም ትግራይ)
- Details
- Created on Thursday, 29 May 2014 04:35
- Written by ዳንኤል ክብረት
ክፍል አንድ
1.1 አጠቃላይ የግእዝ ሥነ ጽሑፋዊ ሀብት
የግእዝ ቋንቋ ከሁለት ሺ ዓመታት በላይ ጊዜ ያስቆጠረ የሥነ ጽሑፍ ሀብት ያለው ቋንቋ ነው፡፡ እስካሁን የተገኙ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የግእዝ ሥነ ጽሑፍ በተጻፉበት ቁስ በሦስት መልኮች ቀርበዋል፡፡ በድንጋይ ላይ፣ በብራና ላይና በወረቀት ላይ፡፡
- የድንጋይ ላይ ጽሑፎች፡- በድንጋይ ላይ የተጻፉት የግእዝ ሥነ ጽሑፎች በአኩስም አካባቢ የተገኙትንና የነገሥታቱን የጦርነት ታሪኮችንና ሌሎች ዘገባዎችን የያዙትን ጽሑፎች ይመለከታል፡፡
ሀገር አቀፍ የግእዝ ዐውደ ጥናት
- Details
- Created on Tuesday, 27 May 2014 06:44
- Written by ዳንኤል ክብረት
ከግንቦት 9 እስከ 11 ቀን ድረስ በትግራይ ክልል አኩስም ከተማ ‹ሀገር አቀፍ የግእዝ ዐውደ ጥናት ተደርጎ ነበር፡፡ ይህ በዓይነቱ በሀገር ዐቀፍ ደረጃ ሲዘጋጅ የመጀመሪያ የሆነው ዐውደ ጥናት የትግራይ ክልል ባሕል ቱሪዝም ኤጀንሲ ከፌዴራል ባሕል ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመሆን ያዘጋጀው ነበር፡፡
የክልሉ ባሕል ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊዎች እንደገለጡት ይህ ዐውደ ጥናት በትግራይ ክልል ደረጃ ሲከናወን ለስድስተኛ ጊዜ ነው፡፡ የዘንድሮውን ልዩ የሚያደርገው በሀገር አቀፍ ደረጃ መከናወኑ ነው፡፡ በዚህ ጉባኤ ላይ ከጎንደርና ከሌሎችም አካባቢዎች
...