መዝሙር (እግዚአብሔር ሆይ እወድሃለሁ) March 3, 2019
እግዚአብሔር ሆይ እወድሃለሁ
ስለ ስምህ እቃጠላለው
ፍቅርህ እኔን ይመስጠኛል
እንደ እግዝአብሔር ከየት ይገኛል(፪)
አለም ሁሉ በጠላኝ ጊዜ
ስንገላታ ይዞኝ ትካዜ
አንተ ከኔ አልተለየህም
እግዝአብሔር ሆይ ወደር የለህም (፪)
እግዚአብሔር ሆይ እወድሃለሁ
ስለ ስምህ እቃጠላለው
ፍቅርህ እኔን ይመስጠኛል
እንደ እግዝአብሔር ከየት ይገኛል(፪)
ሳዖል እኔን ሲያሳድደኝ
ጎልያድም ሲዝትብኝ
ግርማ ሆነህ ከፊቴ የቆምክ
እግዝአብሔር ሆይ ስምህ ይባረክ (፪)
እግዚአብሔር ሆይ እወድሃለሁ
ስለ ስምህ እቃጠላለው
ፍቅርህ እኔን ይመስጠኛል
እንደ እግዝአብሔር ከየት ይገኛል(፪)
ሞቷዋል ብለው ቀብረውኝ ሰዎች
ምስኪን ሁኜ ሳይኖረኝ አንዳች
ከመቃብር ቆፍሮ አወጣኝ
አይዞህ ብሎ አምላክ አፅናናኝ (፪)
እግዚአብሔር ሆይ እወድሃለሁ
ስለ ስምህ እቃጠላለው
ፍቅርህ እኔን ይመስጠኛል
እንደ እግዝአብሔር ከየት ይገኛል(፪)
ሐሳብህን በእግዝአብሔር ላይ ጣል
ለዘለዓለም ያበራልሃል
ታማኝ አባትህ እርሱ ነውና
ሰላም በረከት የእርሱ ነውና
እግዚአብሔር ሆይ እወድሃለሁ
ስለ ስምህ እቃጠላለው
ፍቅርህ እኔን ይመስጠኛል
እንደ እግዝአብሔር ከየት ይገኛል(፪)