መዝሙር (አማን በአማን) March 10, 2019
አማን በአማን /፬/
አማኑኤል ተመስገን ለዚህ ፍቅርህ ምን እንበል /፪/
ድብቁን ኃጢአት አንተ ብትገልጸው
ይቅር ብለኸኝ ባትሸፋፍነው
እንደ ሰው በቀል ቢኖርህ ጌታ
ለእኔ ኃጢአትስ የለውም ቦታ
አማኑኤል ተመስገን ለዚህ ፍቅርህ ምን እንበል /፪/
በየደቂቃው ኃጢአት ስሠራ
ስሰርቅ ስበድል አንተን ሳልፈራ
አንተ ግን ፊትህ ምንም ቢቀየም
በቁጣህ በትር አልገረፍከኝም
አማኑኤል ተመስገን ለዚህ ፍቅርህ ምን እንበል /፪/
ምሕረትን ልከህ አድነኝ ዛሬ
ታክቶኛልና በኃጢአት መኖሬ
ዓለም በኃጢአት እየሳበችኝ
በጽድቅህ ደስታ መኖር አቃተኝ
አማኑኤል ተመስገን ለዚህ ፍቅርህ ምን እንበል /፪/
የኃጢአት ጉዞ ጣፋጭ ቢመስልም
ውጤቱ መርሮ ፍጹም አይጥምም
እንደ በደሌ ስላልከፈልከኝ
ተመስገን እንጂ ሌላ ምን አለኝ
አማኑኤል ተመስገን ለዚህ ፍቅርህ ምን እንበል /፪/