መዝሙር (እመ አምላክ) March 17, 2019



 እመ አምላክ /፪/ አስቢኝ በሠርክ

ኀዘኔ ጭንቀቴ በጣም በዛብኝ
ከልጅሽ አስታርቂኝ አንቺው አማልጂኝ
ከመንበሩ ቆመሽ ንገሪው ለልጅሽ
እናቱ ነሽና እርሱ አያሳፍርሽ

 እመ አምላክ /፪/ አስቢኝ በሠርክ

እኔ ኃጢአተኛው በደሌን አውቃለሁ
ምርኩዜ ነሽና እከተልሻለሁ
መንገዱ ጠፍቶብኝ የጽድቁ ጎዳና
መብራቱን አብሪልኝ እመጣለሁና
 እመ አምላክ /፪/ አስቢኝ በሠርክ

መመገብ ይቅርብኝ አልራብምና
ስምሽን ስጠራ እጠግባለሁና
አበው ሊቃውንቱ በአንቺ ይመካሉ
እመ አምላክ እያሉ ስምሽን ይጠራሉ

 እመ አምላክ /፪/ አስቢኝ በሠርክ

ከገሃነም አውጪኝ ከዚያ ነበልባል
ከሲኦል ወድቄ እንዳልቃጠል
ያ የስቃይ ሀገር ባህሩ ያሰጥመኛል
አንቺ ከለመንሽው ልጅሽ ያዝንልኛል
 እመ አምላክ /፪/ አስቢኝ በሠርክ

እኔስ እፈራለሁ ምግባሬን ሳየው
ደካማው እምነቴ እየለየኝ ነው
አልረሳሽም ድንግል እማጸንሻለሁ
አማላጅነትሽ መድኅን ነው አውቃለሁ