መዝሙር (እንደ በደሌማ) March 24, 2019



እንደ በደሌማ ከሆነ ቅጣቴ
አያልቅም ተነግሮ ብዙ ነው ጥፋቴ
እንጃልኝ ፈራሁኝ አዬ ሰውነቴ(፪)

እመለሳለሁኝ እያልኩኝ ጠዋት ማታ
ዘመኔን ጨረስኩት ሳስብ ሳመነታ
ምን እመልስ ይሆን የተጠራሁ ለታ/፪/

በላዬ ሲያንዣብብ ሞት እጁን ዘርግቶ
ሥጋዬን ሲውጠው መቃብር ተከፍቶ
የነፍሴ ማረፊያ ወደየት ይሆን ከቶ/፪/

ይቅር ባይ ነህና የበደሉህን
አቤቱ ጌታ ሆይ እኔን ባሪያህን
ይቅር በለኝና ልየው ፊትህን /፪/