መዝሙር (ጌታ ሆይ ውለታህ) April 7, 2019



 ጌታ ሆይ ውለታህ ተአምርህ ድንቅ ነው  አምላካዊ ቃልህ ስምህ ሕይወቴ ነው

በሐዋርያት አድረህ ብዙ መክረኸኛል
ስለ ኃጢአቴ ሞተህ ሕይወት ሰጥተኸኛል
ጌታ ሆይ ውለታህ ተአምርህ ድንቅ ነው
አምላካዊ ቃልህ ስምህ ሕይወቴ ነው

 ጌታ ሆይ ውለታህ ተአምርህ ድንቅ ነው  አምላካዊ ቃልህ ስምህ ሕይወቴ ነው

ከሀዘኔ ፈጥነህ ደርሰህ አረጋጋኸኝ
አይዞህ ልጄ ብለህ ስወድቅ ያነሳኸኝ
ከማይጠፋው እሳት ከሞት ያወጣኸኝ
ለአንተ የምከፍለው ምን ስጦታ አለኝ

 ጌታ ሆይ ውለታህ ተአምርህ ድንቅ ነው  አምላካዊ ቃልህ ስምህ ሕይወቴ ነው

እውነተኛ ረዳት አምላኬ አንተ ነህ
ጌታ ሆይ ከእናት ልጅ እጅግ ትበልጣለህ
መታመን በአንተ ነው ደግሞም መመካት
ወቅት የማይለውጥህ የማታውቅ ወረት

 ጌታ ሆይ ውለታህ ተአምርህ ድንቅ ነው  አምላካዊ ቃልህ ስምህ ሕይወቴ ነው

ስምህ ምግቤ ሆኖ ስጠራህ እጠግባለሁ
ፍቅርህን ለብሼ ፍጹም እረካለሁ
በሰማይ በምድር በነፍስም በሥጋ
በአንተ እመካለሁ አልፋና ዖሜጋ