መዝሙር (አቤት የዚያን ጊዜ) March 31, 2019
አቤት የዚያን ጊዜ ክርስቶስ ሲመጣ /፪/
ትንሹም ትልቁም /፫/ መድረሻውን ሲያጣ
ከምሥራቅ ከምዕራብ ከሰሜን ከደቡብ /፪/
ነፋሳት ሲላኩ /3/ መዓትን ለማዝነብ
ሰማይና ምድር በአንድ ሲዋሐዱ /፪/
የት ይሆን መድረሻው /፫/ የት ይሆን መንገዱ
አቤት የዚያን ጊዜ ክርስቶስ ሲመጣ /፪/
ትንሹም ትልቁም /፫/ መድረሻውን ሲያጣ
ፃድቃን በቀኝ በኩል ኃጥአን በግራ /፪/
ሲነፋ መለከት /፫/ ሲመታ እንዚራ
ምድር ቀውጢ ስትሆን አፅም ሲሰበሰብ /፪/
ኀፍረት ይይዘዋል /፫/ ሰው ለፍርድ ሲቀርብ
አቤት የዚያን ጊዜ ክርስቶስ ሲመጣ /፪/
ትንሹም ትልቁም /፫/ መድረሻውን ሲያጣ
ጩኸት ሲበረታ የማይጠቅም ለቅሶ /፪/
እንደ ቁራ ጠቊሮ /፫/ ጽልመትን ተላብሶ
ገነትን ሲያገኙ ፃድቃን በሥራቸው /፪/
ኃጥአን ወደ ሲዖል /፫/ ተፈረደባቸው
አቤት የዚያን ጊዜ ክርስቶስ ሲመጣ /፪/
ትንሹም ትልቁም /፫/ መድረሻውን ሲያጣ