መዝሙር (ንጹም ጾም) February 11, 2018
ንጹም ጾመ ወናፍቅር ቢጸነ(፪)
ወንትፋቀር (፬) ንትፋቀር በበይናቲነ (፪)
ትርጉም….
ጾምን እንጹም ወንድሞቻንን እንውደድ፤ እንስ በርሳችንም እንዋደድ
ንጹም ጾመ ወናፍቅር ቢጸነ(፪)
ወንትፋቀር (፬) ንትፋቀር በበይናቲነ (፪)
ትርጉም….
ጾምን እንጹም ወንድሞቻንን እንውደድ፤ እንስ በርሳችንም እንዋደድ
አቤቱ በመንግስትህ አስበኝ (፪)
በበደሌ ብዛት /፪/ አይተህ አትጣለኝ
ሳስበው በደሌ ብዙ ነው /፪/
ሆዴ ባባ አፈሳለሁ እንባ/፪/
አዝ..
እርቃኔን ቀረሁኝ ተገፈፈ ልብሴ
መድረሻው ጠፋብኝ ተጨነቀች ነፍሴ
የብርሃን ጸዳሌ ከዓይኔ ተገፈፈ
ከፊትህ ለመቆም ጉልበቴ ታጠፈ
አዝ
አልቻልኩም ደግፈኝ እንድቆም /፪/
ለገነት የበቃህ ያን ቀማኛ ሽፍታ
እኔንም ደግፈኝ አውጣኝ ከዛን ለታ
አዝ
ሳስበው በደሌ ብዙ ነው(፪)
በጨለማ ነፍሴን በላት ውድማ /፪/
ሆዴ ባባ አፈሳለሁ እንባ (፪)
ትምክሕተ ዘመድነ /፪/ ማርያም እምነ
ማርያም ትምክሕተ ዘመድነ
የድኅነታችን ዓርማ የነፃነታችን
የሕይወት መሠረት ነሽ ድንግል እናታችን
አንቺን ለእኛ ዘርን ባያስቀር
እንደ ጥንቱ እንደ ሰዶም ምድር
ሁላችን በጠፋን ነበር
አዝ
ሐዋርያት አበው እንዳስተማሩን
ስለ ሰው ልጅ ድኅነት አምላክ ሰው መሆኑን
በስሙ የተጠራን እኛ እናምናለን
መለኮት ከሥጋ ተዋሕዷል ብለን
አንቺ የወይን ሐረግ
አንቺ የወይን ሐረግ ድንግል ልምላሜሽ የበዛ /፪/
ምግብ ሆኖ /፪/ ተሰጠን ፍሬሽ ለእኛ ቤዛ /፪/