መዝሙር (አዳምን ለማዳን) October 21, 2018


 ሰአሊ ለነ ማርያም
አዳምን ለማዳን ሰው የሆነው ወዶ
ስደትን ጀመረ በፍቅር ተዋርዶ
 ሰአሊ ለነ ማርያም
ብርድ በጸናበት በክረምት ወራት
ልጅሽን ታቅፈሽ ተነሳሽ ስደት
 ሰአሊ ለነ ማርያም
የሄሮድስ ጭፍሮች ከሐገር ሲያሳድዱሽ
ልጅሽን ታቅፈሽ እንባሽን አፈሰስሽ
 ሰአሊ ለነ ማርያም
ለምኝልን ማርያም ከአንድዬ ከልጅሽ ከመድኃኔ ዓለም
አንቺ ብቻ እኮ ነሽ ለእግዚአብሔር ፍጹም
 ሰአሊ ለነ ማርያም
ሰሎሜና ዮሴፍን ዘመድ ኣግኝተሽ
ልጅሽን ታቅፈሽ ስደትን ጀመርሽ
 ሰአሊ ለነ ማርያም
ፍጡራን በሙሉ ከቤታቸው ሆነው
አንቺ መሰደድሽ ኧረ ለምንድን ነው
 ሰአሊ ለነ ማርያም
ከረሃብ ጋር ጸሐይ አንዴት አረገሽ
ሀዘንሽን ልካፈል ስለሆንኩ ልጅሽ
 ሰአሊ ለነ ማርያም
አንድ ፍሬ ሕጻን ትንሽ ብላቴና
እንዴት አቋረጥሽው በረሃውን ሲና
 ሰአሊ ለነ ማርያም
ምን አለች ኮቲባ ያልታደለች ፍጡር ጌታዋን ታቅፈሽ ስትዞሪ መንደር  ሰአሊ ለነ ማርያም
አንቺን የመሰለች አንዲህ መቸገሩ ብሆትኚ ነው ክፉ ያዞረሽ ባገሩ  ሰአሊ ለነ ማርያም
ብላ ተናገረች ምስጢሩ ሳይገባት ውሃን ለመዘከር ልቧ ጨክኖባት  ሰአሊ ለነ ማርያም
ክፉም አልመለስሽ እንባሽን አፈሰስሽ ለውሻ እራርተሽ ውሃን የተዘከርሽ  ሰአሊ ለነ ማርያም
ድንገት ወንበዴዎች ደርሰው ሲይዙሽ ከሰሎሜ ወስደሽ ልጅሽን ታቀፍሽ  ሰአሊ ለነ ማርያም
የሌሊት ቁርና የቀን ሀሩርን የተቀበልኩብህ ላላድን ነውን  ሰአሊ ለነ ማርያም
እያልሽ አለቀስሽ ምርር ብለሽ ፊቱ ላይ ወረደ የሐዘን እንባሽ  ሰአሊ ለነ ማርያም
ልጄን ሲገድሉብኝ ከማይ በህይወቴ እኔን ያስቀድመኝ ይቅረብልኝ ሞቴ  ሰአሊ ለነ ማርያም
ያበሰረኝ መልአክ ትወልጂያለሽ ያለኝ ዛሬ በስደቴ ይምጣና ያጽጽናናኝ  ሰአሊ ለነ ማርያም
ብለሽ ማልቀስሽን ባስታወስኩኝ ጊዜ ልቤ ይቃጠላል በሀዘን በትካዜ  ሰአሊ ለነ ማርያም
ከዘመድ መለየት ከሀገር መውጣት እንዴት ያሳዝናል የድንግል ስደት  ሰአሊ ለነ ማርያም
እንባሽ የወረደው አንደ ሐምሌ ደመና ሐዘንሽ ልዩ ነው የእስራኤል መና  ሰአሊ ለነ ማርያም
ጥቂት እፎይ ያልሽው ያኔ በስደትሽ ኢትዮጵያ ስትደርሺ ነበር የተጽናናሽ  ሰአሊ ለነ ማርያም
እንግዲህ አሳስቢ ድንግል ስደትሽን የደረሰብሽን ረሃብ ጥምሽን  ሰአሊ ለነ ማርያም
ስደትሽን ላስብ ስደተኛ ነኝ የሰማዩ ቤቴ የሚናፍቀኝ  ሰአሊ ለነ ማርያም
ነይ ነይ ነይ በረድኤት በአማላጅነትሽ ይሰጠን ምህረት  ሰአሊ ለነ ማርያም
በይ በእናትነትሽ አመሌን ቻይው ትኅትና እንደሆን ከተፈጥሮሽ ነው

መዝሙር (ድንግል መከራሽን) October 14, 2018


 ድንግል መከራሽን
 ድንግል መከራሽን ጥቂት ባስታውሰው
 በሄሮድስ ዘመን ፍጥረት ያለቀሰው
 አንቺ የአምላክ እናት ደግሞም እመቤት
 እንደ ችግረኛ ተነሳሽ ስደት(፪)

ኧረ ለመሆኑ እንዴት አለቀልሽ
ስትከራተቺ በረሃውን ቆርጠሽ
ይገሉታል ብለሽ ለልጅሽ አስበሽ
በሄሮድስ ዘመን መከራሽን አየሽ (፪)

መዝሙር (ጻድቃን ሰማእታት) September 30, 2018


 ጻድቃን ሰማእታት በሙሉ በአካለ ሥጋና በአካለ ነፍስ /፪/ ያሉ
 ከፈጣሪ አማልደው እኛን ያስምራሉ

የእግዚአብሔር ዐይኖቹ ጻድቃንን ከማየት
ጆሮዎቹም አይርቁም እነርሱን ከመስማት
የጻድቅ ሰው ጸሎት ኃይልን ታደርጋለች
በምልጃቸው እንመን አናመንታ በአንዳች

 ጻድቃን ሰማእታት በሙሉ በአካለ ሥጋና በአካለ ነፍስ /፪/ ያሉ
 ከፈጣሪ አማልደው እኛን ያስምራሉ

ጊዜያዊው ፈተና ሳያሳቅቃቸው
እሳትና ስለት ሳያስፈራራቸው
ሰማያዊው ተስፋ ስለሚታያቸው
በፈተና ሁሉ ጸኑ በእምነታቸው

 ጻድቃን ሰማእታት በሙሉ በአካለ ሥጋና በአካለ ነፍስ /፪/ ያሉ
 ከፈጣሪ አማልደው እኛን ያስምራሉ

ኃጥኡ ነዌ እንኳን በሲዖል እያለ
ስለወንድሞቹ ምህረት ከለመነ
እናንተማ ጻድቃን በገነት ያላችሁ
ምንኛ ትረዱን አምነን ስንጠራሁ

 ጻድቃን ሰማእታት በሙሉ በአካለ ሥጋና በአካለ ነፍስ /፪/ ያሉ
 ከፈጣሪ አማልደው እኛን ያስምራሉ

ቀዝቃዛ ውኃ እንኳን በጻድቅ ሰው ስም
የሚያጠጣ ቢኖር ዋጋው አይጠፋም
ብሎ እንዳስተማረን ጌታ በወንጌል
አምነን እንፈጽመው ዋጋ ያሰጣል

መዝሙር 3 (ዝም አትበሉ) September 22, 2018


 ዝም አትበሉ እግዚአብሔርንአመስግኑ/፪/
 ቅዱስ/፭/ በሉ መላእክትን ሁኑ ምስጋናን ጨምሩ ቅዱስ/፪/ በሉ

የሙሴ እህት ማርያም ከበሮውን አንሽው
በምስጋና መዝሙር እስራኤልን ጥሪው
አምላክን እናክብር እንዘምር በእልልታ
ከእኛ ጋር ይሆናል የሰራዊት ጌታ ፪

 ዝም አትበሉ እግዚአብሔርንአመስግኑ/፪/
 ቅዱስ/፭/ በሉ መላእክትን ሁኑ ምስጋናን ጨምሩ ቅዱስ/፪/ በሉ

ፍጥረታትም ጩሁ ሰማያት ዘምሩ
ስለቅድስናው ውዳሴን ጨምሩ
ዳዊት ሆይ ተነሳ ስለፅዮን ዘምር
ከበሮው ይመታ በገናው ይደርደር ፪

 ዝም አትበሉ እግዚአብሔርንአመስግኑ/፪/
 ቅዱስ/፭/ በሉ መላእክትን ሁኑ ምስጋናን ጨምሩ ቅዱስ/፪/ በሉ

ወገኖች እንዘምር ለእግዚአብሔር ክብር
ውለታው ብዙ ነው ለእኛ ያለው ፍቅር
ማዳኑን ያያችሁ ዘምሩ በእልልታ
ለጌታ ለእግዚአብሔር ለሰራዊት ጌታ ፪

 ዝም አትበሉ እግዚአብሔርንአመስግኑ/፪/
 ቅዱስ/፭/ በሉ መላእክትን ሁኑ ምስጋናን ጨምሩ ቅዱስ/፪/ በሉ

ባህሩን አቋርጦ ወንዝ ያሻገራችሁ
ተራራውን ንዶ ያቀለለላችሁ
በአውሎ ነፋስ መሀል መንገድ አለው ጌታ
ለንጉስ ክርስቶስ እንዘምር በእልልታ ፪

 ዝም አትበሉ እግዚአብሔርንአመስግኑ/፪/
 ቅዱስ/፭/ በሉ መላእክትን ሁኑ ምስጋናን ጨምሩ ቅዱስ/፪/ በሉ

መዝሙር 2 (ደስ ይበለን) September 22, 2018


 ደስ ይበለን ደስ ይበለን
 አምላክ አለ መሃላችን
 ምን ይከፈል ለዚህ ሥራህ
 ገናና ነው አምላክ ክብርህ፤

ምሕረቱ አይተናልና
አድርሶናል አምላክ በጤና
ይችን እድሜ የጨመረልን
ለንስሐ ጊዜ የሰጠን

 ደስ ይበለን ደስ ይበለን
 አምላክ አለ መሃላችን
 ምን ይከፈል ለዚህ ሥራህ
 ገናና ነው አምላክ ክብርህ፤

ኃጢአትህ ይታገሰሃል
በቸርነት አምላክ ያይሃል
ደስታ ነው በሰማያት
በአንድ ኃጥእ የጽድቅ ሕይወት

 ደስ ይበለን ደስ ይበለን
 አምላክ አለ መሃላችን
 ምን ይከፈል ለዚህ ሥራህ
 ገናና ነው አምላክ ክብርህ፤

እልል በሉ የጐበኛችሁ
በምሕረቱ አምላክ ያያችሁ
በችግር ቀን ያሰበን ሁሉ
አመስግኑ ዝምም አትበሉ

 ደስ ይበለን ደስ ይበለን
 አምላክ አለ መሃላችን
 ምን ይከፈል ለዚህ ሥራህ
 ገናና ነው አምላክ ክብርህ፤

ድንግል ማርያም ትጸልያለች
ኃጥኡን ሰው ማረው እያለች
በድንግል ክብር እንኖራለን
በጽኑ ፍቅር አንድ እንዲያደርገን

 ደስ ይበለን ደስ ይበለን
 አምላክ አለ መሃላችን
 ምን ይከፈል ለዚህ ሥራህ
 ገናና ነው አምላክ ክብርህ፤