የሚኔሶታ ሃገረ ገዢ በቤት ውስጥ የመቆየት ትዕዛዝ (MN Stay Home Order)

በቤት ውስጥ የመቆየት ትዕዛዝ (Click here)

የሚኔሶታ ሃገረ ገዢ ትዕዛዝ ከ Mar 27 Apr 10 , 2020 ይቆያል። ከዚህ በታች ያሉትን ዕንስቃሴዎችን ብቻ ለማድረግ ከቤት መውጣት ይችላል

● ድንገተኛ አደጋ ወይም ሕመም ካጋጠመ
● የአካል ብቃት ዕንቅስቃሴዎች ለማድረግ
● ገበያ ሄዶ ምግብ መግዛት፣ ነዳጅ መቅዳት እና ከምግብ ቤቶች ምግብ አዝዞ ይዞ መውጣት
● ወደ መኖሪያ ቤት ለመመለስ የሚደረግ ከስቴት ወደ ስቴት ጉዞ
● ነዋሪነታቸው ሌላ ቦታ የሆነና ርዳታ የሚሹ ቤተሰብን፣ ጓደኛንና ድመትና የቤት እንስሳትን ለመንከባከብ
● ከአንዱ ጊዜያዊ መጠለያ ወደ ሌላ መጠለያ መልቀቅ
● ያሉበት ቦታ በጽዳትም ሆነ በሌሎች የተለያዩ ምክንያቶች ለደኅንነትዎ የሚያሰጋ ከሆነ ለደኅንነት ወደ ተለያየ ቦታ መሄድ