መዝሙር (እግዚአብሔር ሆይ እወድሃለሁ) March 31, 2024 (First Mezmur)

እግዚአብሔር ሆይ እወድሃለሁ
==============
 እግዚአብሔር ሆይ እወድሃለሁ
 ስለ ስምህ እቃጠላለሁ
 ፍቅርህ እኔን ይመስጠኛል
 እንደ እግዝአብሔር ከየት ይገኛል/2/

ዓለም ሁሉ በጠላኝ ጊዜ
ስንገላታ ይዞኝ ትካዜ
አንተ ከእኔ አልተለየህም
እግዚአብሔር ሆይ ወደር የለህም /፪/

 እግዚአብሔር ሆይ እወድሃለሁ
 ስለ ስምህ እቃጠላለሁ
 ፍቅርህ እኔን ይመስጠኛል
 እንደ እግዝአብሔር ከየት ይገኛል/2/

ሳዖል እኔን ሲያሳድደኝ
ጎልያድም ሲዝትብኝ
ግርማ ሆነህ ከፊቴ የቆምክ
እግዝአብሔር ሆይ ስምህ ይባረክ /2/

 እግዚአብሔር ሆይ እወድሃለሁ
 ስለ ስምህ እቃጠላለሁ
 ፍቅርህ እኔን ይመስጠኛል
 እንደ እግዝአብሔር ከየት ይገኛል/2/

ሞቷዋል ብለው ቀብረውኝ ሰዎች
ምስኪን ሁኜ ሳይኖረኝ አንዳች
ከመቃብር ቆፍሮ አወጣኝ
አይዞህ ብሎ አምላክ አፅናናኝ /2/

 እግዚአብሔር ሆይ እወድሃለሁ
 ስለ ስምህ እቃጠላለሁ
 ፍቅርህ እኔን ይመስጠኛል
 እንደ እግዝአብሔር ከየት ይገኛል/2/

ኃሳብህን በእግዚአብሔር ላይ ጣል
ለዘለዓለም ያበራልሃል
ታማኝ ወዳጅ እርሱ ነው እና
ሰላም ይሙላህ ለእርሱ ተውና /፪/

 እግዚአብሔር ሆይ እወድሃለሁ
 ስለ ስምህ እቃጠላለሁ
 ፍቅርህ እኔን ይመስጠኛል
 እንደ እግዝአብሔር ከየት ይገኛል/2/