መዝሙር (እያለፈ ነው ዘመኔ) April 14, 2024 (Second Mezmur)

እያለፈ ነው ዘመኔ ትዕዛዙን ሳልፈፅም ወየው ለኔ/2/
በጠራኝ ጊዜ ምን እላለሁ ና/ነይ/ ብሎ ወደ እኔ/2/

በወጣትነቴ ሳልሠራ እያየሁ አለፈኝ ብዙ አዝመራ/2/
ከእንግዲህ በመሥራት ጌታ ሆይ ልኑር ካንተ ጋራ/2/

የማስብበት በየዕለቱ ንፁህ ልብ ስጠኝ አቤቱ/2/
ከትዕዛዝህ ውጪ በመሆን እንዳልቀር በከንቱ/2/

እንደየሥራው ለመስጠት በግርማ መንግሥቱ ሲመጣ/2/
ማን ይሆን የሚቆም ከፊቱ ፈተናን የወጣ/2/

እንዳያስቷችሁ ተጠንቀቁ የተማራችሁ ከቃሉ/2/
ይመጣሉና በእርሱ ስም አምላክነን የሚሉ/2/

ትዕግስትን በመያዝ ሁላችሁ እስከመጨረሻው ጠንክሩ/2/
ያንጊዜ ይሆናል በሱ ዘንድ የማዳን ተግባሩ/2/