FCNP Open House: Feb 14

Feb 14 መልእክት ከጤና አገልግሎት ክፍል።


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን።

ከጽ/ቅ/ሥላሴ የበጎ አድራጎት የጤና አገልግሎት ክፍል የዛሬ ሁለት ሳምንት የካቲት 6 ቀን (Feb 14) ከቅዳሴ በኋላ የጤና አገልግሎት ክፍልን የመክፈቻ ጉብኝት አዘጋጅተዋል ። በዚህ ቀን ስለ ጤና ክፍል አገልግሎት ለማወቅ የምትፈልጉ ሁሉ በቢሮ ቁጥር 10 ተገኝታችሁ ስለሚሰጡት አገልግሎቶች እና እቅዶች እንድታውቁ ተጋብዛችኋል። በዚያን ቀን የጤና ክፍሉ ቀለል ያለ የቡና ቁርስ አዘጋጅቶ ይጠብቃችኋል። በዚህ የጤና ዘርፍ ለማገልገልገልና ለመገልገል የምትፈልጉ ሁሉ ከቅዳሴ በኋላ በጤና ክፍሉ ጽ/ቤ ተገኝታችሁ መነጋገር ትችላላችሁ።
ወስብሃት ለእግዚአብሔር።

ከጤና አገልግሎት ክፍል።