መዝሙር (እውነተኛ ሰላም) May 20, 2018


 እውነተኛ ሰላም ያለው ከቤትህ ነው(፪)
 እርዳኝ አልናወጽ እለምንሀለሁ(፪)

ሃጥያቴን ሳስበው ልቤ ይጨነቃል
ካንተ መለየቴ ነፍሴን አድክሟታል
ወዳንተ መልሰኝ እኔመለሳለሁ
እውነተኛ ሰላም ያለው ከቤትህ ነው

 እውነተኛ ሰላም ያለው ከቤትህ ነው(፪)
 እርዳኝ አልናወጽ እለምንሀለሁ(፪)

ለቅዳሴው ጸሎት ዘውትር እንዳልተጋሁ
ባደባባይ ቆሜ ስምህን እንዳልጠርልሁ
ተሰነካክዬ ወድቄአለሁ እና
እርዳኝ አማኑኤል በሀይማኖት ልጽና

 እውነተኛ ሰላም ያለው ከቤትህ ነው(፪)
 እርዳኝ አልናወጽ እለምንሀለሁ(፪)

አይኔ እንባን ያምንጭ ላልቅስ ስለ ሃጥያቴ
የንስሀ ትሁን ቀሪዋ ሕይወቴ
በመዳኔ ሰአት በዛሬዋ እለት
ፍርቅህ አስቤ መጣሁ ካንተ ፊት

 እውነተኛ ሰላም ያለው ከቤትህ ነው(፪)
 እርዳኝ አልናወጽ እለምንሀለሁ(፪)