ክብር ለሥላሴ (Glory to Trinity)

ሁሉንም በጊዜው ውብ አድ ርጎ ሠራው፣

እንደዚህ ይከብራል እግዚአብሔር የጠራው።

እንደ አዲስ ነደደ የእምነታችን ፍቅር፣

ውስጣችንን ቢባረክ ብትጠራን በክብር።

አንድ ሁለት እያልን ቀን ስንቆጥር ቆየን፣

ጌታ ሆይ መልካም ነህ ይኸው ሁሉን አየን።

 

የሚያቃጥል እሳት ሥጋን ተዋሐደ


የሚያቃጥል እሳት ሥጋን ተዋሐደ

ገብርኤል ተልኮ ብሥራት ሳይናገር፣

ዜናው ሳይሰማ የመምጣትህ ነገር፣

እረኞች ሳያዩህ በግርግም ተኝተህ፣

የሰው ልጅ ሳትባል ከድንግል ተወልደህ፣

አንደበት የሆንከው ኢሳይያስ ሲናገር፣

ሰማዮችን ቀደህ ውረድ ይልህ ነበር።

ከአንተ ሌላ ማንም ሰውን መች ረዳው፣

የገዛ ክንድህ ነው መድኃኒት ያመጣው።