Ethiopian Martyrs: April 19, 2015

ካራ በአንገታችሁ ጥይት በአናታችሁ፣
ሲቃጣ ቢያስፈራም በሰው እጅ ወድቃችሁ፣
የማይቀር ጽዋ ነው ለሞት ታዘዛችሁ ፣
ጽናትን ክርስቶስ በዚያች ቀን ሰጥቷችሁ።
አቤት ያቺ ሰዓት ምን ያህል ታስፈራ ፣
ተስሎ ሲዘጋጅ ጀርባችሁ ላይ ካራ ።
ዛሬ ከኔ ጋራ በገነት ነህ ያለው፣
ነፍሳችሁን ወስዷል በቀኙ ሊያኖረው ።
በካራ ተቆርጦ በጥይት ተመቶ አንገታችሁ ቢጣል
ሰው ሥጋን ነው እንጂ ነፍስን መች ይገድላል።

Click here to read more