ክረምት

ነሐሴ 7 ቀን 2006 ዓ.ም.

ዕጉለ ቋዓት፥ ደስያት

ይህ ወቅት ከነሐሴ 10 እስከ ነሐሴ 27 ቀን ድረስ ያሉት 17 ዕለታት የሚጠሩበት ነው፡፡ ፍጥረታትና በባሕር የተከበቡ ደሴቶች የሚታወሱበት ጊዜ ሲሆን ወቅቱም ዕጓለ ቋዓት ደስያት ዐይነ ኩሉ ይባላል፡፡ ዕጓለ ቋዓት የሚለው ቃል ቁራን ሲያመለክት፣ ቁራ ሲወለድ ያለ ፀጉር በሥጋው ብቻ ይወለዳል፡፡...

ፍልሰታና ሻደይ

ፍልሰታና ሻደይ

ነሐሴ 5 ቀን 2006 ዓ.ም.

ከጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ በኋላ በመላው ዓለም የክርስትና እምነት በሐዋርያቱ መሰበክ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ በኢትዮጵያ ሀገራችን የክርስትና እምነት ተሰብኳል፡፡  በተለይም ሀገራችን የሰሜኑ ክፍል  ህዝበ ክርስቲያኑ ለረጅም ዘመናት ሥርዓተ አምልኮ ሲፈጽምባቸው እንደነበሩና አሁንም አገልግሎት እየሰጡ እንደሆነ በአካባቢው የሚገኙ በርካታ ጥንታዊ አብያተ ክርስቲያናትና መንፈሳዊ ቁሶች ያስረዳሉ። እነዚህም የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ መንፈሳዊ ቅርሶች ናቸው። ከማይዳሰሱ መንፈሳዊ ቅርሶች መካከል የተለያዩ መንፈሳዊ...

ደብረ ታቦርና ቡሄ

 ነሐሴ 5 ቀን 2006 ዓ.ም.

መ/ር ሳሙኤል ተስፋዬ

የኢትየጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከምታከብራቸው ዘጠኝ ዓበይት በዓላት አንዱ የደብረ ታቦር በዓል ነው። በየዓመቱ ነሐሴ ፲፫ ቀን የሚከበረው ይህ በዓል መሠረቱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ደብረ ታቦር ኢየሱስ ክርስቶስ ሦስት ደቀመዛሙርቱን ይዞ ወደ ተራራው የወጣበትና ፊቱ እንደ ፀሐይ የበራበት፣ ልብሱም እንደብርሃን ነጭ የሆነበት፣ ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት ተራራ ነው።...

ጾመ ፍልሰታ

ሐምሌ 28 ቀን 2006 ዓ.ም.

መ/ር ሳሙኤል ተስፋዬ

ጾመ ፍልሰታ የእመቤታችን ዕረፍት፣ ትንሣኤና ዕርገቷ የሚታሰብበት ወቅት ነው፡፡ እመቤታችን በተለያዩ ጊዜያት ሞትና ትንሣኤዋን ለሐዋርያት የገለጸችበትን ምስጢር ከነሐሴ 1-16 ድረስ ምእመናን በጾም በጸሎት ተወስነው የልጇን ቸርነት የእርሷን አማላጅነት በሱባኤ ይማጸናሉ፡፡ የሱባኤው ወቅት ሲፈጸም “እመቤታችን በእውነት ተነሥታለች” ብለው በደስታ የጾሙን ወቅት ይፈጽማሉ፡፡ ሞቷ የሚያስደንቅ መሆኑን ቅዱስ ያሬድ “ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የሐጽብ ለኲሉ፤ ሞት ለማናቸውም ሰው ሁሉ የተገባ ነው፡፡...

ማቴዎስ ወንጌል

 ሐምሌ 9 ቀን 2006 ዓ.ም.

ምዕራፍ አምስት

የተራራው ስብከት /አንቀጸ ብፁዓን/


ይህ ምዕራፍ ልዑለ ባሕርይ አምላክ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ተራራ ወጥቶ ከፍ ካለ ቦታ ተቀምጦ ያስተማረው ትምህርት በመሆኑ የተራራው ስብከት በመባል ይታወቃል፡፡ ብፁዓን እያለ በማስተማሩም አንቀጸ ብፁዓን ይባላል፡፡ ጌታችን ከፍ ካለ ቦታ ተቀምጦ ያስተማረበት ምክንያት፣ መምህር ከፍ ካለ ቦታ ተማሪዎች ደግሞ ዝቅ ካለ ቦታ ተቀምጠው የሚማሩት ትምህርት ስለሚገባ ነው፡፡...

አነ ጽጌ ገዳም … ወከመ ጽጌ ደንጐላት በማእከለ አሥዋክ ከማሁ አንቲኒ እንተ ኀቤየ በማእከለ አዋልድ

መስከረም 25 ቀን 2007 ዓ.ም.

በዲ/ን በረከት አዝመራው

 

  • "እኔ የምድረ በዳ አበባ ነኝ … በሾህ መካከል ያለ የሱፍ አበባ ያማረ የተወደደ እንደሆነ አንችም በቈነጃጅት መካከል በእኔ ዘንድ እንደዚያ የተወደድሽ ነሽ፡፡" (መኃልይ. ፪፥፩)


ታላቁ የቤተክርስቲያን አባት ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ "አይንህን አንስተህ ፍጥረታትን ተመልከት፤ስለ እግዚአብሔር የሚናገሩ አሻራዎቹን በየቦታው ታገኛለህ፤ አይንህን ዝቅ አድርገህ ቅዱሳት መጻሕፍትን አንብብ፤ ስለ እርሱ የሚናገሩ ምሳሌዎችን ታገኛለህ" ይላል (Hymns Against Heresies)፡፡ ለኑሮ ፍጆታ ከሚጠቅመን...

አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል

 መስከረም 20 ቀን 2007 ዓ.ም. 


በእግዚአብሔርና በሰው ልጆች መካከል የነበረውን የጥል ግድግዳ ያፈርስ ዘንድ ከአምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን በኋላ ከሦስቱ አካል አንዱ አካል አምላካችን ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ፤ እንደ ሕፃናት ቀስ በቀስ አድጎ፤ ወንጌልን ለዓለም ሰብኮ፤ ለሰው ልጆች ቤዛ ይሆን ዘንድ፤ በሞቱ ሞትን ይሽር ዘንድ፤ በመስቀል ላይ ተሰቀለ፡፡ በትንሣኤውም ለሰው ልጆች ትንሣኤን አወጀ፡፡ በእግዚአብሔርና በሰው ልጆች መካከል የነበረውንም የጥል ግድግዳ አፈረሰ፡፡ የሰው ልጆች ያጣነው...

ደብረ ጽጋጋ አቡነ አኖሬዎስ ገዳም

anoros gedam 5.jpg

በመ/ር ሳሙኤል ተስፋዬ


anoros gedam 5.jpg የአቡነ አኖሬዎስ ገዳም ደሴ ዙሪያ በጽጋጋ የሚገኝ ሲሆን ከደሴ ወደ መካነ ሰላም በሚወስደው መንገድ በ12 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ገዳሙ የተመሠረተውም በ1317ዓ.ም በንጉሥ ዓምደ ጽዮን ዘመነ መንግሥት ሲሆን ግብፃዊው አቡነ ያዕቆብ ከግብፅ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው የደብረ ሊባኖሱን እጨጌ አቡነ ፊልጶስን አስጠርተው፤ ለስብከተ ወንጌል መስፋፋት “ኢትዮጵያ በአንድ ጳጳስ መወሰን የለባትም፡፡ ስለዚህ ዐሥራ ሁለት አበው መርጠን ክርስትና ይስፋፋ” ብለው ባቀረቡት ሐሳብ መሠረት፤ አቡነ ፊልጶስ ዘደብረ ሊባኖስ /ኤጲስ ቆጶስ/፣አቡነ አ...

ቅዱስ መስቀል ፍቅር ነው

meskele 1

መስከረም 14 ቀን 2007 ዓ.ም.

አባ ዘሚካኤል

meskele 1

ወሶበ ርእዮሙ እግዚእ ኢየሱስ ለእሙ ወለረድኡ ዘያፈቅር ይቀውሙ፤ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሚወደውን ደቀ መዝሙርና እመቤታችንን ከእግረ መስቀል ቁመው ባያቸው ጊዜ፣ ወይቤላ ለእሙ ኦ ብእሲቶ ነዋ ወልድኪ፤ አንቺ ሆይ ልጅሽ ይርዳሽ ያጽናናሽ አላት፡፡ ውሉድኪ ሲል ነው በዮሐንስ እኛን ለርስዋ መስጠቱ ነውና፡፡ ወይቤሎ ለውእቱኒ ረድ ነያ እምከ፣ ደቀ መዝሙሩንም እነኋት እናትህ ታጽናህ አለው እምክሙ ሲል ነው፡፡ በዮሐንስ እርስዋን ለኛ መስጠቱ ነውና፡፡(ዮሐ. 19: 26-27)

 ...

በዓለ ሲመቱ ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል

በዓለ ሲመቱ ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል
ዲ/ን ሽመልስ መርጊያ
ህዳር 8/2007 ዓ.ም
{gallery count=1 width=350 height=300 counter=1 links=0 alignment=center animation=3000}hidar12{/gallery}
 

የሰው ልጅ በገነት እንደ ቅዱሳን መላእክት በቅድስና አምላኩን በማመስገን በደስታ ይኖር ነበር፡፡ ነገር ግን “ክፉና ደጉን ከምታሳውቀው ዕፀ በለስ እንዳትበላ” ተብሎ የተሰጠውን ትእዛዝ በመተላለፉ ምክንያት ከአምላኩ ተለየ(ዘፍ.3፡6)፡፡እግዚአብሔር በአርአያውና በአምሳሉ የፈጠረው ሰው ክብሩን አጣ፣ ጸጋው ተገፈፈ፣ ፈጣሪውንም አሳዘነ፡፡ ቅዱሳን...

“ሰው ማለት ምን ማለት ነው?”

ነሐሴ 26 ቀን 2007ዓ.ም

ሰው ማለት ነፋሳዊነት፣ እሳታዊነት፣ ውኃዊነት፣ መሬታዊነት ባሕርያት ያሉት በነፍስ ተፈጥሮውም ነባቢት ለባዊትና ሕያዊት የሆነች ነፍስ ያለችው ፍጥረት ነው፡፡ እንዲህ ብለን ግን የሰውን ተፈጥሮ ጠቅልለን መናገር አይቻለንም፡፡ ምክንያቱም ሰውን ከሌሎች ፍጥረታት ይልቅ እጅግ ልዩ በሆነ መልኩ በእግዚአብሔር አርአያና አምሳል ተፈጥሮአልና፡፡ ስለዚህም ቅዱሳን አባቶች እንዲህ ብለው ሰው ለሚለው ስያሜ ትርጓሜ ይሰጡታል፡፡...

“በዚህች ዓመት ደግሞ ተዋት” ሉቃ.13÷6-9

ዲ/ን ተስፋሁን ነጋሽ

ጳጉሜ 3/2006 ዓ.ም.

adye abeba 2006

 

ጌታችንና መድኃኒታችን ፈጣሪያችንና አምላካችን እግዚአብሔር ወልድ /ኢየሱስ ክርስቶስ/ በመዋዕለ ሥጋዌው በምሳሌ አድርጐ ወንጌልን አስተምሯል፡፡ በምሳሌ ማስተማር ሊተላለፍ የተፈለገውን መልእክት ሲያስተላልፉት ምግብን በጣፈጠ መረቅ ፈትፍቶ እንደማጉረስ ያህል ይሆናልና፤ እንዲሁም አንድ መልእከት በምሳሌ ጣፍጦ በቋንቋ ዘይቤ ተውቦ ሲቀርብ ምሥጢሩ ልብን ይማርካል፡፡ ስለዚህ የሰው አእምሮ በሃይማኖት ልጓም ተስቦ ለምግባረ ጽድቅ እንዲዘጋጅ ጌታችን ለነጋዴው በወርቅ በዕንቁ፣ ለገበሬው በእርሻ በዘር፣ ለባልትና ባለ...

ርእሰ ዐውደ ዓመት ዮሐንስ

ርእሰ ዐውደ ዓመት ዮሐንስ

ጳጉሜን 5 ቀን 2006 ዓ.ም.

ዲ/ን ዘላለም ቻላቸው

"የአሕዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃል" /1ኛ.ጴጥ.4.3/


ርእሰ ዐውደ ዓመት ዮሐንስ መስከረም 1 ቀን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንና የኢትዮጵያውያን የዘመን መለወጫ በዓል ነው፡፡ ይህንን ምክንያት አድርገን በዚህ ጽሑፍ የዘመን አቆጣጠርን ምንነትና ታሪክ፣ የኢትዮጵያን የዘመን አቆጣጠር እንዲሁም የዘመን መለወጫ በዓልና አዲስ ዓመት ሊኖራቸው የሚገባውን መንፈሳዊ ትርጉምና ፋይዳ አስመልክተን አንዳንድ ነገሮችን እንመለከታለን፡፡ እግዚአብሔር ማስተዋሉን ያድለን፤...